አምባሳደር አሐዱ ሳቡሬ አረፉ

Ambassador Ahadu Sabure

“አሐዱ ሳቡሬ፣ አጠገበኝ ወሬ” በመባል ይጠሩ ነበር

ኢዛ (ሰኞ ኅዳር ፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 18, 2019)፦ አንጋፋው ጋዜጠኛና ዲፕሎማት አምባሳደር አሐዱ ሳቡሬ በአሜሪካን አገር በሎስ አንጀለስ ከተማ በተወለዱ በዘጠና አራት ዓመታቸው ሐሙስ ኅዳር 4 ሌሊት ለዓርብ አጥቢያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአዲስ አበባ ሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን ሲያትሙ የነበሩ ስምንት የውጭ ዜጎች ተያዙ

በቁጥጥር ሥር የዋሉት ኖቶች፣ መሣሪያዎችና ኬሚካሎች

ያትሙባቸው የነበሩ መሣሪያዎቻቸውም በቁጥጥር ሥር ውለዋል

ኢዛ (ቅዳሜ ኅዳር ፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 16, 2019)፦ በአዲስ አበባ ከተማ የግለሰብ መኖሪያ ቤቶችን ተከራይተው ሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን ሲያትሙ የነበሩ ስምንት የውጭ ዜቶችን ሕገወጥ ገንዘብ ያትሙባቸው ከነበሩ መሣሪያዎቻቸው ጋር በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

47.7 ኪሎ ግራም ኮኬይን ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ተያዘ

Cocaine at bole airport

ከ109 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ አለው

ኢዛ (ቅዳሜ ኅዳር ፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 16, 2019)፦ ከሁለት ሳምንት በፊት የስናይፐር መለዋወጫዎች የተያዙበት የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ዛሬ ደግሞ 47.7 ኪሎ ግራም ኮኬይን አደገኛ አደንዛዥ እፅ ተያዘ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለኦነግና ለኦብነግ የእውቅና የምስክር ወረቀት ተሠጠ

የምስክር ወረቀት

ኦነግ ለምርጫ ቦርድ ምስጋና አቀረበ

ኢዛ (ዓርብ ኅዳር ፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 15, 2019)፦ ለኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና ለኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ፓርቲዎች የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የእውቅና የምስክር ወረቀት እንደሠጣቸው አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ስብሰባ ነገ ይካሔዳል

EPRDF

በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል

ኢዛ (ዓርብ ኅዳር ፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 15, 2019)፦ የተለያዩ ውሣኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ የሚጠበቀው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ነገ ኅዳር 6 ቀን 2012 ዓ.ም. እንደሚሰበሰብ ታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢሕአዴግናን አጋር ድርጅቶቹን ውሑድ ፓርቲ ለማድረግ ዝግጅቱ ተጥናቅቋል

አቶ መለስ ዓለም

ከሕወሓት በስተቀር የኢሕአዴግ ፓርቲዎችና አጋሮቹ ውሕደቱን ደግፈዋል

ኢዛ (ሐሙስ ኅዳር ፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 14, 2019)፦ የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶችንና አጋር በሚል ይታወቁ የነበሩ ፓርቲዎችን በማዋሐድ አንድ ሕብረብሔራዊ ፓርቲ ለማድረግ ሲካሔድ የቆየው ዝግጅት መጠናቀቁ ታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሰኔ 15ቱን ግድያን አጣርቼ ጨረስኩ አለ

Berhanu Tsegaye

በ78 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ሊመሠረት ነው

ኢዛ (ሐሙስ ኅዳር ፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 14, 2019)፦ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በአዲስ አበባና በባህርዳር ከተሞች በከፍተኛ መኮንኖችና የመንግሥት ባለሥልጣናት ላይ የተፈጸመው ግድያ በብርጋዲየር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ የተቀነባበረ መኾኑን የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ይፋ አደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ2012፣ 9ኛ ሳምንት አንኳር ወሬዎች

EZ Weekly digest, 9th 2012 Eth. C

የዓመቱ ዘጠነኛ ሳምንት አንኳር ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ክንውኖች

ኢዛ (ከጥቅምት 24 - 30 ቀን 2012 ዓ.ም.)፦ እንደ ወትሮው ባሳለፍነው ሳምንት የተለያዩ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ክንውኖች ተካሒደዋል። በቀደመው ሳምንት መጨረሻ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ ጉዳዮች መግለጫ የሰጡበት ስለነበር፤ ባሳለፍነው ሣምንትም ይህንን መግለጫ ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰነዘሩበት ነበር። ብዙዎች አሁንም “ሕግ ይከበር!” የሚለውን ጠንከር ያለ አቋም እየገለጹ ይገኛሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሁለት ተማሪዎች ሞቱ

Woldia University

10 ቀላልና ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል

ኢዛ (ሰኞ ኅዳር ፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 11, 2019)፦ እስካሁን መንሥኤው አልታወቀም በተባለ ግጭት ሁለት የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሞታቸውንና አሥር ተማሪዎች ደግሞ ቀላልና ከፍተኛ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገለፀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የመከላከያ ሠራዊት መተዳደሪያ ረቂቅ ደንብ አፀደቀ

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

የተሻሻለው የመከላከያ ሠራዊት ደንብ ቁጥር 385/2008ን ነው

ኢዛ (ሰኞ ኅዳር ፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 11, 2019)፦ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የመከላከያ ሠራዊት መተዳደሪያ ረቂቅ ድንብና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሣኔ ማሳለፉ ተገለፀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ