ይህ ምስል አውሮፓና አሜሪካ እንዳይመስልዎ፤ ኢትዮጵያ እንጂ

ዛሬ የበረዶ ክምር የወረራት አሾካ ቀበሌ፣ ምዕራብ አርሲ ዞን ኮፈሌ ወረዳ

ዛሬ በምዕራብ አርሲ ዞን ውስጥ፤ ኮፈሌ ወረዳ አሾካ ቀበሌ የተከሰተ በረዶ ነው

ኢዛ (እሁድ መጋቢት ፲፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 22, 2020)፦ እንዲህ ያለው የበረዶ ክምር ሲታይ የተለያዩ የአውሮፓና የአሜሪካ ጎዳናዎች ይታወሳሉ። በምስሉ ላይ እንደሚታየው የበረዶ ክምሩ መንገዶችን ዘግቷል። አካባቢውንም ሸፍኗል። ይህ ግን አውሮፓ ሳይኾን የኾነው በምዕራብ አርሲ ዞን ውስጥ፤ ኮፈሌ ወረዳ አሾካ ቀበሌ ዛሬ መጋቢት 13 ቀን 2012 ዓ.ም. ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጃክ ማ ለአፍሪካ አገሮች ቃል የገባው የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መሣሪያዎች አዲስ አበባ ገቡ

ጃክ ማ እና አሊባባ ግሩፕ የኮሮና ቫይረስን ሥርጭት በአፍሪካ ለመቀነስ እያደረጉ ያለው የመጀመሪያው ዙር እርዳታ

ለ54ቱ የአፍሪካ አገራት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ጀምሮ ያጓጉዛል

ኢዛ (እሁድ መጋቢት ፲፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 22, 2020)፦ በጃክ ማ እና አሊባባ ግሩፕ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለአፍሪካ ለመሥጠት ቃል ከተገባው የተለያዩ የሕክምና መሣሪያዎች መካከል የመጀመሪያው ዙር አዲስ አበባ ገብቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ስካይላይት ሆቴል ለገቢ መንገደኞች የለይቶ ማቆያ ይኾናል

Skylight Hotel, Addis Ababa, Ethiopia

ለ14 ቀን በልዩ ማቆያ የመቆየት ግዴታ አለባቸው

ኢዛ (ቅዳሜ መጋቢት ፲፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 21, 2020)፦ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞችን ለ14 ቀን ለይቶ ለማቆየት የተሠጠውን የመንግሥት ውሳኔ ተከትሎ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለለይቶ ማቆያው በስሩ የሚተዳደረውን ስካይላይት ሆቴል አንዱ ማቆያ እንደሚኾን ገልጿል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኮረና ቫይረስ በምርጫ 2012 ጣልቃ ገብቷል

ምርጫው መካሔድ አለመካሔድ እየተመረመረ ነው

ምርጫው መደረግ አለበት፤ የለበትም የሚለው ሙቀት እየተለካ ነው

ኢዛ (ዓርብ መጋቢት ፲፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 20, 2020)፦ በመጪው ነኀሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ይካሔዳል ተብሎ ቀን የተቆረተለት ምርጫ፤ አሁን በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት መካሔድ አለመካሔዱ በምርጫ ቦርድ የሚወሰን መኾኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መሸታ ቤቶች ይዘጋሉ

Best Western Plus Addis Ababa

ኢዛ (ዓርብ መጋቢት ፲፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 20, 2020)፦ ዛሬ ማምሻውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መግለጫ እንደሚያመለክተው፤ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ አገልግሎት እንዳይሠጡ ገደብ ከተጣለባቸው መካከል የምሽት መዝናኛ ቤቶች ወይም መሸታ ቤቶች ናቸው። (ኢዛ)

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ እስረኞች ሊፈቱ ነው

PM Abiy Ahmed

የአመክሮ ጊዜያቸው የደረሱ፣ ሕፃናት የያዙና የወንጀል ድርጊታቸው አነስተኛ የኾኑት ይለቀቃሉ

ኢዛ (ዓርብ መጋቢት ፲፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 20, 2020)፦ የኮሮና ቫይረስ በማረሚያ ቤቶች ለመቆጣጠር አስቸጋሪ በመኾኑ በእስር ከሚገኙ ታራሚዎች መካከል የአመክሮ ጊዜያቸው የደረሰ፣ ሕፃናት የያዙና የወንጀል ድርጊታቸው አነስተኛ መኾኑ የተረጋገጠ ታራሚዎች ከእስር እንዲለቀቁ ተወስኗል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ 30 አገሮች በረራ አቆመ

Ethiopian Airlines

ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች ለ14 ቀኖች በልዩ ማቆያ የመቆየት ግዴታ ተጣለባቸው

ኢዛ (ዓርብ መጋቢት ፲፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 20, 2020)፦ በኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ምክንያት በረራዎቹን እንዲያቋርጥ ተደጋጋሚ ውትወታ ሲደረግበት የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ ወደ 30 አገሮች የሚያደርገውን በረራ አቋረጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በጎዋ ካትሪን አረፉ

Dr Catherine Hamlin

የፌስቱላ ኢትዮጵያ መሥራች ናቸው

ኢዛ (ሐሙስ መጋቢት ፲ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 19, 2020)፦ የበርካታ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ችግር በመፍታትና “ፌስቱላ ኢትዮጵያ” የሚል ስያሜ ያለው ግብረሰናይ ድርጅት በማቋቋም ከ60 ዓመታት በላይ የፌስቱላ ሕክምና የሠጡት ዶ/ር ካትሪን ሐምሊን አረፉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ