ለኢሳት መርጃ የገንዘብ ማሰባሰብ ተደረገ

ኢትዮጵያ ዛሬ (እሁድ ኅዳር ፲፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 20, 2016)፦ በስዊድን ርዕሰ ከተማ ስቶክሆልም ለኢሳት መርጃ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ተደረገ። ዝግጅቱን ያስተባበረው የስዊድን የኢሳት ድጋፍ ኮሚቴ ሲሆን፣ በዝግጀቱ ላይ በእንግድነት ጋዜጠኛ መሳይ መኮንንና ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀፀላ ተገኝተዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢትዮጵያ ዛሬ (እሁድ ኅዳር ፲፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 20, 2016)፦ በስዊድን ርዕሰ ከተማ ስቶክሆልም ለኢሳት መርጃ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ተደረገ። ዝግጅቱን ያስተባበረው የስዊድን የኢሳት ድጋፍ ኮሚቴ ሲሆን፣ በዝግጀቱ ላይ በእንግድነት ጋዜጠኛ መሳይ መኮንንና ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀፀላ ተገኝተዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢትዮጵያ ዛሬ (እሁድ ኅዳር ፲፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 20, 2016)፦ አንዴ በጸጥታ ችግር ሌላ ጊዜ በመንገድ ስራ ተሳቦ ላለፉት አራት ዓመታት ከህዝባዊው አደባባይ ርቆ የነበረው ታላቁ የኢትዮጵያ ሩጫ ዛሬ ወደ መስቀል አደባባይ ተመልሶ ተከናውኗል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢትዮጵያ ዛሬ (ቅዳሜ ኅዳር ፲ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 19, 2016)፦ አንዲት ኢትዮጵያዊት ስምንት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ሩፒስ (የሕንድ ገንዘብ) የሚያውጣ ሦስት ኪሎ ወርቅ ይዛ በኢንድራ ጋንዲ ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ በኩል ስትገባ የሕንድ ጉምሩክ ባለሥልጣን በቁጥጥር ስር አዋላት። ኢትዮጵያዊቷ በእጅዋ ላይ አስር ሺህ የአሜሪካ ዶላር እና ስድሳ ሺህ ሩፒስ ተይዞባታል። ግለሰብዋ በወርቅ ኮንትሮባንድ በሕንድ ፖሊስ ስትያዝ ሁለተኛ ጊዜዋ ነው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢትዮጵያ ዛሬ (ቅዳሜ ኅዳር ፲ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 19, 2016)፦ የአዲስ ጉዳይ መጽሔት አዘጋጅ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና አናንያ ሶሪ ትናንት አርብ ኅዳር ፱ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. ኮማንድ ፖስቱ ማሰሩን ለኢትዮጵያ ዛሬ የደረሰው ዘገባ አስረዳ። ጋዜጠኞቹ የታሰሩት በማኅበራዊ ድረገጾች ላይ በመሳተፋቸው መሆኑን ምንጮቻችን ጠቁመዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
(ቪኦኤ፣ ኅዳር ፲፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም./ኖቨምበር ፲፯ ቀን ፳፻፲፮ እ.ኤ.አ.) ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከመድረክ የወቅቱ ሊቀመንበር ጋር መሠረታዊ በሆኑ ፖለቲካዊ ችግሮች ላይ ለመነጋገር መወያየታቸው ተነገረ፤ እስካሁን ግን ከገዢው ግንባር ተጨባጭ እርምጃ እንዳልተወሰደ የመድረክ መሪ አስታውቀዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢትዮጵያ ዛሬ (ኀሙስ ኅዳር ፰ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 17, 2016)፦ በምህጻረ ቃል ሲፒጄ በሚባል የሚታወቀው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ዛሬ ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የመንግሥትን አያያዝ የተቹ ጋዜጠኞች ለእስር መዳረጋቸውን አስታውሶ "በአስቸኳይ እንዲፈቱ" ሲል በአጽንኦት ጠይቋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...“እኔ ገጠር ተቀምጬ ልጆቼን ከተማ ነበር የማኖራቸው። በታጣቂዎች መገደላቸውን ሰምቼ ወደ ሚኖሩበት ከተማ ስሄድ የሦስቱንም ወንድ ልጆቼን አስከሬን ደጄ ላይ ወድቆ አገኘሁት” - አቶ ጀማል ሁሴን ለአሜሪካ ድምፅ

(ቪኦኤ፣ ኖቨምበር ፲፮ ቀን ፳፻፲፮ እ.ኤ.አ.) በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምስራቅ አርሲ ዞን ውስጥ በሽርካ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ አቶ ጀማል ሁሴን የተባሉ ግለሰብ ሦስት ልጆቻቸው በታጣቂዎች እንደተገደሉባቸው ለአሜሪካ ድምጽ አፋን ኦሮሞ ዝግጅት ክፍል ገለጹ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢትዮጵያ ዛሬ (ኀሙስ ኅዳር ፰ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 17, 2016)፦ ዛሬ ኢትዮጵያ ኢንተርኔት ከዘጋች አርባ አምስተኛ ቀን ሆናት። ላለፉት አርባ አምስት ቀናት አገሪቱ ኢንተርኔት በመዝጋትዋ ቢያንስ ፲፫ (13) ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንዳጣች የኢትዮጵያ ዛሬ የዜና ዝግጅት ክፍል ”ሴንተር ቴክኖሎጂ ኢኖቬሽን” ከዚህ በፊት ያወጣውን መረጃ መሰረት በማድረግ ያሰላው ስሌት ጠቆመ። ስሌቱ ያላካተታቸው መስፈርቶች ቢካተቱ ኪሳራው ወደ ፴፱ (39) ሚሊዮን ዶላር ሊጠጋ ይችላል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢትዮጵያ ዛሬ (ኀሙስ ኅዳር ፰ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 17, 2016)፦ ኢትዮጵያ ኢንተርኔት በማግኘት ነጻነት ከዓለም አገራት ከመጨረሻዎቹ በአራተኝነት ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ”ፍሪደም ኃውስ” የተሰኘው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ያወጣው ዓመታዊ ሰነድ መጠቆሙን ኳርትዝ አፍሪካ ዘገበ። ከአፍሪካ የመጨረሻዋ አገር እንደሆነች ታውቋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
መንግሥት በተፈጥሮ ነው የሞቱት ቢልም፤ ሳይገደሉ እንዳልቀሩ ይጠረጠራል
ኢትዮጵያ ዛሬ (ረቡዕ ኅዳር ፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 16, 2016)፦ የተከበሩ የፓርላማ ተመራጭ ወ/ሮ አዲሴ ዘለቀ አዲስ አበባ በሚገኘው ጽሕፈት ቤታቸው ትናንት ተገድለው እንደተገኙና ዛሬ እንደተቀበሩ ለኢትዮጵያ ዛሬ የደረሰው ዘገባ አስረዳ። የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ”ባጋጠማቸው ድንገተኛ ሕመም” ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን ቢዘግቡም፤ ወ/ሮ መገደላቸውን የሚጠቁሙ ያልተጣሩ ፍንጮች እንዳሉ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ችለናል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...