ታላቁ ገጣሚና ባለቅኔ ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) አሁንም በስደት በስዊድን መዲና ስቶክሆልም ይገኛል። አንዳንዶች ይህ ታላቅ የኢትዮጵያ ሀብት በሕይወት መኖሩን አያውቁም፣ የት እንደሚኖር የማያውቁም አሉ። ይህ ቪዲዮ በስዊድን የኢትዮጵያ ሙዚቃና ድራማ ቡድን ለታላቁ ገጣሚና ባለቅኔ ያበረከተለት ነው። በዚህ ቪዲዮ ላይ ያለው ሙዚቃ ደራሲ ዘነበ በቀለ ሲሆን፣ ምስልና ድምፅ ቅንብሩ ደግሞ በስዊድን የኢትዮጵያ ሙዚቃና ድራማ ቡድን ነው። ቪዲዮው የተዘጋጀው ሐምሌ 2002 ዓ.ም. (ጁላይ 2010 እ.ኤ.አ.) ነው።
ይህ አጭር ፊልም “Democracy is fair play” በሚል ርዕስ በያሬድ ሹመቴ የተዘጋጀ ነው። ዲሞክራሲን አስመልክቶ በዓለም በሚደረገው የአጭር ፊልሞች ውድድር ላይ ፊልሙ ቀርቦ ከፍተኛ ድምፅ ካገኙት 18 ፊልሞች ውስጥ አንዱ ለመሆን በቅቷል። ከ18ቱ ፊልሞች አሸናፊውን ለመለየት በዩቲዩብ እርስዎም ድምፅዎን መስጠት ይችላሉ። የሚከተለውን አስፈንጣሪ በመንካት (http://www.youtube.com/democracychallenge) ቀጥታ ወደ ድምፅ መስጫው መሄድ ይችላሉ። ከዚያም “VOTE” የሚለውን ይጫናሉ፣ በቀኝ በኩል ከሚመጡት ዘጠኝ ፊልሞች ውስጥ ኢትዮጵያውያን ህፃናት ያሉበትን ካላገኙት፣ በቀኝ በኩል ያለውን ቀስት ሲነኩት ቀሪዎቹን ዘጠኝ ፊልሞች ያገኛሉ። ፊልሙን ሲያገኙ አንድ ጊዜ ይጫኑት፣ ከዚያም ከፊልሙ በታች ያለውን አረንጓዴ እጅ በመጫን ድምፅዎትን ይስጡ! … በዚህ ድምፅ አሰጣጥ ድምፅዎ በትክክል ለመረጡት ይደርሳል። ድምፄ ይሰረቃል ብለው አይስጉ! የኢትዮጵያው ምርጫ ቦርድ እዚህ እጁ አይደርስም። ወደ ድምፅ መስጫ ጣቢያው ውሰደኝ!
”በእውነት ኢትዮጵያውያን ለመብታችሁና ለሀገራችሁ ምን እየሠራችሁ ነው?” በማለት ዳያስፖራውን የሚጠይቀው አሜሪካዊው የፊልም ፀሐፊ፣ ፕሮዲዩሰር እና ዳይሬክተር ክሪስ ፍላህሪቲ ነው። ክሪስ ”ማይግሬሽን ኦፍ ቢዩቲ” (Migration of Beauty) የተሰኘ ጥናታዊ ፊልም ዳይሬክተር መሆኑ ይታወቃል። ”... እኔ በግሌ የማደርገውን አውቃለሁ፤ እናንተስ? ... በዋሽንግተን ዲሲ ኋይት ሐውስ በማደርገው የረሃብ አድማ ስንቶቻችሁ ናችሁ ልትሳተፉ የምትችሉት? ...” በማለት በተለይም በስደት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለትውልድ ሀገራቸውና ለመብታቸው ምን ያህል እየታገሉ ስለመሆኑ ወሳኝ ጥያቄዎች ይጠይቃሉ። ... ቪዲዮውን ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!
በዕለቱ ጠ/ሚንስትሩ ፀያፍ ቃላትን ከመጠቀማቸው በተጨማሪ፤ የተቃዋሚ ፓርቲዎች የፓርላማ ተወካዮች ጠ/ሚንስትሩ በጥያቄ አፈጥጠዋቸዋል። ጠ/ሚ መለስ ፀያፍ ቃላትን እንዳሻቸው ሲጠቀሙ፤ ሥርዓት ባለው መንገድ የሚናገሩትን ተቃዋሚዎች ግን አፈጉባዔው እንዳይናገሩ ሲያግዷቸው ይህ ቪዲዮ ያሳያል። ለአንባብያን ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ የ6 ደቂቃ ከ26 ሰከንዱን ቪዲዮ ይመለከቱ ዘንድ እንጋብዛለን።