ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ እስረኞች ሊፈቱ ነው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
የአመክሮ ጊዜያቸው የደረሱ፣ ሕፃናት የያዙና የወንጀል ድርጊታቸው አነስተኛ የኾኑት ይለቀቃሉ
ኢዛ (ዓርብ መጋቢት ፲፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 20, 2020)፦ የኮሮና ቫይረስ በማረሚያ ቤቶች ለመቆጣጠር አስቸጋሪ በመኾኑ በእስር ከሚገኙ ታራሚዎች መካከል የአመክሮ ጊዜያቸው የደረሰ፣ ሕፃናት የያዙና የወንጀል ድርጊታቸው አነስተኛ መኾኑ የተረጋገጠ ታራሚዎች ከእስር እንዲለቀቁ ተወስኗል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ መጋቢት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. እንደገለጹት፤ ከዚህ በኋላ ወደ ማረሚያ የሚገባ ካለ ከቫይረሱ ነፃ መኾኑን በማረጋገጥ ይኾናል ብለዋል። ከዚህም ሌላ ሌሎች አማራጮችም ይወሰዳሉ ብለዋል።
ከማረሚያ ቤቶች ጋር ተያይዞ ከትናንት በስትያ ለአስራ አምስት ቀናት ጠያቂዎች እስረኞችን መጎብኘት እንደማይችሉ ተገልጾ እንደነበር አይዘነጋም። (ኢዛ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሠጥተዋል። (ኢዛ)



