”ዜሮ ቁጥር ነው ወይ?” ኃይሉ ገሞራው

ነፍሱን ይማረውና ባለቅኔው ኃይሉ ገብረዮሐንስ ገሞራው እ.ኤ.አ. ዲሴምበር 12 ቀን 1987 ዓ.ም. በእንግሊዝ ዋና ከተማ ሎንዶን በሦስት ቋንቋዎች (አማርኛ፣ እንግሊዝኛ እና ቻይንኛ) ግጥም አቅርቦ የነበረ ሲሆን፣ በአማርኛ ደግሞ ”ዜሮ ቁጥር ነው ወይ”? በሚል ርዕስ ስለ ዜሮ ቁጥር (አልቦ) ሰፋ ካለ ትንታኔ ጋር ግጥም አቅርቦ ነበር።

ክብብው ገዳ በአቶ መለስ፣ አባ ጳውሎስና ሃይሌ ከቀለደ በኋላ ያደረገው ቃለ ምልልስ

ክበበው ገዳ ሟቹ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፣ ኃይሌ ገብረስላሴ እና አባጳውሎስን የቀድሞ ድርጊት በማውሳት በአሜሪካን ሀገር ስራውን በመድረክ ማቅረቡ ይታወሳል። ይህንን ስራ ለትእይንት ካበቃ በኋላ የተለያዩ ማስፈራሪያዎችን ጨምሮ አድናቆቶችና አበረታች መልእክቶች ደርሰውታል። ክበበው በቫንኩቨር ካናዳ CFRO 100.5FM ከሚተላለፈው መለከት የኢትዮጵያ ራዲዮ ጋር ሰፊ ቃለ ምልልስ አድርጓል። (ቪድዮውን ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!)

የክበበው ገዳ አዲስ ኮሜዲ ስለ መለስና አባ ጳውሎስ ይኮምካል

ክበበው ገዳ በአሜሪካን ሀገር ባሳየው የመድረክ ትእይንት ያቀረበው ስራ በበርካቶች ዘንድ አነጋጋሪ ሆኗል። በዚሁ የመድረክ ስራው በተለይ ኃይሌ ገብረስላሴ ፕሬዝዳንትየመሆን ምኞት ላይና በሟች የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈት ላይ ያቀረበው ቀልድ ብዙዎችን ያስደነቀ ሲሆን አባ ፓውሎስ በህይወት በነበሩ ጊዜ የነበራቸውን ገጽታ በስራው አካቷል። (ቪድዮውን ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ