ሲዳማ 10ኛዋ ክልል

ሻፌታን 98.51 በመቶ ሕዝብ ሲመርጥ፣ 1.48 በመቶው ደግሞ ጎጆ ቤትን መርጧል

98.5 በመቶ መራጭ ክልል እንሁን በማለት መርጧል

ኢዛ (ቅዳሜ ኅዳር ፲፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 23, 2019)፦ የሲዳማ የክልልነትን ጥያቄ በተመለከተ ኅዳር 10 ቀን በተደረገው ሕዝበ ውሣኔ ከ98 በመቶ በላይ የሚኾነው መራጭ የሲዳማ ዞን ክልል ይሁን የሚለውን ድምፅ መሥጠቱ ይፋ ኾነ። ይህም ሲዳማን 10ኛዋ የአገሪቱ ክልል ለመኾን የሚያስችላትን እድል መገኘቱን የሚያረጋግጥ ኾኗል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሲዳማ ሕዝበ ውሣኔ ውጤት ዛሬ ይፋ ይደረጋል

የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ

ሕዝበ ውሣኔው በሰላም ተጠናቅቋል

ኢዛ (ቅዳሜ ኅዳር ፲፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 23, 2019)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ ላይ ኅዳር 10 የተካሔደውን ሕዝበ ውሣኔ ውጤት ዛሬ ኅዳር 13 ቀን 2012 ዓ.ም. ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የግል ባንኮችን ሲደቁስ ነበር የተባለው መመሪያ ተሻረ

National bank of Ethiopia

መመሪውያው የግል ባንኮችን በእጅጉ ጎድቷል ተብሎ በተደጋጋሚ አቤቱታ ሲቀርብበት ነበር

ኢዛ (ዓርብ ኅዳር ፲፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 22, 2019)፦ የግል ባንኮችን በእጅጉ ጎድቷል ተብሎ በተደጋጋሚ አቤቱታ ሲቀርብበት የነበረው አስገዳጅ የ27 በመቶ ቦንድ ግዥ መመሪያ ተሻረ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢሕአዴግ የሚለው መጠሪያ የከሰመበት ውሳኔ

ከኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢሕአዴግ/ ምክር ቤት የተሠጠ መግለጫ

መግለጫው የአዲሱን ፓርቲ የወደፊት አቅጣጫ ያመለከተ ነው

ኢዛ (ዓሙስ ኅዳር ፲፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 22, 2019)፦ የኢሕአዴግ ምክር ቤት አዲሱን ውሕድ ፓርቲ ሕገደንብ በማጽደቅ ሲያካሒድ የነበረውን ስብሰባ በማጠናቀቅ አዲሱ ፓርቲ የወደፊት አቅጣጫን ያመለከተ መግለጫ አውጥቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሲጠበቅ የነበረው የኢሕአዴግ ውሕደት በምክር ቤቱ ጸደቀ

የኢሕአዴግ ምክር ቤት

የጸደቀው በሙሉ ድምፅ ነው

ኢዛ (ሐሙስ ኅዳር ፲፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 21, 2019)፦ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ምክር ቤት የፓርቲውን ውሕደት አጸደቀ። የሕወሓት ተውካዮች ያልተሳተፉበት እንደኾነ የተነገረለት የዛሬው የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ፤ የፓርቲውን ውሕደት ያጸደቀው በሙሉ ድምፅ እንደኾነ ተገልጿል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሕወሓት የብልጽግና ፓርቲን ጉዳይ ያጸናል በተባለው በዛሬው ስብሰባ ላይ አይገኝም

ሕወሓትና ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በዛሬው ስብሰባ እንደማይገኙ በደብዳቤ ገለጹ

ኢዛ (ሐሙስ ኅዳር ፲፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 21, 2019)፦ የኢሕአዴግ ምክር ቤት ዛሬ ኅዳር 11 ቀን 2012 ዓ.ም. በሚያካሒደው ስብሰባ ላይ የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እንደማይሳተፉ የሕወሓት ጽሕፈት ቤት ትናንት ማምሻውን አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ2012 ዓ.ም. 10ኛ ሳምንት አንኳር ወሬዎች

ከኅዳር 1 - 7 ቀን 2012 ዓ.ም. የሳምንቱን አንኳር ወሬዎች በጨረፍታ

በዩኒቨርሲቲዎች የፈጠረው ግጭትና የዶ/ር ዐቢይ ማስጠንቀቂያ

ኢዛ (ከኅዳር 1 - 7 ቀን 2012 ዓ.ም.)፦ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የሁለት ተማሪዎች ሞት ከተሰማ በኋላ በተለያዩ የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ያለመረጋጋት ተፈጥሮ ሰንብቷል። በደንቢ ዶሎም የአንድ ተማሪ ሞት መሰማቱ በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የፈጠረው ውጥረት የሳምንቱ መሪ ዜና ነበር። በጅማና በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲዎች የተፈጠረው ሥጋት ጥቂት የማይባሉ ተማሪዎች ዶርማቸውን (ዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሚገኝ ማደሪያቸውን) ለቀው በቤተ እምነቶች እንዲጠለሉ አስገድዷቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሲዳማ ጉዳይ ነገ ይለያል

የምርጫው ምልክቶች

ለምርጫው 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን መራጮች ተመዝግበዋል

ኢዛ (ማክሰኞ ኅዳር ፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 19, 2019)፦ ለዓመታት የቆየውን የሲዳማ የክልልነት ጥያቄን እልባት ለመሥጠትና ሲዳማ በክልልነት ይደራጅ፣ ወይም ሲዳማ የደቡብ ክልል ኾኖ እንዲቆይ እፈልጋለሁ የሚለውን ለመለየት ሲጠበቅ የነበረው ምርጫ ነገ ይካሔዳል። ለምርጫው 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን መራጮች ተመዝግበዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቀድሞው የቤንሻንጉል ክልል ፕሬዝዳንት አረፉ

The first president of Benishangul and Gumuz, Yaregal Ayesheshum

አቶ ያረጋል አይሸሹም ያረፉት በድንገተኛ ሕመም ነው

ኢዛ (ማክሰኞ ኅዳር ፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 19, 2019)፦ የመጀመሪያው የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ፕሬዝዳንት (ርዕሰ መስተዳድር) አቶ ያረጋል አይሸሹም ትናንት ኅዳር 8 ቀን 2012 ዓ.ም. አረፉ። አቶ ያረጋል በድንገተኛ ሕመም ማረፋቸው ዛሬ ተሰምቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ያልተገመተው ውጤት

Ethiopia vs Cote d ivoire

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ኮትዲቯርን 2ለ1 አሸነፈ

ኢዛ (ማክሰኞ ኅዳር ፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 19, 2019)፦ በተደጋጋሚ ሽንፈት ሲወቀስ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በአፍሪካ ኃያል ከሚባሉ ቡድኖች አንዱ የኾነውን የኮትዲቯርን ቡድን ሁለት ለአንድ ረታ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ