የ2012 ዓ.ም. 26ኛ ሳምንት አንኳር ወሬዎች

Ethiopia Zare's weekly news digest, week 26th, 2012 Ethiopian calendar

የዓመቱ ሃያ ስድስተኛ ሳምንት አንኳር ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ክንውኖች

ኢዛ (ከየካቲት 23 - 29 ቀን 2012 ዓ.ም.)፦ ባሳለፍነው ሳምንት ዐበይት ጉዳዮች መካከል በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያና ግብጽ የገቡበት የቃላት ጦርነትን የሚስተካከል የለም። ሳምንቱን ሙሉ በዚህ ጉዳይ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ቀዳሚውን ሥፍራ የያዙ ናቸው። የአገር ውስጥ ሚዲያዎች የመክፈቻ ዜናዎቻቸው በዚሁ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያነጣጠረ ነው። የህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ ከተጣለና ግንባታው ተጀምሮ አሁን ያለበት ደረጃ እስኪደርስ ድረስ ውስጥ ውስጡን ካልኾነ በቀር በግብጽና በኢትዮጵያ መካከል ጠንከር ያለ የቃላት ምልልስ የተደረገበት ጊዜ አልነበረም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከቱርክ ወደ ኢትዮጵያ በረቀቀ መንገድ የገባ ሁለት ኮንቴይነር የጦር መሣሪያ ተያዘ

Ethiopian National Intelligence and Security Service (NISS)

የዓለም አቀፍ የጦር መሣሪያ አዘዋዋሪዎች እጅ አለበት

ኢዛ (ማክሰኞ መጋቢት ፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 10, 2020)፦ ከሕገወጥ የመሣሪያ ዝውውር ጋር ተያይዞ እስካሁን በይፋ ከተገለጹት መረጃዎች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የጦር መሣሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአማራ ባንክ አክስዮኖችን የገዙ 145 ሺህ መድረሱ ተገለጸ

Bank of Amhara

የተፈረመ ካፒታሉ 5.3 ቢሊዮን ሲሆን፣ የተከፈለ ካፒታሉ 4 ቢሊዮን ደርሷል፤ የአክስዮን ሽያጩን ለአምስት ሳምንት አራዝሟል

ኢዛ (ሰኞ የካቲት ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 9, 2020)፦ አማራ ባንክ አክስዮን ማኅበር ባላፉት ስምንት ወሮች አክስዮን የገዙ ግለሰቦችና ኩባንያዎች ቁጥር 145 ሺህ መድረሱንና ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ የተከፈል ካፒታል ማሰባሰቡን ገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ የተቃጣውን የግድያ ሙከራ አድራሾች አልታወቁም

በሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ላይ የግድያ ሙከራው የተቃጣበት ስፍራ

ዶ/ር ዐቢይ የግድያ ሙከራውን አውግዘዋል

ኢዛ (ሰኞ የካቲት ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 9, 2020)፦ ዛሬ ጠዋት ወደ ቢሯቸው ሲያቀኑ እስካሁን ማንነታቸው ባልታወቀ ጥቃት አድራሾች የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ደኅንነቱ በተጠበቀ ስፍራ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዶ/ር ዐቢይ ከከፍተኛ የአገር መከላከያ አመራሮች ጋር መከሩ

PM Abiy Ahmed

“የሠራዊታችን አመራሮችና አባላት ያላቸው ሁሉ ለአገራቸው ለመሥጠት ፍጹም ቆራጦች ናቸው” ዶ/ር ዐቢይ

ኢዛ (ሰኞ የካቲት ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 9, 2020)፦ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከአገር መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር አደረጉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ነፃነት አስፋው አረፉ

Netsanet Asfaw

ከሕወሓት ነባር ታጋዮች አንዷ ነበሩ

ኢዛ (ሰኞ የካቲት ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 9, 2020)፦ ከሕወሓት ነባር ታጋዮች መካከል አንዷ የነበሩትና በተለያዩ መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነት ላይ የነበሩት ወይዘሮ ነፃነት አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሁለት ኢትዮጵያውያን በኮሮና ቫይረስ በአቡዳቢ ተያዙ

ኮሮና ቫይረስን በምስል ለማሳየት በበሽታ ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል የተሠራጨ

በአገሪቱ እስካሁን 45 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል

ኢዛ (ቅዳሜ የካቲት ፳፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 7, 2020)፦ የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የጤና ሚኒስቴር ዛሬ እንዳስታወቀው 15 አዲስ ግለሰቦች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል። ከእነዚህም ውስጥ ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል። በአገሪቱ እስካሁን 45 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቅንጅት መሥራች አባላት ፊርማ በፖሊስ ሊመረመር ነው

Ayele Chamiso

ምርጫ ቦርድ ለናሙና ከመረመረው 50 ፊርማዎች 49ኙ ያልፈረሙ ናቸው ብሏል

ኢዛ (ቅዳሜ የካቲት ፳፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 7, 2020)፦ በአቶ አየለ ጫሚሶ የሚመራው ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (ቅንጅት) ለምርጫ ቦርድ ካቀረበው የመሥራች አባላት ፊርማ ዝርዝር ጋር በተያያዘ ያልፈረሙ እንደፈረሙ ተደርጎ በመቅረቡ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰነዱን የፌዴራል ፖሊስ እንዲያጣራለት መላኩን አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኮሮና ቫይረስ ምልክት ያሳዩ ሁለት ሰዎች በለይቶ ማቆያ ገብተዋል

Ethiopian Arilines

በአራት ቀን ውስጥ 382 መንገደኞች ቫይረሱ ሪፖርት ከተደረገባቸው አገራት ኢትዮጵያ ገብተዋል

ኢዛ (ዓርብ የካቲት ፳፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 6, 2020)፦ የኮሮና ቫይረስ ተመሳሳይ ምልክት የታየባቸው ሁለት ሰዎች በለይቶ ማቆያ እንዲገቡ መደረጉ ተገለጸ። በአራት ቀን ውስጥ 382 መንገደኞች ቫይረሱ ሪፖርት ከተደረገባቸው አገራት ኢትዮጵያ መግባታቸው ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ባልደራስና መኢአድ በቅንጅት ለመሥራት ተፈራረሙ

አቶ እስክንድር ነጋና አቶ ማሙሸት አማረ

ለጥምረታቸው “ባልደራስ መኢአድ” የሚል ሥያሜ ሠጥተዋል

ኢዛ (ዓርብ የካቲት ፳፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 6, 2020)፦ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ (ባልደራስ) እና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በቅንጅት ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት በማድረግ፤ በጋራ የሚታገሉበትን የፓርቲ ስያሜም “ባልደራስ መኢአድ” ፓርቲ እንዲኾን በመወሰን ተፈራረሙ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ