ኢህአዴግ ካባረራቸው አባላቱ ጋር ለእርቅ እየተነጋገረ ነው

Ethiopia Zare (እሁድ ግንቦት 29 ቀን 2007 ዓ.ም. June 7, 2015)፡- የትግል ታሪኩ ጥንካሬ በገዛ አባላቱ ተጋኖ የሚነገርለት ኢህአዴግ ሥልጣን ይዞ በቆየበት 24 ዓመታት ለህልውናው አስጊ የሆኑ ፈታኝ ጊዚያቶች በተደጋጋሚ አሳልፏል። ከእነዚህ ውስጥ በ1993 ዓ.ም. አመራሩ ለሁለት ተሰንጥቆ በነበረበት ጊዜ የደረሰው ውጣውረድ፣ በቀድሞው ጠ/ሚንስትር ሞት የደረሰው ክፍተት እንዲሁም የ1997ቱ ምርጫ ባስከተለው ህዝባዊ ዓመጽ መሬት ነክቶ የመመለሱ አደጋ የሚጠቀሱ ናቸው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
በኢትዮጵያ የተካሄደውን የ2007ቱን ምርጫ አስመልክቶ የቪኦኤ ጋዜጠኛ ሰለሞን አባተ ባጠናከረው ዘገባ፣ "አዲስ አበባ ውስጥ ከባነሮቹና እጅግ ከተጋነነው የሙዚቃ ጩኸት በተረፈ አገሪቱ በ90 ሚሊዮን ሕዝብ የተመላች አትመስልም፤ ባልተለመደ ሁኔታ እረጭ ያለ ምርጫ" በማለት የምርጫውን ሁኔታ ገልጦታል።






