ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ቅሬታ ተስምቷቸዋል

የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና ጠቅይላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ዶ/ር ዐቢይ በኮሮና ቫይረስ የከፋ ነገር ቢገጥመን እንኳን መዘጋጀት አደጋውን ይቀንሰዋል አሉ

ኢዛ (ሐሙስ መጋቢት ፲፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 26, 2020)፦ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በመንግሥት የወጡ መመሪያዎችና እርምጃዎች በአግባቡ እየተተገበሩ አለመኾኑን ዛሬ አዲስ አበባን ተዘዋውረው ከጎበኙ በኋላ ገልጸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ከ4 ሺህ በላይ እስረኞችን ከእስር እንዲለቀቁ ወሰነ

አዳነች አቤቤ

የ33ቱ ተጠርጣሪዎች ክስ ተቋረጠ፤ ጋዜጠኛ ፍቃዱ በይቅርታ ይለቀቃል

ኢዛ (ረቡዕ መጋቢት ፲፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 25, 2020)፦ የፌዴራሉ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመከላከልና ለመግታት ሲባል ከአራት ሺህ በላይ ታራሚዎች በይቅርታ፣ እንዲሁም 33 ግለሰቦች ደግሞ ክሳቸው ተቋርጦ እንደሚለቀቁ አስታወቀ። በይቅርታ ከእስር ከሚፈቱት ውስጥ ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ ይገኝበታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲሔዱ ተወሰነ

Ministry of Science and Higher Education - Ethiopia

ኢዛ (ረቡዕ መጋቢት ፲፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 25, 2020)፦ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመከላከል ሲባል በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎቻቸው እንዲቆዩ ተሠጥቶ የነበረው ውሳኔ ተሻሽሎ፤ ላልተወሰነ ጊዜ ወደየቤተሰቦቻቸው እንዲሔዱ የሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ ማሳለፉ ታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኤጀንሲው የፓስፖርት አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ ማቆሙን አስታወቀ

FDRE Immigration Nationality and Vital Event Agency

ለአዲስ ፓስፖርት ፈላጊዎችም ኾነ የማደስ አገልግሎት ቆሟል

ኢዛ (ረቡዕ መጋቢት ፲፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 25, 2020)፦ የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመከላከል ፓስፖርት የመሥጠትና የማደስ አገልግሎቱን ማቋረጡን አስታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመንግሥት ሠራተኞች ከነገ ጀምሮ ሥራ እንዳይገቡ ተወሰነ

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

እያንዳንዱ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የትኞቹ ሠራተኞቻቸው ከቤታቸው እንደሚሠሩ ይወስናሉ

ኢዛ (ማክሰኞ መጋቢት ፲፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 24, 2020)፦ የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች ከነገ መጋቢት 16 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ተጨማሪ ውሳኔ እስኪሠጥ ድረስ ሥራቸውን በቤታቸው ኾነው እንዲሠሩ ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሔደው 17ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ወሰነ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሳሪስ አካባቢ በባቡር አንድ ሰው ገጭቶ ቆሟል

Addis Ababas tram

የገተጨው ግለሰብ በሕይወት መኖር አለመኖሩ አልታወቀም

ኢዛ (ሰኞ መጋቢት ፲፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 23, 2020)፦ ሳሪስ አደይ አበባ አካባቢ የከተማ ውስጥ ባቡር አንድ ሰው ላይ ግጭቶ ማድረሱ ተጠቆመ። የተገጨው ግለሰብ በሕይወት መኖር አለመኖሩ አልታወቀም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መንግሥት ለኮሮና ቫይረስ አምስት ቢሊዮን ብር መደበ

PM Abiy Ahmed

ከጎረቤት አገሮች ወደ ኢትዮጵያ በየብስ መግባት ተከለከለ

ኢዛ (ሰኞ መጋቢት ፲፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 23, 2020)፦ የኮሮና ቫይረስን (ኮቪድ-19) ሥርጭትን ለመቀነስና ለመከላከል መንግሥት 5 ሚሊዮን ብር መመደቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ። ከጎረቤት አገሮች ወደ ኢትዮጵያ በየብስ የሚገቡ ማናቸውንም እንቅስቃሴዎች መታገዱንም አስታውቀዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ2012 ዓ.ም. 28ኛ ሳምንት አንኳር ወሬዎች

Special report on Coronavirus in Ethiopia

ከኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ መከሰት ጋር ተያይዞ የተፈጠሩ አንኳር ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ክስተቶች (ልዩ ጥንክር)

ኢዛ (ከየካቲት መጋቢት 7 - 13 ቀን 2012 ዓ.ም.)፦ የዓለምም የኢትዮጵያም ወቅታዊ አጀንዳ የኮሮና ቫይረስ እያስከተለ ያለው ጥፋት ነው። በኢትዮጵያም ይህ የአገር ሥጋት እየኾነ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ለመገደብ የተለያዩ እርምጃዎች እየወሰዱ መኾናቸውን የሚያመላክተው በዚህም ሳምንት የመገናኛ ብዙኀን ቀዳሚ ዜና የመንግሥትም ተከታታይ መረጃዎች የኮሮና ቫይረስን የተመለከተ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ