በኑሩንበርግ ከተማ (ጀርመን) የተካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ
በጀርመኗ የኑሩንበርግ ከተማ ፌብሩዋሪ 17 እና 18 ቀን 2012 ዓ.ም. የከተማዋና የአካባቢው ነዋሪዎች ህዝባዊ ስብሰባ አካሂደዋል። ፌብሩዋሪ 17 ቀን ከሂዩማን ራይት ዎች ጋር በትብብር በተዘጋጀው ውይይት ላይ የሕግ ባለሙያዎች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች ተወካዮች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ የበጎ አድራጎት ድርጅት ተወካዮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ተወካዮች ተገኝተዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
የአዲስ አድማስ ጋዜጣ አዘጋጅ የሆነችው ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ከእስር በተፈታችበት ዕለት ከቃሊቲ እስር ቤት ጀምሮ ፈረንሣይ በሚገኘው መኖሪያ ቤትዋ ድረስ የነበረውን ትዕይነት በዚህ ሪፖርቷ ታስቃኘናለች። የአንድነት አመራሮች (እነ ኢ/ር ግዛቸው) እንዲሁም የመርኅ ይከበር አባላት (እነ ፕ/ር መስፍን) በወ/ት ብርቱካን ቤት መገናኘትን፣ የፖለቲከኞቹን አስተያየት፣ የህዝቡንና የአካባቢውን ሰዎች አስተያየት ታስነብበናለች። ወ/ት ብርቱካን ለጠ/ሚ መለስ ዜናዊ የፃፈችውን ደብዳቤ፣ የመንግሥት መገናኛ ብዙኀኑን ዘገባ፣ በተለይም በሰነዱ አንደምታ ላይ እና በ”ይቅርታው” ጉዳይ ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና እና የኢንስቲትዩት ኦፍ ሂዩማን ራይት መምህር የሆኑት ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋን አናግራለች። ዶ/ር ዳኛቸው ሰነዱን ከአራት ነጥቦች አንጻር በመመዘን ሰፋ ያለ ትንታኔ ሰጥተዋል። ይህንን ሰፋ ያለ ሪፖርታዥ ታነቡ ዘንድ እንጋብዛለን! … መልካም ንባብ!
የሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ ኃላፊዎችንና ኢትዮጵያውያንን አነጋገሩ 





