ከዚህ በታች “ጨንበላላ” የተሰኘው ዘፈን ሦስት የተለያዩ ቪዲዮዎችን ያገኛሉ። ቪዲዮ አንድ - “ጨንበላላ” በተሰኘው የዮሐንስ በቀለ (ቶክቻው) ዘፈን የተቀናበረ በአኒሜትድ የእንስሳት ዳንስ ሲሆን፣ ቪዲዮ ሁለት (ከቪዲዮ አንድ በታች ያገኙታል) - በኦፊሴል የተለቀቀው “ጨንበላላ” ቪዲዮ ነው። ቪዲዮ ሦስት ደግሞ “ጨንበላላ 2” የሚል መጠሪያ የተሰጠው የቪዲዮ ክሊፕ ነው።
ቪዲዮ ፩ - እንስሳት የሚደንሱበት
ቪዲዮ ፪ - "ጨንበላላ" ክፍል አንድ ዋና ቪዲዮ
ቪዲዮ ፫ - "ጨንበላላ" ክፍል ሁለት ዋና ቪዲዮ
"ሰው - አቤልና ቃዬል" የተሰኘውን ዘፈን አርቲስት ቴድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ከእስር ከተለቀቀ በኋላ የተጫወተው አዲስ ዘፈን ሲሆን፣ ጥቅምት 1 ቀን 2002 ዓ.ም. (ኦክቶበር 11 ቀን 2009 እ.ኤ.አ.) በአዲስ አበባ ስታዲየም ለምኖ አዳረዎችን ለመርዳት ባዘጋጀው ኮንሰርት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ለህዝብ ተጫውቶታል።
ዜማ በሔኖክ ገብሬ፣ ግጥም በማትያስ ከተማ (ወለላዬ)
(ለማዳመጥ የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!)
በአውሮፓ የሚገኝ ”ባውንስ የመንገድ ላይ ዳንስ ካምኒ” (BOUNCE Streetdance Company) የተሰኘ የዳንስ ድርጅት በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም፣ ጁላይ 8 ቀን ከሰዓት በኋላ በሰገል ጎርየት እና ከሌሊቱ 5 ሰዓት ላይ በስቱሬፕላን 300 የመንገድ ላይ ዳንሰኞችን በማስተባበር ማይክል ጃክሰንን በኦፊሴል መንገድ ማሰብ አክብሮ ዋል። ድርጅቱ በመላው ዓለም ያሉ የማይክል ጃክሰን አፍቃሪዎችንና መሰል ድርጅቶችም በተመሳሳይ ዝግጅት አርቲስቱን እንዲያስቡት ጥሪ አቅርቧል። ቪዲዮውን ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!