ዛሬ ሃያ ሁለት ሰዎች በሽብርተኝነት ክስ ተመሰረተባቸው

ኢትዮጵያ ዛሬ (ሰኞ ኅዳር ፭ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 14, 2016)፦ አቃቤ ሕግ፤ ከኦነግ አመራሮች ተልዕኮ በመቀበል በምዕራብ ወለጋ ውስጥ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ኹከት ፈጥረዋል ባላቸው ፳፪ (22) ሰዎች ላይ በሽብርተኝነት ዛሬ ክስ መመስረቱን ለኢትዮጵያ ዛሬ የደረሰው ዘገባ አስረዳ። ክሱ የተመሰረተው አዲስ አበባ በሚገኘው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፬ኛ ወንጀል ችሎት መሆኑ ታውቋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...





Ethiopia Zare (ማክሰኞ መስከረም ፳፬ ቀን ፪፲፻፱ ዓ.ም. October 4, 2016)፦ በጦር ኃይሎች፣ በዓለም ገና፣ በአየር ጤና፣ በጀሞ ሁለት፣ በቡሌ ሆራ፣ በፉሪ እና ቡራዩ አካባቢዎች ከፍተኛ ህዝባዊ አምጽ የተነሳ ሲሆን፣ በርካታ መኪኖች ከመቃጠላቸውም በላይ የሰው ሕይወት መጥፋቱን የኢትዮጵያ ዛሬ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የከተማው ነዋሪዎች ገለጡ። ህዝባዊ እምቢተኝነቱ የተጀመረው ዛሬ ከሰዓት በኋላ ወደ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ሲሆን፣ በተለያዩ ቦታዎች የተኩስ ድምፅ እየተሰማ መሆኑን ለመረዳት ችለናል።




