በኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹ ቫይረሱ የተገኘባቸው ጃፓናውያን ወደ አገራቸው ተሸኙ
ኮሮና ቫይረስን በምስል ለማሳየት በበሽታ ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል የተሠራጨ
ኢዛ (ሰኞ መጋቢት ፲፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 23, 2020)፦ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ከታወቁት ከ11ዱ መካከል ሁለቱ ጃፓናውያን ወደ አገራቸው ዛሬ መሸኘታቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ከእነዚህ ከሁለት ጃፓናውያን መከከል አንደኛው ግለሰብ፤ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ የተገኘበትና ኢትዮጵያም ቫይረሱ የተገኘባት አገር መኾንዋን ሪፖርት ያደረገችበት መኾኑ ይታወቃል። (ኢዛ)



