የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽልማትና ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ የገነነችበት ቀን
ኢዛ (ረቡዕ ታኅሣሥ ፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. December 11, 2019)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅና የሚሠጠውን የኖቬል ሽልማት (የዓለም የሰላም ኖቤል ሽልማት) በኦስሎ በታላቅ ክብር ተቀብለዋል። ዕለቱ ኢትዮጵያ የገነነችበት ቀን ለመኾን በቅቷል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢዛ (ረቡዕ ታኅሣሥ ፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. December 11, 2019)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅና የሚሠጠውን የኖቬል ሽልማት (የዓለም የሰላም ኖቤል ሽልማት) በኦስሎ በታላቅ ክብር ተቀብለዋል። ዕለቱ ኢትዮጵያ የገነነችበት ቀን ለመኾን በቅቷል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢዛ (ሐሙስ ጥቅምት ፳፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 7, 2019)፦ በኢትዮጵያ የሚደርሰው የሳይበር ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱንና ባለፉት ስድስት ዓመታት ውስጥ የሳይበር ጥቃት በ13 እጥፍ እንደጨመረ የኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) አስታውቋል። ኤጀንሲው ሰሞኑን እየተካሄደ ባለው የጥቃቱን ግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት አስመልክቶ ይፋ እያደረጋቸው ካሉት መረጃዎቹ እንደሚያመለክቱ፤ በ2012 በጀት ዓመት ብቻ የሳይበር ጥቃቱ መጠን 791 መድረሱ ነው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢዛ (ማክሰኞ ጥቅምት ፲፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. October 22, 2019):- ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ክስተቶች ተስተናግደዋል። የዶክተር ዐቢይ አሕመድ የዓለም የሰላም ኖቤል ሽልማት ከአገር አልፎ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ቀዳሚ ወሬ ሆኖ የተስተናገደበት ነበር። አሁንም ድረስ ወሬው በተለያየ መንገድ እየተተነተነና አስተያየቶች እየተሠጠበትም ይገኛል። ከዚሁ ጐን ለጐን የሚኒሊክ ቤተመንግሥት እድሳት ተጠናቅቆ ለሕዝብ ክፍት የሆነበት ሳምንት ነው። ይህም ብዙ አስተያየቶች ያስተናገደ ነበር።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ማቴዎስ ዘገየ (ከስዊድን)

በዚህ በያዝነው የአውሮፓውያን በጋ ሐምሌ ወር፣ የሰከነ የሕይወት እንቅስቃሴና የረጋ ጸጥታ የሚታይባት፣ ከአውሮፓ ጽዱ ከተሞች አንዷ የሆነችው የስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም፤ ፳ኛውን በአውሮፓ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዓመታዊ ስብከተ ወንጌል ጉባዔን በተሳካ ኹኔታ አስተናገደች።
በመላው አውሮፓ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በየዓመቱ የሚዘጋጀው ይኸው መንፈሳዊ ጉባዔ ከሐምሌ (ጁላይ) ፲፬ እስከ ፲፮ ቀን ፳፻፲፯ እ.ኤ.አ. ድረስ ከተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች የመጡ ምዕመናን፣ እንዲሁም ከአውሮፓ፣ ከአሜሪካና ከካናዳ የመጡ ብፁዓን ጳጳሳት በተገኙበት ነበር በተሳካ ኹኔታ የተካኼደው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...አክሊሉ ሀብተወልድ

(ሚያዝያ 27 ቀን 2009 ዓ.ም)፡- ሚያዝያ 27 ታሪካዊ ቀን ናት፤ ከሰባት አስርት ዓመታት በፊት ከፋሺስት ጣሊያን ወረራ በኋላ አገር ነጻነቷን ያወጀችበት ሕዝብ እንደ ሕዝብ ደስ የተሰኘበት ቀን ናት። የዛኔ በስደት የነበሩት ንጉሥ ከስደት መልስ አገራቸው የገቡበት ቀን ነው፤ ዛሬ ግን በደርግ ዘመነ መንግሥት በጽሑፋቸው ለአስር ዓመት ከስድስት ወር በማዕከላዊ ካሳለፉ በኋላ በዘመነ ኢሕአዴግ የ16 ዓመት እስር የተፈረደባቸው። ላለፉት 25 ዓመታት በስደት በአገረ አሜሪካ ሕይወታቸውን የገፉት የሦስት ልጆች እና የዘጠኝ የልጅ ልጆች አባት፤ አገራቸውን ለማቅናት ዕድሜ ዘመናቸውን ሲወጡ ሲወርዱ፤ አገሬን ... አገሬን እያሉ ሞታቸው ከስደት አገር ከወደ ዳላስ የተሰማው አንጋፋው ጎምቱ ጸሐፊ፤ የሕግ ባለሙያ፤ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ፖለቲከኛና ምሁር የአቶ አሰፋ ጫቦ ሥርዓተ ቀብር የተከናወነበት ቀን ነበር።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የጋምቤላ ጥቃትና ታፍነው የተወሰዱት ሕጻናት ጉዳይ

(ዶቼቬለ) ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በጋምቤላ ክልል አኝዋክ ዞን በጎን እና በጆር ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች ውስጥ ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሙርሌ ጎሣ ታጣቂዎች በጣሉት ጥቃት ከአስራ ስምንት ሰዎች በላይ መገደላቸውንና ከ22 በላይ ሕጻናት ታግተው መወሰዳቸውን ተቀማጭነቱን ለንደን ላይ ያደረገው ”አኝዋ ሰርቫይቫል” የተሰኘው ድርጅት ገለፀ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ) ስኳር የጫኑ 101 የከባድ ጭነት መኪናዎች አዋሽ ፍተሻ ጣቢያ ካለፈው ዓርብ ጀምሮ እየተጉላሉ ነው ሲል አገር በዝምታ ተውጣ በትዝብት የምትከታተለውን የስኳር ወሬ ወደ ፊት አምጥቶታል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ሪፖርታዥ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ በፓልቶክ ክፍል ቀርቦ የኦሮሞ ተወላጅ መሆኑን አስረግጦ ተናግሯል። ካፈርኩ አይመልሰኝ ነገር።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ወቅታዊ ሪፖርታዥ (ክንፉ አሰፋ)

በሳምንቱ መግቢያ የአውሮፓ ሕብረት በኢትዮጵያ ብሔራዊ እርቅ እና ድርድር እንዲደረግ ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል። አምስቱ የህወሓት ቁንጮዎች ትዕቢት የተሞላበት ምላሽ ነው የሰጡት። ከድርድር ይልቅ ከህዝብ ጋር ጦርነት መግጠምን መርጠዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ሳሚታ ተፈራ

እኔና ጓደኛዬ በስልካችን ምስልና ቪዲዮ እየቀረፅን ስለምንጓዝ ጉዟችን ቀርፋፋ ነበር። በምንሄድበት መንገድ የወታደሩ ቁጥር፤ መሣሪያ የደገኑ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች እጅግ ብዙ ከመሆናቸውም በተጨማሪ ደንበኛ ጦር ሜዳ በሚያስመስል መልኩ በመሬት ታንክ እና በሰማይ ላይ ደግሞ የጦር ተዋጊ ጄት ከ4:00 ሰዓት ጀምሮ በማንዣበብ ህዝቡን ሲያሸብሩ ነበር። እኛም ወደ ሆራ አርሰዲ በተጠጋን ቁጥር የህዝቡ ብዛት እና የህዝብ ጥያቄ የሚያስተጋቡ ዜማዎችና መፈክሮች ጠንከር ባለ መልኩ በዚያ አካባቢ በነበሩ የበዓሉ ታዳሚዎች በሙሉ ይስተጋባ ነበር።
ሙሉውን አስነብበኝ ...