በኢትዮጵያ አራት አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪዎች ወደ ክትትል ማዕከል ገቡ

Ethiopia quarantines again four persons over coronavirus

አንዱ ቻይናዊ ሦስቱ ኢትዮጵያውያን ናቸው

ኢዛ (ሰኞ ጥር ፳፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 3, 2020)፦ በኮሮና ቫይረስ የተጠረጠሩ አንድ ቻይናዊና ሦስት ኢትዮጵያውያን በለይቶ ማቆያ ክትትል እየተረገላቸው መኾኑ ተገለጸ። እንደ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጻ ከኾነ፤ እነዚህ አራት ተጠርጣሪዎች ከዚህ ቀደም ተጠርጥረው ከነበሩት አራት ግለሰቦች ሌላ አዲስ ተጠርጣሪዎች ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ፓርላማ ይቀርባሉ

PM Abiy Ahmed

በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ይሠጣሉ ተብሎ ይጠበቃል

ኢዛ (ሰኞ ጥር ፳፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 3, 2020)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጥር 25 ቀን 2012 ዓ.ም. ፓርላማ ቀርበው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ይሠጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢዜማ አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲነት ሕጋዊ የሰውነት ማረጋገጫውን አገኘ

ኢዜማ

ሕጋዊ ሰርቲፊኬቱን የሠጠው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነው

ኢዛ (ኀሙስ ጥር ፳፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. January 30, 2020)፦ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ - ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ በመኾን ለመንቀሳቀስ የሚያስችለውንና ይህንኑ የሚያረጋግጥ የምዝገባና የሕጋዊ የሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተቀበለ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሐረር ከተማ መውጫና መግቢያ በቡድን በተደራጁ ወጣቶች ተዘግቶ ዋለ

Harar

የድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ከተማዋ እንዳይገቡ ደንገጎ ላይ መንገድ ተዘጋባቸው

ኢዛ (ኀሙስ ጥር ፳፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. January 30, 2020)፦ በዛሬው ዕለት በሐረር ከተማና አካባቢው ሰዎች ከከተማ እንዳይወጡና እንዳይገቡ መንገድ የተዘጋባቸው ሲሆን፤ ወደ ድሬ ዳዋ ይጓዙ የነበሩ የድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ሌሎች ተጓዦች ከወደ አዲስ አበባ ሊገቡ ሲሉ ደንገጎ በሚባል ቦታ መንገድ ተዘግቶባቸዋል። ሐረር መሐል ከተማ የሚገኙ አብዛኞች ሱቆች ተዘግተው መዋላቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ገልጸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የታገቱ ተማሪዎች የት እንዳሉ እንደሚያውቅ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

ኮሚሽነር እንደሻው ጣሰው የፊደራል ፖሊስ ኮሚሽነር፣ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሰክሬታሪያት ኃላፊና ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ

የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በጋራ መግለጫ ሠጡ

ኢዛ (ኀሙስ ጥር ፳፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. January 30, 2020)፦ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የታገቱት የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ያሉበትን ቦታ በተመለከተ ፖሊስ መረጃ እንዳለው ገልጸዋል። ይህ የተገለጸው ትናንት ጥር 20 ቀን ማምሻውን ሦስት የመንግሥት ተቋማት በጋራ በሠጡት መግለጫ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተቋረጠውን ትምህርት መጀመሩን ገለጸ

Dire Dawa University

ትምህርት ያቋረጡት ተማሪዎች በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲው አልተመለሱም

ኢዛ (ኀሙስ ጥር ፳፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. January 30, 2020)፦ የመማር ማስተማር ሒደቱን አቋርጦ የቆየው የድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ በከፊል የመማር ማስተማር ተግባሩን ስለመጀመሩ ገለጸ። ትምህርት ያቋረጡት ተማሪዎች በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲው አልተመለሱም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከሕወሓት የተፋቱት አቶ ዛዲግ በሚኒስትር ማዕረግ ተሾሙ

Zadig Abrha

ሿሚው ጠ/ሚ ዐቢይ ናቸው

ኢዛ (ረቡዕ ጥር ፳ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. January 29, 2020)፦ የሕወሓት ከፍተኛ አመራር አባል በመኾን ሲያገለግሉ የቆዩትና ይፋዊ በኾነ መንገድ ከሕወሓት መልቀቃችውን ያሳወቁት አቶ ዛዲግ አብርሃ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ተሾሙ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከፌዴራልና ከአዲስ አበባ መስተዳድር የተሻሩት የሕወሓት አባላት በትግራይ ተሾሙ

ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ፣ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔርና አስመላሽ ወልደሥላሴ (ከግራ ወደቀኝ)

ወ/ሮ ፈትለወርቅ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የፍትሕና መልካም አስተዳደር ኃላፊ ኾኑ

ኢዛ (ረቡዕ ጥር ፳ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. January 29, 2020)፦ በቅርቡ ከፌዴራል መንግሥትና ከአዲስ ከተማ አስተዳደር በከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊነታቸው የተነሱት ሁለት የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ሹመት ሠጣቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአማራ ክልል የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጐኑ እንዲቆም ጠየቀ

Protest in Amhara region over student abductions, January 28, 2020

ተማሪዎቹ ለታገቱበት ክልል ለኦሮሞ ሕዝብ ጥሪ አስተላልፏል

ኢዛ (ማክሰኞ ጥር ፲፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. January 28, 2020)፦ በደንቢ ዶሎ ተማሪዎች ላይ በተፈጸመው እገታና ጥቃት በአማራና በአማራ ተወላጅ ተማሪዎች ላይ ብቻ ሳይሆን፤ በሰብዓዊ ፍጡርና በዜጐች ላይ መኾኑን በመገንዘብ፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም ጥቃቱ የተፈጸመበት ክልል የኦሮሞ ሕዝብ ከጐናችን ይቁም ሲል የአማራ ክልል ብሔራዊ ክልል መንግሥት ዛሬ ጥር 19 ቀን 2012 ዓ.ም. አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የታገቱትን ተማሪዎች አስመልክቶ ከፍተኛ ሰላማዊ ሰልፍ በሃያ ዘጠኝ ከተሞች ተካሔደ

Protest in Amhara region over student abductions

“መንግሥት በእነዚህ ተማሪዎች እገታ ጉዳይ ላይ ግልጽ መረጃ ይሠጥ!”

ኢዛ (ማክሰኞ ጥር ፲፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. January 28, 2020)፦ ወደ ሁለት ወራት ለተጠጋ ጊዜ በእገታ ላይ መኾናቸው ሲገለጽ የቆዩትን የደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በተመለከተ እስካሁን ምንም ዐይነት መፍትሔ ባለመወሰዱ በአማራ ክልል ባህር ዳርን ጨምሮ በሃያ ዘጠኝ ከተሞች ዛሬ ጥር 19 ቀን 2012 ዓ.ም. ከፍተኛ ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ