ፍርድ ቤቱ አቶ ልደቱ በአስቸኳይ እንዲፈቱ አዘዘ

Lidetu Ayalew

የቢሾፍቱ ፖሊስ ትእዛዙን ባይፈጽም አዛዡ ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታወቀ
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንም ማብራሪያ እንዲሰጥ ታዟል

ኢዛ (ሰኞ ጥቅምት ፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 19, 2020)፦ የምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ አያሌው ባስቸኳይ እንዲለቀቁና ይህ የፍርድ ቤቱ ትእዛዝ የማይፈጸም ከኾነ አቶ ልደቱን ይዞ በቆየው የቢሾፍቱ (ደብረዘይት) ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታወቀ። የኦሮሚያ ፖሊስም አቶ ልደቱ ታስረው እንዲቆዩ ያደረገበትን ምክንያት ቀርቦ እንዲያስረዳ ትእዛዝ ሰጥቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአገሪቱ ባንኮች አንድ ትሪሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ ሰበሰቡ

PM Abiy Ahmed

ባንኮች ካበደሩት 270 ቢሊዮን ብር 70 በመቶ ለግል ዘርፉ የተሰጠ ነው

ኢዛ (ሰኞ ጥቅምት ፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 19, 2020)፦ በተጠናቀቀው 2012 በጀት ዓመት በአገሪቱ ታሪክ ከፍተኛ የሚባለውን የአንድ ትሪሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ ባንኮች ማሰባሰባቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ተጠባቂው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ

PM Abiy Ahmed

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎች ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል

ኢዛ (ቅዳሜ ጥቅምት ፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 17, 2020)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከነገ በስቲያ (ሰኞ ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም.) በፓርላማ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢሳት ቴሌቪዥን መቋረጥ እየተነገረ ነው

ESAT

ችግሩ የፋይናንስ እጥረት ነው

ኢዛ (ቅዳሜ ጥቅምት ፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 17, 2020)፦ በሳተላይት የቴሌቪዥን ሥርጭት ከሚተላለፉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በአድማጭ ተመልካች ከሚዘወተሩት መካከል አንዱ በመኾን የሚታወቀው የኢሳት ሥርጭት መቋረጥ አነጋጋሪ ኾኗል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከ100 ሺህ እስከ 1.5 ሚሊዮን ብር የብር ኖት ለውጥ የጊዜ ገደብ ተጠናቀቀ

ዶ/ር ይናገር ደሴ (በግራ)፣ አቶ አሕመድ ሺዴ (መኻል) እና ዶ/ር ቀንአ ያደታ (በቀኝ)

እስካሁን ከ96 ቢሊዮን ብር በላይ ተሰራጭቷል
ሐሰተኛ የብር ኖት አታሚዎች እየተያዙ ነው
ከባንክ ውጭ ሲዘዋወር የነበረ 31 ቢሊዮን ብር ገቢ ተደርጓል

ኢዛ (ዓርብ ጥቅምት ፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 16, 2020)፦ እስካሁን በተካሔደው የብር ኖት ለውጥ ከ96 ቢሊዮን ብር በላይ መሰራጨቱንና ሐሰተኛ የገንዘብ ኖት ሲያትሙ ነበሩ የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የህዳሴው ግድብ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ተነስተው ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ተተኩ

Aregawi Berhe (PHD)

የቀድሞዋ ዳይሬክተር ሕወሓት ጥሪ ካደረገላቸው አባላቱ አንዷ ነበሩ

ኢዛ (ሐሙስ ጥቅምት ፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 15, 2020)፦ ከሕወሓት ቀደምት ታጋዮችና በኋላም ከሕወሓት አካሔድ በተቃራኒ በመቆም፤ የራሳቸውን ፓርቲ መሥርተው በመታገል የሚታወቁት የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) ሊቀመንበር ዶ/ር አረጋዊ በርሄ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ኾነው ተሾሙ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እነ ተመስገን ደሳለኝ ተፈትተዋል

ፍትሕ መጽሔት

የተፈቱት በራሳቸው ዋስ ሲሆን፤ ስትፈለጉ ትቀርባላችሁ ተብለዋል

ኢዛ (ሐሙስ ጥቅምት ፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 15, 2020)፦ ትናንት በፖሊስ ተይዘው ታስረው የነበሩት የፍትሕ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና ዋና አዘጋጁ ምስጋን ዝናቤ ዛሬ ከእስር ተለቀዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከአርቲስት ሐጫሉ ግድያ ጋር ተያይዞ ክስ የተመሠረተባቸው ፍርድ ቤት ቀረቡ

Hachalu Hundessa

የተጠቀሰውን ወንጀል አልፈጸምንም በማለት ቃላቸውን ሰጡ

ኢዛ (ረቡዕ ጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 14, 2020)፦ በአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ክስ የተመሠረተባቸው አራት ተከሳሾች የክስ መቃወሚያ የሌላቸው መኾኑንና ክስ የተመሠረተባቸውን ወንጀል አልፈጸምንም አሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ