አቶ ልደቱ በዚህ ሳምንት ሁለት ጊዜ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

Lidetu Ayalew

ሁለተኛው ክሳቸው በፍርድ ቤት በመጪው ዓርብ ይነበባል

ኢዛ (ሰኞ ጥቅምት ፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 12, 2020)፦ አቶ ልደቱ አያሌው ሕገ መንግሥቱን ለመናድ በማሰብ የተለያዩ ሕገ መንግሥት የሚቃረኑ የሽግግር ሰነዶችን በማዘጋጀት በሚል በተከሰሱበት ሁለተኛው ክስ ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ.ም. ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በቤንሻንጉል ጉሙዝ 12 ንጹኀን ተገደሉ

Demeke Mekonen

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነዋሪው ትጥቅ መታጠቅ አለበት አሉ

ኢዛ (ሰኞ ጥቅምት ፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 12, 2020)፦ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪ ራሱን አደራጅቶ አስፈላጊውን ትጥቅ ታጥቆ የተጠናከረ መከላከል መገንባት አማራጭ የሌለው መኾኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ። በዞኑ ትናንት ሌሊት 12 ንጹኀን ተገድለዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአቶ ዳውድ መግለጫ በጸጥታ ኃይሎች መቋረጡ ተነገረ

Dawud Ibas

በጉዳዩ ላይ እስካሁን የተሰጠ ማብራሪያ የለም

ኢዛ (ሰኞ ጥቅምት ፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 12, 2020)፦ በቅርቡ በኦነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከኦነግ ሊቀመንበርነታቸው ተነስተዋል የተባሉት አቶ ዳውድ ኢብሳ፤ ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ.ም. በመኖሪያ ቤታቸው ሊሰጡ የነበረው መግለጫ በመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች መቋረጡ ተነገረ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢሳይያስ አፈወርቂ ጅማ ናቸው

Presidant Isaias Afwerki and PM Dr. Abiy Ahmed

በኢትዮ-ኤርትራ ግንኙነት ላይ ይመክራሉ ተብሏል

ኢዛ (ሰኞ ጥቅምት ፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 12, 2020)፦ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በሦስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሲሆን፤ አቀባበል የተደረገላቸው በጅማ ከተማ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ውዝግብ ውስጥ ባሉት የኦነግ አመራሮች ጉዳይ በምርጫ ቦርድ ተይዟል

ምርጫ ቦርድ፣ አቶ ዳውድ ኢብሳ፤ እገዳውን ካሳለፉት አመራሮች ሦስቱ

ከኦነግ የተለያዩ አካላት በቀረበለት አቤቱታ ምርጫ ቦርድ የመጨረሻ ውሳኔ እሰጣለሁ አለ

ኢዛ (ዓርብ መስከረም ፳፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 9, 2020)፦ በኦነግ ከፍተኛ አመራሮች መካከል በተፈጠሩ አለመግባባቶች ከተለያዩ የፓርቲው አካላት ሲደርሱት በነበሩት አቤቱታዎች ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚሰጥ አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በመተከል ሽብር ሲፈጥሩ ነበሩ የተባሉ 14 ታጣቂዎች ተገደሉ

ጋሹ ዱጋዝ

ታጣቂዎች አንድ የውጭ ዜጋን ጨምሮ አሥራ አራት ንጹኀንን ገድለዋል

ኢዛ (ሐሙስ መስከረም ፳፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 8, 2020)፦ በተደጋጋሚ የጸጥታ ችግር ሲስተዋልበት በቆየው የመተከል ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በመንቀሳቀስ ሽብር ሲፈጥሩ ነበሩ የተባሉ 14 ታጣቂዎችን መግደሉንና ሁለት መማረኩን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የምርጫ ቦርድ አባሉ የስንብት ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ

ምርጫ ቦርድ

የስንብቱን ደብዳቤ የጻፉት የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ ናቸው

ኢዛ (ረቡዕ መስከረም ፳፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 7, 2020)፦ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባልነታቸው በፈቃዳቸው እንደሚለቁና ይህንንም ጥያቄያቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቡት ዶ/ር ጌታሁን ካሣ ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቶ መሰናበታቸው ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በትግራይ ክልል ምክር ቤት ላይ የተላለፈው ውሳኔ ተጨማሪ ማብራሪያ ተሰጠበት

አደም ፋራህ
  • የፌዴራል መንግሥት የበጀት ድጎማ አያደርግም

  • የፌዴራል ተቋማት ከክልሉ ተቋማት መረጃ መለዋወጥ አይችሉም

  • ከቀበሌ፣ ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ጋር የሚኖረው ግንኙነት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ይወሰናል

ኢዛ (ረቡዕ መስከረም ፳፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 7, 2020)፦ የፌዴራል መንግሥት የትግራይ ክልል ምክር ቤትና የክልሉ ከፍተኛ የሕግ አስፈጻሚ አካላት ኢ-ሕገ መንግሥታዊ በኾነ ምርጫ የተቋቋሙ በመኾኑ፤ ለእነዚህ አካላት የፌዴራል መንግሥት የበጀት ድጐማ ማድረግ እንደማይችል የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፕሮፌሰር መስፍን በክብር ተሸኙ

Prof. Mesfin WoldeMariam's funeral

ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ታዋቂ ሰዎች ተገኝተዋል

ኢዛ (ማክሰኞ መስከረም ፳፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 6, 2020)፦ የእውቁ ምሁርና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ሥርዓተ ቀብር ዛሬ ማክሰኞ መስከረም 26 ቀን 2013 ዓ.ም. በክብር ተፈጽሟል። ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና ታዋቂ ሰዎች ተገኝተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሕወሓት በአመራር ላይ ያሉ አባላቱን ኃላፊነታቸውን ለቅቃችሁ ሪፖርት አድርጉ አለ

TPLF letter to Dr. Arkebe Oqubay

ለ27ቱ የሕወሓት የፓርላማ አባላትም ተመሳሳይ ጥሪ አስተላልፏል

ኢዛ (ሰኞ መስከረም ፳፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 5, 2020)፦ ሕወሓት በፌዴራል ደረጃ በተለያዩ የአመራር ደረጃ ለሚገኙ 13 አባላቱና በፓርላማ የድርጅቱ አባል ናቸው ላላቸው 27 የፓርላማ አባላቱ፤ ኃላፊነታችሁን አቁማችሁ ለድርጅታችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ ሲል ጥሪ አስተላለፈ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ