የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ወሰነ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት

የፌዴራል መንግሥት በክልሉ ጣልቃ እንዲገባ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ አሳለፈ

ኢዛ (ቅዳሜ ጥቅምት ፳፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 7, 2020)፦ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ቅዳሜ 28 ቀን 2013 ዓ.ም. ባካሔደው አስቸኳይ ስብሰባ የፌዴራል መግንሥት በትግራይ ክልል ጣልቃ እንዲገባና ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም የቀረበለትን ሐሳብ በሙሉ ድምፅ አጸደቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአቶ ልደቱ አያሌው ጉዳይ ተለዋጭ ቀጠሮዎች ተሰጡ

Lidetu Ayalew

የጤና ሁኔታቸው አስጊ ደረጃ ላይ መኾኑን በማመልከት ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ መርምሮ ትእዛዝ ለመስጠት ለኅዳር 18 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ

ኢዛ (ሐሙስ ጥቅምት ፳፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 5, 2020)፦ አቶ ልደቱ አያሌው ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘት በተከሰሱበት ወንጀል መከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርቡ የኦሮሚያ ክልል የምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ብይን ሰጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሰብአዊ መብት ኮምሽን የትግራይ የጸጥታ ሁኔታ ያሳስበኛል አለ

Danile Bekele (PHD), Ethiopian Human Rights Commission

የሲቪል ሰዎች ደኅንነት መረጋገጥ ይኖርበታል ብሏል

ኢዛ (ሐሙስ ጥቅምት ፳፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 5, 2020)፦ ከወቅታዊው ጉዳይ ጋር በተያያዘ በትግራይ ክልል የሲቪል ሰዎችን ደኅንነት እና የሰብአዊ እርዳታ አገልግሎት አቅርቦት ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ እና እየተባባሰ የቆየውን የትግራይ ክልል የጸጥታ ሁኔታ የሚያሳስበው መኾኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮምሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ ሐሙስ ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የጸጥታ ኃይሉ ትጥቅ እንዲፈታ ጭምር የሚያስገድድ ነው

ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ

ግብረ ኃይሉ እንዳስፈላጊነቱ ማንኛውም የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ወደ ትግራይ ክልል እንዳይገባም ኾነ እንዳይወጣ ትእዛዝ መስጠት ይችላል

ኢዛ (ሐሙስ ጥቅምት ፳፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 5, 2020)፦ አዋጁ ተፈጻሚ በሚኾንበት ክልል ውስጥ ፖሊስ ወይንም ሌላ ማንኛውም የጸጥታ ኃይል ትጥቁን እንዲፈታ ትእዛዝ መስጠት የሚችል መኾኑ ተገለጸ። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዙሪያ ዛሬ ሐሙስ ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ.ም. ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፤ ግብረ ኃይሉ አካባቢውን ለመቆጣጠርና ሰላምን ለማስፈን አስፈላጊውን እርምጃ የመውሰድ ሥልጣንም እንደተሰጠው ገልጸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ኢትዮጵያውያን ከመከላከያ ጐን እንዲኾኑ ጥሪ አቀረበ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት

በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ አሳዛኝና አሳፋሪ ጥቃት ተፈጽሟል ብሏል

ኢዛ (ሐሙስ ጥቅምት ፳፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 5, 2020)፦ ከትናንት በስቲያ ምሽት ላይ በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ የተለያዩ ተቋማት ድርጊቱን በማውገዝ አቋማቸውን እያስታወቁ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለትም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ከመከላከያ ሠራዊት ጎን በመቆም ተገቢውን ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ ጥሪ አቅርቧል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በትግራይ ክልል ለታወጀው አስቸኳይ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ተሰየመ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

ቦርዱ ሰባት አባላት አሉት

ኢዛ (ሐሙስ ጥቅምት ፳፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 5, 2020)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ሐሙስ ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ.ም. ባካሔደው በመደበኛ ስብሰባው የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትግራይ ክልል ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማጽደቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላትን ሰየመ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሱዳንና ኢትዮጵያ በድንበር ላይ የተጠናከረ ጥበቃ ለማድረግ ተስማሙ

PM Abiy Ahmed (L) and Abdel Fattah Al-burhan (R)

ሱዳን ድንበርዋን ዘግታለች

ኢዛ (ረቡዕ ጥቅምት ፳፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 4, 2020)፦ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ ጠንካራ የጋራ የጸጥታ ለማካሔድ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር መስማማታቸውን የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እነጃዋር መሐመድ ለድኅንነታችን እንሰጋለን በማለት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ

Jawar Mohammed (L), Bekele Gerba (R)

“አሁን ባለው ሁኔታ በእነርሱ ላይ ጥቃት ቢፈጸም አገሪቷ የባሰ ችግር ውስጥ ትግባለች በማለት ነው ፍርድ ቤት ያልቀረቡት” አቶ ሃምዛ

ኢዛ (ማክሰኞ ጥቅምት ፳፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 3, 2020)፦ አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም. ፍርድ ቤት በነበራቸው ቀጠሮ ላይ ለደኅንነታችን እንሰጋለን በማለት ችሎት ሳይቀርቡ መቅረታቸው ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኤርትራ መንግሥት ሕወሓትን የሚወነጅል መግለጫ አወጣ

President Isaias Afwerki (L), Debretsion Gebremichael (PHD)

“ወያኔ በሞት ጣር ላይ ኾኖ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ግን፤ በአካባቢው የተፈጠረውን ሁኔታ ወደ ኋላ ሊመልሰው አይችልም” የኤርትራ መንግሥት

ኢዛ (ቅዳሜ ጥቅምት ፳፩ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 31, 2020)፦ በምሥራቅ አፍሪካ መታየት የጀመረውን ለውጥ ትግራይ ተቋዳሽ እንዳትኾን ሕወሓት እንቅፋት ኾኗል ሲል የኤርትራ መንግሥት አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ የፌዴራልና የትግራይ ክልል ፍጥጫ አሳስቦታል

International Crisis Group

ፍጥጫውን ትተው ወደ ድርድር እንዲመለሱ ጠይቋል

ኢዛ (ዓርብ ጥቅምት ፳ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 30, 2020)፦ ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ የፌዴራል መንግሥትና የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ከገቡበት ፍጥጫ ወጥተው ወደ ድርድር ይመለሱ ዘንድ ጠየቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ