ሦስተኛዋን ”እሁድ” - በአራዳ ምድብ ችሎት

ጽዮን ግርማ
ሦስተኛዋን ”እሁድ” - በአራዳ ምድብ ችሎት

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ስድስቱን ጦማሪያንና ሦስቱን ጋዜጠኞች በሰንበት ቀን ለሚሰየም ተረኛ ችሎት መቅጠሩን የተለመደ አድርጎታል። ከቀናት በፊት በሦስቱ ብሎገሮች አቤል ዋበላ፣ በፍቃዱ ኃይሉና ማኅሌት ፋንታሁን ላይ በተሰጠው የዐሥራ አራት ቀናት የጊዜ ቀጠሮ መሠረት የቀጠሮው ቀን ዛሬ ግንቦት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. ነበር። ዛሬ በዚህ ፍርድ ቤት ተገኝቼ የነበረውን ሁኔታ መከታተል ባልችልም ምንጮቼ የነገሩኝን ዝርዝር እንዲህ ጽፌዋለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሁለት ቀናት ክራሞት በአራዳ ምድብ ችሎት

ጽዮን ግርማ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.(በፋክት መጽሔት የታተመ)
የታሰሩት ስድስቱ ጦማሪያንና (Bloggers) ሦስቱ ጋዜጠኞች 3 jailed journalists and 6 bloggers
ሚያዚያ 17 እና ሚያዚያ 18 ቀን 2006 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር የዋሉት ስድስቱ ጦማሪያንና (Bloggers) ሦስቱ ጋዜጠኞች በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) ከታሠሩ ዛሬ ሃያ ሦስተኛ ቀናቸውን ይዘዋል። በእነዚህ ጊዜያት ውስጥም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ሁለት ጊዜ ቀርበዋል። እሁድ ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቀርቡ ብቻቸውን በመኾኑም የፍርድ ቤቱ ድባብ ምን ይመስል እንደነበር የሚያውቅ አንድም ታዛቢ ሰው አልነበረም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"የሳዑዲ መንግሥት በሕግ ሊጠየቅ ይገባል" በፍሎሪዳ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን

እሁድ ኖቨምበር 24 ቀን 2013 (እ.ኤ.አ.) በፍሎሪዳ ስቴትስ በምትገኘው ታምፓ ቤይ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት በሳዑዲ ዐረቢያ በሚገኙ የኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ኢሰብዓዊ በደል ከልብ እንዳስቆጣቸው ገልጠዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በስዊድን ጉተንበርግ ከተማ ሊደረግ የታሰበው የዓባይ ግድብ የቦንድ ሽያጭ ከሸፈ

ተቃዋሚው ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ መድረኩን ተቆጣጠሮ ያዘ (ቪዲዮ አለው!)

በስዊድን ጉተንበርግ ከተማ ሊደረግ የታሰበው የዓባይ ግድብ የቦንድ ሽያጭ ከሸፈ

ከኢትዮጵያ ዛሬ ሪፖርተር

"ይገርማል!" ብሎ መጀመር ይቻላል። አዎን ይገርማል! ከስቶክሆልም የሄድነው ወደ አዳራሹ የገባነው ጥሪ ባደረጉበት 13፡00 ሰዓት ነበር። እ.ኤ.አ ኦገስት 31 ቀን 2013.። ህዝቡ እስኪሰባሰብ ጥቂት ከተጠበቀ በኋላ ስብሰባው በአንድ የኢህአዴግ/ወያኔ ካድሬ ተከፈተ። እንዲህም አለ፤ "እዚህ እኛን ለመቃወም የመጣችሁ እንዳላችሁ እናውቃለን። ሃሳባችሁን እንድትናገሩ አንከለክልም፤ ነገር ግን ጩኸት፣ አላስፈላጊ ረብሻና ግርግር የምትፈጥሩ ከሆነ ወዮላችሁ! አስቀድመን ባዘዝነው የፖሊስ ኃይል እየተለቀማችሁ ትወጣላችሁ። መውጣታችሁ ብቻ አይደለም፤ ታሪካችሁ ይጠፋል፣ ውርደት ይከተላችኋል። በመለያ ቁጥራችሁም ላይ የሚጻፈው ወንጀል ዕድሜ ልካችሁን ይከተላችኋል።"

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሽግግር ም/ቤቱ በኦስሎ ከተማ የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባ አደረገ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት የኖርዌይ ቻፕተር ጠቅላላ ህዝባዊ ስብሰባ 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት የኖርዌይ ቻፕተር ጠቅላላ ህዝባዊ ስብሰባውን ሰኔ 15 ቀን 2005 ዓ.ም (ጁን 22 ቀን 2013) ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በተገኙበት ታሪካዊና ስኬታማ ህዝባዊ ስብሰባ አደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሁለት ወር ውስጥ ከ15 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ የመን ተሰደዋል

  • የመን ውስጥ ምላሱ የተቆረጠውን ሀፊዝ ጨምሮ 25 ኢትዮጵያዊያን ሆስፒታል ገብተዋል
  • ዮርዳኖስን መኪና ላይ አስረው መሬት ለመሬት ጎተቷት፣ (ሚሚ) ተደፈረች ... ቃለምልልስ

ግሩም ተ/ሀይማኖት

የመን ውስጥ ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርሰው በደል ከእለት ወደ እለት እየጨመረ መጥቷዋል። በጅቡቲ አድርገው ቀይ ባህርን ተሻግረው ወደ የመን የሚገቡትን ኢትዮጵያዊያንን በማገት 1000 እና 1500 የሳዑዲ አረቢያ ሪያል እና ከዛም በላይ ከወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲያስልኩ የሚያደርጉ አፋኞች መኖራችን ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ መግለጼ ይታወሳል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ በጀርመን በርሊን ተደረገ

በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ኖቨምበር 6 ቀን 2012 እ.ኤ.አ. በበርሊን ከተማ ያደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ Ethiopians protest in Berlin 2012-11-06

በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባለፈው ኖቨምበር ስድስት ቀን 2012 እ.ኤ.አ. በአይነቱ ልዩ የሆነ በተለያዩ መፈክሮች እና በኢትዮጵያ ባንዲራ ያሸበረቀ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን አደረጉ። ሰላማዊ ሰልፉን ያዘጋጀው በጀርመን የፖለቲካና የሲቪክ ማህበራት አንድነት ድርጅት (EPCOU) ሲሆን፣ በዕለቱም ከተለያዩ የጀርመን አካባቢ የሚኖሩ ቁጥራቸው ከ290 በላይ የሚገመት ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ህመም ማነጋገሩን ቀጥሏል

ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ PM Meles Zenawi

ደረጀ ሀብተወልድ

ላለፉት 21 ዓመታት በስልጣን የቆዩት መለስ ዜናዊ፤ የዛሬ ሁለት ወር የቡድን ሀያ አገሮች በዋሽንግተን ዲሲ የሬጋን ህንፃ ውስጥ ባደረጉት ስብሰባ ላይ ተገኝተው ገለፃ ሲያደርጉ ከጋዜጠኛ አበበ ገላው ተቃውሞ ባጋጠማቸው ማግስት ያደረባቸውን ህመም ተከትሎ፤ ከሥራ ገበታቸው ላይ ከጠፉ በትንሹ ጥቂት የማይባሉ ጊዜያት አልፈዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ