ኮማንድ ፖስቱ ትናንት ሁለት ተጨማሪ ጋዜጠኞቸን አሰረ

ኢትዮጵያ ዛሬ (ቅዳሜ ኅዳር ፲ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 19, 2016)፦ የአዲስ ጉዳይ መጽሔት አዘጋጅ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና አናንያ ሶሪ ትናንት አርብ ኅዳር ፱ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. ኮማንድ ፖስቱ ማሰሩን ለኢትዮጵያ ዛሬ የደረሰው ዘገባ አስረዳ። ጋዜጠኞቹ የታሰሩት በማኅበራዊ ድረገጾች ላይ በመሳተፋቸው መሆኑን ምንጮቻችን ጠቁመዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...

(ኢሰመፕ) ፌስቡክ ላይ በጻፋቸው ጹሁፎች ምክንያት የሽብር ክስ ቀርቦበት ጉዳዩ በፍ/ቤት እየታየ የሚገኘውና በእስር ቂሊንጦ ያለው የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ በሚገኝበት እስር ቤት ውስጥ ከአርብ ኅዳር 2/2009 ዓ.ም. ጀምሮ ቀንና ሌሊት በሰንሰለት ታስሮ እንደሚገኝ ታውቋል።


ኢትዮጵያ ዛሬ (ረቡዕ ኅዳር ፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 16, 2016)፦ በአራት ታዋቂ የተቃዋሚ ፓርቲ ሰዎች፤ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ አቶ አብርሃ ደስታ እና የፓርቲ አባል ባልሆኑት አቶ አብርሃም ሰለሞን የተከሰሱበትን ጉዳይ ለማየት የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ትናንት ቢሰየምም፤ የፌዴራሉ አቃቤ ሕግ በችሎቱ ባለመገኘቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ።
ኢትዮጵያ ዛሬ (ረቡዕ ኅዳር ፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 16, 2016)፦ ዛሬ በዋለው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፲፰ኛ ወንጀል ችሎት፣ የፌዴራሉ አቃቤ ሕግ ትናንት የእነ አቶ በቀለ ገርባ ጉዳይ ላይ ምስክርነት የመስጠቱ ሂደት በዝግ ችሎት እንዲታይለት ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አደረገበት።
መንግሥት በተፈጥሮ ነው የሞቱት ቢልም፤ ሳይገደሉ እንዳልቀሩ ይጠረጠራል


