የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5





ወ/ሮ ሂላሪ ክሊንተን የአፍሪካ አምባገነን መሪዎችን አስጠነቀቁ
የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ወ/ሮ ሂላሪ ክሊንተን ጁን 13 ቀን 2011 እ.ኤ.አ. በአዲስ አበባ ለአፍሪካ ሀገራት ዲፕሎማቶች ንግግር አድርገዋል። በዚህ ንግግራቸው ለአፍሪካ መሪዎች የመንግሥት አስተዳደራቸውን አስመልክተው ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል። ሙሉውን ንግግራቸውን ከዚህ በታች በቪዲዮ ቀርቧል። ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!





የገዥው የኢህአዴግ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት ቅዳሜ ሚያዝያ 1 ቀን 2003 ዓ.ም. (April 9, 2011 እ.ኤ.አ.) በዋሽንግተን ዲሲ ከደጋፊዎቻቸው ጋር ሊያደርጉት የነበረውን ስብሰባ ተቃዋሚ ኢትዮጵያውያን አከሸፉባቸው። ይህንን አስመልክቶ ኢሳት ያቀረበውን ዘገባ ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!





በዋሽንግተን ዲሲ የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሚያዝያ 1 ቀን 2003 ዓ.ም. (April 9, 2011 እ.ኤ.አ.) ከደጋፊዎቻቸው ጋር ሊያደርጉት የነበረውን ስብሰባ በከተማዋ እና አካባቢዋ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ በማሰማታቸው የከተማዋ ፖሊስ ስብሰባውን በተነው። ክስተቱን የሚያሳየውን ቪዲዮ ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!
የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ዲሴምበር 13 ቀን 2003 እ.ኤ.አ. 424 አኝዋኮች በወያኔ/ኢህአዴግ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በአስከፊ ሁኔታ ተጨፍጭፈው ተገድለዋል። ጭፍጨፋውን ያዩ፣ የጭፍጨፋው ሰለባ የነበሩ፣ ወገኖቻቸውን ያጡ፣ … ኢትዮጵያውያን በዚህ ቪዲዮ የምስክርነት ቃላቸውን ይሰጣሉ። (ከአዘጋጁ፦ ይህን ቪዲዮ ሕፃናት አይመልከቱት)
የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





ይህ አጭር ፊልም “Democracy is fair play” በሚል ርዕስ በያሬድ ሹመቴ የተዘጋጀ ነው። ዲሞክራሲን አስመልክቶ በዓለም በሚደረገው የአጭር ፊልሞች ውድድር ላይ ፊልሙ ቀርቦ ከፍተኛ ድምፅ ካገኙት 18 ፊልሞች ውስጥ አንዱ ለመሆን በቅቷል። ከ18ቱ ፊልሞች አሸናፊውን ለመለየት በዩቲዩብ እርስዎም ድምፅዎን መስጠት ይችላሉ። የሚከተለውን አስፈንጣሪ በመንካት (http://www.youtube.com/democracychallenge) ቀጥታ ወደ ድምፅ መስጫው መሄድ ይችላሉ። ከዚያም “VOTE” የሚለውን ይጫናሉ፣ በቀኝ በኩል ከሚመጡት ዘጠኝ ፊልሞች ውስጥ ኢትዮጵያውያን ህፃናት ያሉበትን ካላገኙት፣ በቀኝ በኩል ያለውን ቀስት ሲነኩት ቀሪዎቹን ዘጠኝ ፊልሞች ያገኛሉ። ፊልሙን ሲያገኙ አንድ ጊዜ ይጫኑት፣ ከዚያም ከፊልሙ በታች ያለውን አረንጓዴ እጅ በመጫን ድምፅዎትን ይስጡ! … በዚህ ድምፅ አሰጣጥ ድምፅዎ በትክክል ለመረጡት ይደርሳል። ድምፄ ይሰረቃል ብለው አይስጉ! የኢትዮጵያው ምርጫ ቦርድ እዚህ እጁ አይደርስም። ወደ ድምፅ መስጫ ጣቢያው ውሰደኝ!





”በእውነት ኢትዮጵያውያን ለመብታችሁና ለሀገራችሁ ምን እየሠራችሁ ነው?” በማለት ዳያስፖራውን የሚጠይቀው አሜሪካዊው የፊልም ፀሐፊ፣ ፕሮዲዩሰር እና ዳይሬክተር ክሪስ ፍላህሪቲ ነው። ክሪስ ”ማይግሬሽን ኦፍ ቢዩቲ” (Migration of Beauty) የተሰኘ ጥናታዊ ፊልም ዳይሬክተር መሆኑ ይታወቃል። ”... እኔ በግሌ የማደርገውን አውቃለሁ፤ እናንተስ? ... በዋሽንግተን ዲሲ ኋይት ሐውስ በማደርገው የረሃብ አድማ ስንቶቻችሁ ናችሁ ልትሳተፉ የምትችሉት? ...” በማለት በተለይም በስደት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለትውልድ ሀገራቸውና ለመብታቸው ምን ያህል እየታገሉ ስለመሆኑ ወሳኝ ጥያቄዎች ይጠይቃሉ። ... ቪዲዮውን ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!
የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5





በዕለቱ ጠ/ሚንስትሩ ፀያፍ ቃላትን ከመጠቀማቸው በተጨማሪ፤ የተቃዋሚ ፓርቲዎች የፓርላማ ተወካዮች ጠ/ሚንስትሩ በጥያቄ አፈጥጠዋቸዋል። ጠ/ሚ መለስ ፀያፍ ቃላትን እንዳሻቸው ሲጠቀሙ፤ ሥርዓት ባለው መንገድ የሚናገሩትን ተቃዋሚዎች ግን አፈጉባዔው እንዳይናገሩ ሲያግዷቸው ይህ ቪዲዮ ያሳያል። ለአንባብያን ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ የ6 ደቂቃ ከ26 ሰከንዱን ቪዲዮ ይመለከቱ ዘንድ እንጋብዛለን።