የዶናልድ ትራምፕ ፕሬዝዳንትነትን ከ16 ዓመት በፊት በፊልም ተተንብዮ ነበር

Screen shot of The Simpsons

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥቅምት ፴ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. November 9, 2016):- ”ዘ ሲምፕሰንስ” የተሰኘው ተከታታይ የካርቱን ፊልም እ.ኤ.አ. ሁለት ሺህ መጀመሪያ አካባቢ (ከዛሬ ፲፮/16 ዓመት በፊት) ስለዶናልድ ትራምፕ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተንብዮ ነበር። ከፊልሙ ክፍሎች ውስጥ በተለይም ”Bart To The Future” በተሰኘው ርዕስ ስለአሜሪካ ቀጣይ ፕሬዝዳንት ሽፋን ሰጥቶ እንደነበረ በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን በዛሬው ዕለት ሲዘገብ ውሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአውሮፓ ሕብረት የፖለቲካ መሪዎችንና ታዋቂ ሰዎችን ማነጋገር ጀመረ

Prof. Berhanu Nega, Prof. Merera Gudina and Athlet Lelisa Feyesa in EU parlament

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥቅምት ፴ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. November 9, 2016):- ዛሬ የአውሮፓ ሕብረት በብራስልስ ባደረገው ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያውያኖችን ጋብዞ አነጋገረ። ከተጋባዦቹ መካከል ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ ፕ/ር መረራ ጉዲና እና አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ይገኙበታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዶናልድ ትራምፕ ፵፭ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆኑ

Donald Trump after he calls mexicans rapists and drug runners

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥቅምት ፴ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. November 9, 2016):- የአሜሪካ ሕዝብ በዘረኝነት፣ ሴቶችን አሳንሶ በመመልከት፣ ቀረጥ ባለመክፈል እና በተለያዩ ጉዳዮች ሲወነጀሉ የነበሩትን ዶናልድ ትራምፕ ፵፭ኛው (45ኛው) የአሜሪካ ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቃጠሎ ደረሰበት

Debre Markos University.

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጥቅምት ፳፱ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. November 8, 2016)፦ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ትናንት ማታ ቃጠሎ እንደደረሰበት ለኢትዮጵያ ዛሬ የደረሰው ዘገባ ጠቆመ። ቃጠሎው በይበልጥ የደረሰው የአዲስ ገቢ ተማሪዎች የወንዶች ማደሪያ ክፍሎች (ዶርሚተሪ) ላይ ሲሆን፣ ዛሬ ጠዋት ተማሪዎች ከግቢው ለመውጣት ቢሞክሩም እንዳይወጡ ተከልክለዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሹም ሽር አካሄዱ

፳፩ አዳዲስ ሚኒስትሮች ተሾሙ፣ ፱ኙ ባሉበት ቀጠሉ

PM Hailemariam Desalegne

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጥቅምት ፳፪ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. November 1, 2016)፦ በዛሬው ዕለት ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 21 አዳዲስ የካቢኔ ሹመቶችን ያቀረቡ ሲሆን፣ ፱ኙን ደግሞ ባሉበት ይቀጥላሉ ብለዋል። ፓርላማው ሹመቱን በሙሉ ድምፅ አጽድቆታል። በዚህ ሹም ሽረት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም እና አቶ ጌታቸው ረዳ ከሥልጣናቸው ተነስተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለስድስት ወር የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ (ሰበር ዜና)

“እንዴት ወደኋላ ተመልሶ፣ ከትናንት ምሽት ጀምሮ የሚሠራ አዋጅ ይታወጃል?”

PM Hailemariam Desalegn

Ethiopia Zare (እሁድ መስከረም ፳፱ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. October 9, 2016)፦ ትናንት የሚኒስትሮች ምክር ቤትን በአስቸኳይ የሰበሰቡት ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ምክር ቤቱን አባላት በማሳመን በሀገሪቱ ያለውን የህዝብ ተቃውሞና አለመረጋጋት ምክንያት በማድረግ ለስድስት ወር የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸው ታወቀ። ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከትናንት ማምሻ ቅዳሜ መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ተፈጻሚነት እንደሚኖረው ለማወቅ ችለናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ አበባ ተቆላልፋለች፤ ፖሊስ እና ሠራዊቱ በህዝብ ላይ አልተኩስም ብለዋል

ወቅታዊ ሪፖርታዥ (ክንፉ አሰፋ)

Addis Ababa joined the protest

በሳምንቱ መግቢያ የአውሮፓ ሕብረት በኢትዮጵያ ብሔራዊ እርቅ እና ድርድር እንዲደረግ ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል። አምስቱ የህወሓት ቁንጮዎች ትዕቢት የተሞላበት ምላሽ ነው የሰጡት። ከድርድር ይልቅ ከህዝብ ጋር ጦርነት መግጠምን መርጠዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአዲስ አበባ ነዋሪ ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ተቀላቀለ (ሰበር ዜና)

The protest started in Addis AbabaEthiopia Zare (ማክሰኞ መስከረም ፳፬ ቀን ፪፲፻፱ ዓ.ም. October 4, 2016)፦ በጦር ኃይሎች፣ በዓለም ገና፣ በአየር ጤና፣ በጀሞ ሁለት፣ በቡሌ ሆራ፣ በፉሪ እና ቡራዩ አካባቢዎች ከፍተኛ ህዝባዊ አምጽ የተነሳ ሲሆን፣ በርካታ መኪኖች ከመቃጠላቸውም በላይ የሰው ሕይወት መጥፋቱን የኢትዮጵያ ዛሬ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የከተማው ነዋሪዎች ገለጡ። ህዝባዊ እምቢተኝነቱ የተጀመረው ዛሬ ከሰዓት በኋላ ወደ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ሲሆን፣ በተለያዩ ቦታዎች የተኩስ ድምፅ እየተሰማ መሆኑን ለመረዳት ችለናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኢሬቻ በዓል ላይ ስለነበረው ሁኔታ አንድ የዓይን እማኝ ምስክርነት

ሳሚታ ተፈራ

Irrecha protest, 2nd Oct 2016

እኔና ጓደኛዬ በስልካችን ምስልና ቪዲዮ እየቀረፅን ስለምንጓዝ ጉዟችን ቀርፋፋ ነበር። በምንሄድበት መንገድ የወታደሩ ቁጥር፤ መሣሪያ የደገኑ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች እጅግ ብዙ ከመሆናቸውም በተጨማሪ ደንበኛ ጦር ሜዳ በሚያስመስል መልኩ በመሬት ታንክ እና በሰማይ ላይ ደግሞ የጦር ተዋጊ ጄት ከ4:00 ሰዓት ጀምሮ በማንዣበብ ህዝቡን ሲያሸብሩ ነበር። እኛም ወደ ሆራ አርሰዲ በተጠጋን ቁጥር የህዝቡ ብዛት እና የህዝብ ጥያቄ የሚያስተጋቡ ዜማዎችና መፈክሮች ጠንከር ባለ መልኩ በዚያ አካባቢ በነበሩ የበዓሉ ታዳሚዎች በሙሉ ይስተጋባ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ