ቢቢሲ በሦስት የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ስርጭት ሊጀምር ነው

ኢትዮጵያ ዛሬ (ረቡዕ ኅዳር ፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 16, 2016)፦ የብሪቲሽ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ቢቢሲ)፣ በሚቀጥለው የአውሮፓውያን አዲስ ዓመት (2017) የኢትዮጵያን ሦስት ቋንቋዎች ጨምሮ በአስራ አንድ የዓለም ቋንቋዎች አዲስ ስርጭት ሊጀምር መሆኑ ታወቀ። ኢትዮጵያውያን ቋንቋዎቹ አማርኛ፣ ኦሮምኛ እና ትግሪኛ መሆናቸው ታውቋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢትዮጵያ ዛሬ (ማክሰኞ ኅዳር ፮ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 15, 2016)፦ የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ፮ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ በዋለው ችሎት፤ በኢትዮ ምኅዳር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ ላይ የአንድ ዓመት እስራት እንደበየነበት ለኢትዮጵያ ዛሬ የደረሰው ዘገባ ጠቆመ። ጋዜጠኛ ጌታቸው ካለፈው ጥቅምት ፳፬ ቀን ጀምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ነበር።
አንኳር፣ ማክሰኞ ኅዳር ፮ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. ስርጭቱ የዕለቱን አንኳር ወሬዎች እንደሚከተለው ዘግቧል።



- መቅረብ ከነበረባቸው 22 ሰዎች አምስቱ አልቀረቡም
(ዞን ዘጠኝ) የዞን ዘጠኝ ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ ዛሬ (ዓርብ ኅዳር ፪ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም./ Nov. 11, 2016) ማለዳ 12:30 ሰዓት ገደማ ኮማንድ ፓስት ይፈልግሃል በሚል ሰበብ ከመኖሪያ ቤቱ በጸጥታ ኃይሎች ተይዞ፤ እዛው መኖሪያ ቤቱ አካባቢ በሚገኝው 06 ፖሊስ ጣቢያ ታስሯል።


