በፍራንክፈርት የእንግሊዝ ኮንስለር ፅ/ቤት የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሰኔ 16 ቀን 2007 ዓ.ም.  June 23, 2015)፡- በጀርመን ፍራንክፈርት ትላንት ሰኞ ሰኔ 15,2007 (June 22,2015) የእንግሊዝ ኮንስለር ፅ/ቤት የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ። በዚሁ ታጋይ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን በኩል ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፈው የተሰጡበትን 1ኛ ዓመት ለማስታወስና እንዲሁም ላለፉት አንድ ዓመት ሁኔታዎችን በለዘብተኝነት የምትመለከተው ታላቋ ብሪታንያ ለራሷ ዜጋ ምንም ዓይነት ድጋፍና ከለላ ባለመስጠቷ ለማውገዝና አስፈላጊውን እርምጃ እንድትወሰድ ለማሳሰብ የተጠራው የተቃውሞ ሠልፍ ከጅምሩ ደማቅና አላማውን ያሳካ ነበረ።

የዕለቱን ዝግጅት ያስተባበረው (EPPCO HESSEN) — የኢትዮጵያ የፖለቲካና ሲቪክ ማህበራት ድርጅት ለ24 ሰዓት አቅዶት የነበረው ፕሮግራም በዕለቱ በነበረው ከባድ ዝናብና ንፋስ የቀላቀለ አየር ምክንያት ለሰባት ተከታታይ ሰዓት ተደርጐ ተጠናቋል።

በዕለቱም ከተለያዩ የፍራንክፈርት አካባቢ የመጡ ቁጥራቸው እስከ 200 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በአገሩ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ 3:00pm (15:00) በBOCKENHEIMER ANLAG 46 እንግሊዝ ኮንስለር ፅ /ቤት ፊት ለፊት በመሆን የተለያዩ መፈክሮችን ጬኸትና ዑዑታ በተሞላበት አኳኋን ካሰሙ በኋላ አስፈላጊውን መልዕክት የያዘ ደብዳቤ ለካውንስለሩ አስረክበዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሰልፉ ተሳታፊዎች ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ እየተባባሰ የመጣውን የሰብአዊ መብት ረገጣ እንዲሁም የዜጎች የማሰብ የመጻፍና የመናገር ነፃነት በከፋ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ በአሁኑ ሰዓትም አሳሳቢ ደረጃ እንደደረሰ የሚገልጽ ምስልና የታሰሩ ጋዜጠኞች ፣ ጦማሪያንና የፖለቲካ መሪዎች ፎቶ በመያዝ የምዕራባውያን መሪዎች ለወያኔ መንግሥት ድጋፋቸውን እንዲያቆሙና የታሰሩትም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ጫና እንዲፈጥሩ አሳስበዋል።

በዕለቱ ከተደረጉት ዋና ዋና ፕሮግራሞች ውስጥ አንዱ ከምሽቱ 10:00pm የተደረገው የሻማ ማብራት ስነስርዓት ነበር ክንውኑም የሚገርም ድባብ የነበረውና በአካባቢው የሚያልፉ የፍራንክፈርት ነዋሪዎችን ቀልብ የሳበ ሲሆን የአስተባባሪው ግበረ ኃይሎችም የሰልፉን ምንነትና ዓላማ የሚገልፅ በራሪ ወረቀት ለነዋሪዎቹ በትነዋል።

በፍራንክፈርት የእንግሊዝ ኮንስለር ፅ/ቤት የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ

እንደሚታወሰው አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ሰኔ 16,2006 ዓ.ም ከዱባይ ተነስተው በየመን በኩል አድርገው ወደ ኤርትራ በሚጓዙበት የየመን ጥቂት ቆይታ ወቅት የአለም አቀፍ መንገደኞችን ህግ በጣሰ ሁኔታ የየመን መንግሥት ባለሥልጣኖች ለአቻቸው የወያኔ መንግሥት ባለሰልጣናት ካስረከቧቸው በኋላ ያለፈውን አንድ ዓመት የጤንነታቸው ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ታውቋል። ይህንንም በተመለከተ ባለፉት ሳምንታት የእንግሊዝ ጋዜጦች ጠንከር ያለ መልዕክት ቢያስተላልፉም ለዘብተኛዋ እንግሊዝ የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ ብላለች፣ ያም ቢሆንም ቅሉ በምዕራቡ አለም ያሉ ኢትዮጵያውያን ያለመታከት ለአለፈው አንድ ዓመት ድምፃቸውን አሰምተዋል።

ከሰልፉ አስተባባሪዎች ለመረዳት እንደተቻለው በበርሊንና ሙኒከ ከተሞችም ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፉች ተደርገዋል።

በዕለቱ ከነበሩት መፈክሮች የሚከተሉት ጐልተው ተደምጠዋል ፣-

Brtain where Is Andargachew.

Brtain Andarhachew is one Year

In abduction.

Brtain Andargachew is one year

in torture.

Brtain Andargachew is one year

in solitary confinment.

He is not a terrorist he is

he is a freedom fighter

Free free free free Andargachew with no pre condtion.

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ