”የፍርሃት ከፈን፤ በጎንደር ተቀደደ፤ የጎሕ ብርሃን በኢትዮጵያ ፈነጠቀ!” ጎሕ

የጎንደር ሕብረት / GOHEthiopia Zare (ረቡዕ ሐምሌ 27 ቀን 2008 ዓ.ም. August 3, 2016):- ”የጎንደር ሕብረት” ትናንት ማክሰኞ ሐምሌ 26 ቀን 2008 ዓ.ም. (ኦገስት 2 ቀን 2016 እ.ኤ.አ.)፤ ”የፍርሃት ከፈን፤ በጎንደር ተቀደደ፤ የጎሕ ብርሃን በኢትዮጵያ ፈነጠቀ!” በሚል ርዕስ ያወጣውን ልዩ መግለጫ ለኢትዮጵያ ዛሬ ልኳል። መግለጫው በህወሓት የሚመራው ገዥ ፓርቲን አፈና፣ ጭቆናና በደል የመረረው ህዝብ፤ በተለይ ባላፈው እሁድ ሐምሌ 24 ቀን በጎንደር ከተማ ላይ ህዝባዊው ኃይል የነበረውን የጨለማ ዘመን ገፍፎ መውጣቱን አመላካች መሆኑን ጠቁሟል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከሆላንድ የገባውን ዲያስፖራ ስምንት ቦታ በሳንጃ የገደሉት አልተያዙም

ለይኩን እሸቱ. Leyikun Eshetu(ኢ.ኤም.ኤፍ) ከሚኖርበት ሆላንድ ወደ ትውልድ ሀገሩ ኢትዮጵያ የገባው ወጣት ለይኩን እሸቱ፤ በፋሲካ በዓል ዋዜማ ስምንት ቦታ በስለት ወግተው የገደሉት ወንጀለኞች እስካሁን አልተያዙም። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ገዳዮቹ ባለጊዜዎች ስለሆኑ ሟች ደመ ከልብ ሆኖ ቀርቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የግዕዝ ፊደል የዩናይትድ ስቴትስ የባለቤትነት መብት አገኘ

Geezedit. ግዕዝኤዲት

ዋና መሥሪያ ቤቱ ብራይተን ኮሎራዶ የሆነው የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር ቁጥሩ ዘጠኝ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ኃምሳ ሰባት የሆነ የዩናይትድ ስቴትስ የባለቤትነት መታወቂያ (ፓተንት) መጋቢት ፳፱ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. (አፕሪል 7 ቀን 2016 እ.ኤ.አ.) ማግኘቱን አስታወቀ። ፓተንቱ የተሰጠው ለፈጠራውና የኩባንያው ባለቤት ለዶ/ር አበራ ሞላ ሲሆን፤ ኩባንያው የእርሳቸውንና የባለቤታቸው የወ/ሮ ሠናይት ከተማ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንጋፋው የሳክስፎን ተጫዋች አርቲስት ጌታቸው መኩሪያ አረፈ

Artist Getachew Mekuria. አርቲስት ጌታቸው መኩሪያ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. April 4, 2016):- በ1927 ዓ.ም. የተወለደው አርቲስት ጌታቸው መኩሪያ ጥበብን የተቀላቀላት በመንገድ ላይ ታንቡር መቺ በመሆን ነው። ይህ የሆነው በ1940 ዓ.ም. ነበር ። በኋላም ጥበብን እየተከተላት እሷም ወዳለችበት እየጠራችው በ1948 ዓ.ም. በመዘጋጃ ቤት ተቀጥሮ በፊት ከሚያደንቃቸው በኋላም ለረጅም ዓመታት አብረውት ከሠሩት ከአርቲስት ተፈራ አቡነወልድና ከአርቲስት ወዳጄነህ ፍልፍሉ ጋር ተቀላቀለ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮንቴይነር የተጫነ ሰው ስዊድን ተገኘ

ፖሊስ በሕገወጥ መንገድ ሰዎችን የሚያሸጋግሩ አሉ ብሎ ይጠረጥራል

Ethiopian Airlines 787 dreamliner የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን (Foto: STEFAN MATTSSON)

Ethiopia Zare (ሰኞ የካቲት 28 ቀን 2008 ዓ.ም. Mar. 01, 2016)፡- ከአዲስ አበባ ሌሊት ተነስቶ ዛሬ ጠዋት በስዊድን መናገሻ ስቶክሆልም በሚገኘው የአርላንዳ አየር ማረፊያ ባረፈው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን የዕቃ ኮንቴይነር ውስጥ የተደበቀ የ27 ዓመት ዕድሜ ያለው አንድ ሰው መገኘቱን ፖሊስ ገለጸ። ይኸው ግለሰብ በስዊድን ጥገኝነት መጠየቁ ታውቋል። ፖሊስ በሕገወጥ መንገድ ሰዎች የሚያሸጋግሩ ወገኖች እንዳሉ ጥርጣሬ አለኝ፣ ጉዳዩን እያጣራኹ ነው አለ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ድረገጽ ተጠለፈ

Anon+

Ethiopia Zare (ሰኞ ጥር 30 ቀን 2008 ዓ.ም. Feb. 08, 2016)፡- በኢህአዴግ መንግሥት ሙሉ ቁጥጥር ስር ያለውና ጋዜጦችንና መጽሔቶችን የሚያሳመው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ድረገጽ “አኖን ፕላስ” (AnonPlus) በተሰኙ ያልታወቁ ወገኖች ከቅዳሜ ጥር 28 ቀን ጀምሮ ተጠለፈ (ሐክ ተደረገ)። ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ ድረገጹ እንደማይሠራ ለመገንዘብ ችለናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመጀመሪያው በግዕዝ ፊደል የሚጽፍ ኮምፒዩተር ገበያ ላይ ዋለ

ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ፊደል በላፕቶፕና በዲስክቶፕ ተቀርጾ አገልግሎት መስጠት ቻለ

The first Amharic, Geez laptop

Ethiopia Zare (ዓርብ ጥር 6 ቀን 2008 ዓ.ም. January 15, 2016)፡- ጋዜጠኛና ፀሐፊ ገነት አየለ የኢትዮጵያ ፊደላት እንደሌሎቹ የቋንቋ ፊደላት በላፕቶፕና በዴስክቶፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ተቀርጸው ለተጠቃሚዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ መቻላቸውን ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ችለናል። ይኸው የመጀመሪያው በኢትዮጵያ ፊደል የሚጽፍ ኮምፒዩተር በገበያ ላይ መዋሉ ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሰብዓዊ መብት ቀን በፍራንክፈርት ተከበረ

ዮሐንስ ደሳለኝ (ጀርመን - ፍራንክፈርት)

የሰብዓዊ መብት ቀን በፍራንክፈርት ተከበረ

በየዓመቱ ዲሰምበር 10 የሚከበረው የሰብዓዊ መብት ቀን ሐሙስ December 10,2015 በፍራንክፈርት የዋናው ባቡር ጣቢያ አካባቢ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ አመሸ። ከተለያዩ አገሮች የመጡ ተገን ጠያቂዎች የተገኙበት ይህ አከባበር ለየት ያለና የወቅቱ አጥንት ድረስ ዘልቆ የሚገባው ብርድ ያልበገረው ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በስዊድን ለአርበኞች ግንቦት ሰባት መርጃ ገንዘብ ተሰበሰበ

ወለላዬ ከስዊድን

አቶ ዘለሌ ፀጋ ስላሴ ዝግጅቱን በንግግር ሲከፍቱቅዳሜ ጥቅምት 20 ቀን 2008 ዓ.ም. (ኦክቶበር 31 ቀን 2015 እ.ኤ.አ.) በስዊድን ዋና ከተማ በስቶክሆልም ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ መርጃ የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ተደረገ። በዝግጅቱ ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ተገኝተዋል። በቦታው ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት አቶ አበበ ቦጋለ የውጪ እንቢተኝነት ሊቀመንበር እና አቶ ቸኮል ጌታነህ የንቅናቄው ከፍተኛ አመራር ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በፍራንክፈርት የእንግሊዝ ኮንስለር ፅ/ቤት የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ

በፍራንክፈርት የእንግሊዝ ኮንስለር ፅ/ቤት የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሰኔ 16 ቀን 2007 ዓ.ም.  June 23, 2015)፡- በጀርመን ፍራንክፈርት ትላንት ሰኞ ሰኔ 15,2007 (June 22,2015) የእንግሊዝ ኮንስለር ፅ/ቤት የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ። በዚሁ ታጋይ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን በኩል ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፈው የተሰጡበትን 1ኛ ዓመት ለማስታወስና እንዲሁም ላለፉት አንድ ዓመት ሁኔታዎችን በለዘብተኝነት የምትመለከተው ታላቋ ብሪታንያ ለራሷ ዜጋ ምንም ዓይነት ድጋፍና ከለላ ባለመስጠቷ ለማውገዝና አስፈላጊውን እርምጃ እንድትወሰድ ለማሳሰብ የተጠራው የተቃውሞ ሠልፍ ከጅምሩ ደማቅና አላማውን ያሳካ ነበረ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ