ደቡብ አፍሪካ የሕብረቱ ሊቀመንበርነትን በመረከብ የአፍሪካ ሕብረት ጉባዔ ተጀመረ

PM Abiy Ahmed and South Afrian President Cyril Ramaphosa

ደቡብ አፍሪካ ሊቀመንበርነቱን የተረከበቸው ከግብጽ ነው

ኢዛ (እሁድ የካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 9, 2020)፦ ደቡብ አፍሪካ የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር በመኾን ለቀጣዩ አንድ ዓመት ለማገልገል የሚያስችላትን ኃላፊነት በመረከብ፤ 33ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ዛሬ የካቲት 1 ቀን 2012 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በሕብረቱ አዳራሽ ተጀመረ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ዛሬ ይጀምራል

PM Dr. Abiy Ahmed and Canadian PM Justin Trudeau

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ የበርካታ አገራት መሪዎችን ሲቀበሉ ነበር

ኢዛ (እሁድ የካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 9, 2020)፦ 33ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ከዛሬ የካቲት 1 እስከ የካቲት 2 ቀን 2012 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ይካሔዳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በስብሰባው ላይ ተካፋይ የኾኑ አገራትን ሲቀበሉ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኮሮና ቫይረስ የተጠረጠሩ 14 ሰዎች ማቆያ እንዲገቡ ተደረገ

Coronavirus in Ethiopia

ከቻይና የሚመጡ መንገዶች በቦሌ ለብቻቸው እንዲስተናገዱ ተወሰነ

ኢዛ (ዓርብ ጥር ፳፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 7, 2020)፦ የኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ ሊገባ ይችላል የሚል ሥጋት እየበረከተ ባለበት ወቅት እስካሁን በቫይረሱ የመያዝ ምልክት ያሳዩ 14 ሰዎች በለይቶ ማቆያ ሥፍራ እንዲገቡ ተደርጓል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በ22ቱ ግጭት ሕይወታቸው ያለፉ ወጣቶች የቀብር ሥነሥርዓት ተፈጸመ

Thousends gather at funeral for 2 youngster killed in 22, Addis Abab. (January 6, 2020)

ዛሬ የሦስተኛው ወጣት ሕይወት አልፏል

ኢዛ (ሐሙስ ጥር ፳፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 6, 2020)፦ ለትናንት አጥቢያ ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት በኋላ፤ በአዲስ አበባ በ22 አካባቢ ከቤተክርስቲያን ግንባታ ጋር ተያይዞ ተፈጠረ በተባለ ግጭት ሕይወታቸው ያለፈ የሁለት ወጣቶች ሥርዓተ ቀብር ዛሬ ጥር 28 ቀን 2012 ዓ.ም. በሺህዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተገኙበት ተፈጸመ። ሦስተኛውና የ17 ዓመቱ ወጣት ሕይወት ማለፉም ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጸጥታና ከደኅንነት ጋር ለተገናኙ ተቋማት አምስት ሹመቶች ሠጡ

Dr. Shumete Gizaw

ዶ/ር ሹመቴ ግዛው የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ኾነው ተሹመዋል

ኢዛ (ሐሙስ ጥር ፳፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 6, 2020)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከጸጥታና ከደኅንነት ጋር ለተገኛኙ ተቋማት ለአምስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ዛሬ ሹመት ሠጡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአዲስ አበባ ሃያ ሁለት አካባቢ በተፈጠረ ግጭት የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ

Eng. Takele Uma and His Holiness Abune Mathias I

በግጭቱ ተሳታፊነት የተጠረጠሩ ሰባት ሰዎች ታስረዋል

ኢዛ (ረቡዕ ጥር ፳፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 5, 2020)፦ በአዲስ አበባ 22 አካባቢ በሚገኝ ቦታ ላይ ቤተክርስቲያን እንገነባለን በሚሉ ወገኖችና በሕግ አስከባሪ አካላት መካከል ተፈጠረ በተባለው ግጭት የሰው ሕይወት ጠፋ። በድርጊቱ ተሳታፊ ናቸው የተባሉ ሰባት ሰዎች ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው መኾኑን ኢ/ር ታከለ ዛሬ በሠጡት መግለጫ ላይ አስታውቀዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቻይና በረራውን እንደማያቆም አረጋገጠ

Ethiopian Arilines

በረራውን ማቆም መፍትሔ አይሆንም የሚል አመለካከት ይዟል

ኢዛ (ረቡዕ ጥር ፳፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 5, 2020)፦ ከኮሮና ቫይረስ ክስተት ጋር ተያይዞ ሊፈጠር የሚችለውን ችግር ከግምት በማስገባት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርጋቸውን በረራዎች እንዲያቆም የሚለውን ውትወታ አየር መንገዱ የማይቀበለው ስለመኾኑ ተገለጸ። በረራውን ማቆም መፍትሔ አይሆንም የሚል አመለካከት ይዟል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢሕአዴግ መፍረስ በምርጫ ቦርድ ተወሰነ

TPLF vs Prosperity party

በሕወሓት የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ላይ ውሳኔ ሠጥቷል

ኢዛ (ማክሰኞ ጥር ፳፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 4, 2020)፦ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) በይፋ መፍረሱን የሚያረጋግጥ ውሳኔ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተወሰነ። ሕወሓት ኢሕአዴግ ስለፈረሰ የንብረት ልካፈል ጥያቄ በሊቀመንበሩ በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በተጻፈ ደብደቤ ማቅረቡ ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ማብራሪያ

PM Abiy Ahmed parliamentary hearing

የታገቱት ተማሪዎችን በተመለከት ምላሽ ሠጥተዋል

ኢዛ (ሰኞ ጥር ፳፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 3, 2020)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እንደሚሠጡ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ወቅታዊውን የዶ/ር ዐቢይ አንደበት ለመስማት ብዙዎች ጓጉተው ነበር። ዛሬ ከጠዋቱ ጀምሮ ሁሉም ማብራሪያውን ለመስማት የሚያስችለውን የሥርጭት አማራጭ አስተካክሎ ሲጠብቅ ነበር ማለት ይቻላል። ይሁንና ብዙዎች እንደጠበቁት ወይም ረፋድ ላይ ሳይሆን ፕሮግራሙ ከሰዓት በኋላ ነበር የተካሔደው። የታገቱት ተማሪዎችን በተመለከት ምላሽ ሠጥተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ2012 ዓ.ም. 21ኛ ሳምንት አንኳር ወሬዎች

Ethiopia Zare's weekly news digest, week 21, 2012 Ethiopian calendar

የዓመቱ ሃያ አንደኛ ሳምንት አንኳር ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ክንውኖች

ኢዛ (ከጥር 18 -24 ቀን 2012 ዓ.ም.)፦ በቀዳሚው ሳምንት ብዙ መነጋገሪያ ኾኖ የሰነበተው የደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች እገታ አሁንም መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል። የታገቱ ተማሪዎች እንዲለቀቁ መንግሥት ላይ ግፊት የሚያደርጉ የተቃውሞ ሰልፎች በተለዩ የአማራ ክልል ከተሞች ተደርገዋል። በአዲስ አበባም ትናንት ጥር 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ይደረጋል ተብሎ የነበረ ቢኾንም ሰላማዊ ሰልፉ አልተደረገም። ኾኖም ባሳለፍነው ሳምንት በዚህ ጉዳይ ላይ በተለየ የሚታየው ክስተት የመንግሥት ባለሥልጣናት በጉዳዩ ላይ መግለጫ መሥጠታቸው፣ የአማራ ክልል ጠንከር ያለና ተማፅኖም የነበረው መግለጫ ማውጣቱ ሊጠቀስ ይችላል። የታገቱ ተማሪ ወላጆችም ወደ አዲስ አበባ መጥተው ከባለሥልጣናቱ ጋር የተነጋገሩ ሲሆን፣ ታጋቾቹ በሕይወት አሉም ተብሏል። ግን አሁንም በዚህ እገታ ዙሪያ ያለው መረጃ ጥርት ያለ አይደለም የሚለው የብዙዎች ምልከታ እንደኾነ ይታወቃል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ