በኢትዮጵያ በ27ኛው ቀን የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር 55 ደርሷል

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ (መጋቢት 30 ቀን 2012 ዓ.ም.፤ በጤና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተዘጋጀ)

በአማካኝ በቀን ሁለት በቫይረሱ የተያዘ ሰው ሪፖርት እየተደረገ ነው

ኢዛ (ረቡዕ መጋቢት ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 8, 2020)፦ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ሰው ሪፖርት ከተደረገበት ከመጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ባላፉት 27 ቀናት በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 55 ደርሷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአገሪቱ ትልቁ ባንክ ከነገ ጀምሮ ለሦስት ቀናት ይዘጋል

Commercial Bank of Ethiopia

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መደበኛ ሥራውን የሚጀምረው የፊታችን ሰኞ ነው

ኢዛ (ረቡዕ መጋቢት ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 8, 2020)፦ የአገሪቱ ትልቁ ባንክ የኾነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከነገ ሚያዝያ 1 ቀን ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀኖች አገልግሎት እንደማይሠጥ አስታውቋል። ባንኩ መደበኛ ሥራውን የሚጀምረው ሰኞ ሚያዝያ 5 ቀን 2012 ዓ.ም. ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መንግሥት አወጀ

PM Abiy Ahmed

መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝን በተመለከተ የሚከተለው ስትራቴጂ በመከላከል ላይ ያተኮረ መኾኑን ገለጸ

ኢዛ (ረቡዕ መጋቢት ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 8, 2020)፦ በዛሬው ዕለት (ረቡዕ መጋቢት 30 ቀን 2012 ዓ.ም.) በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን አስታውቀዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሦስት የበረራ ሠራተኞች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል

Mr. Tewolde GebreMariam was appointed as Group Chief Executive Officer of Ethiopian Airlines

አየር መንገዱ በአራት ወር 550 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አጥቷል፤ የሚቀነስ ሠራተኛ የለም ብሏል

ኢዛ (ማክሰኞ መጋቢት ፳፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 7, 2020)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሦስት ሠራተኞች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዘጠኝ ወር ሕፃን በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ተጠቃ

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ (መጋቢት 29 ቀን 2012 ዓ.ም.፤ በጤና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተዘጋጀ)

በቫይረሱ የተያዙ 52 ደርሰዋል

ኢዛ (ማክሰኞ መጋቢት ፳፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 7, 2020)፦ በኢትዮጵያ የዘጠኝ ወር ዕድሜ ያለው ሕፃንን ጨምሮ ስምንት አዳዲስ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች መገኘታቸውንና በኢትዮጵያ አጠቃላይ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 52 መድረሱ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ2012 ዓ.ም. 30ኛ ሳምንት አንኳር ወሬዎች

Ethiopia Zare's weekly news digest, week 30th, 2012 Ethiopian calendar

የዓመቱ ሠላሳኛ ሳምንት አንኳር ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ክንውኖች

ኢዛ (ከመጋቢት 21 - 27 ቀን 2012 ዓ.ም.)፦ ያሳለፍነው ሳምንትም ቀዳሚ መነጋገሪያ ሆኖ የቀለው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝና ከዚሁ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ናቸው። በኢትዮጵያ አንፃር ሰሞናዊውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሚመለከቱ መረጃዎች በተለየ የሚታየው ከቀዳሚዎቹ ሦስት ሳምንት የበለጠ ቁጥር ያላቸው ተጠቂዎች መገኘታቸው ሪፖርት መደረጉ ነው። ከዚህም ሌላ የመጀመሪያዎቹ ሁለት በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ሕይወት ማለፉም የተነገረው ባሳለፍነው ሳምንት የመጨረሻ ቀን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከሐረሪ ማረሚያ ቤት እስረኞች ለማምለጥ ያደረጉት ሙከራ መክሸፉ ተነገረ

ሐረር ከተማ

በእስረኞች ማደሪያ 180 ሞባይሎች ተይዘዋል

ኢዛ (እሁድ መጋቢት ፳፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 5, 2020)፦ በሐረሪ ክልል ማረሚያ ቤት ዛሬ መጋቢት 27 ቀን ጠዋት ላይ የሕግ ታራሚዎች የማረሚያ ቤቱን በራፍ በመገንጣጠል ለመውጣት ያደረጉት ሙከራ መክሸፉን የማረሚያ ቤቱ ኮሚሽነር ገልጸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የመጀመሪያው ሞት ተመዘገበ

የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር

የ60 ዓመት ሴት ናቸው ያረፉት

ኢዛ (እሁድ መጋቢት ፳፯ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 5, 2020)፦ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ዛሬ አዲስ ተጨማሪ በቫይረሱ የተጠቁ አምስት ሰዎች መገኘታቸውን ካስታወቀ በኋላ፤ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ይፋ ባደረገው መግለጫ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ የ60 ዓመት ታማሚ ሕይወታቸው አልፏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሁለት ረቂቅ አዋጆች ላይ ውሳኔ አሳለፈ

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

ስብሰባው የተካሔደው በቪዲዮ ኮንፈረንስ ነው

ኢዛ (ቅዳሜ መጋቢት ፳፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 4, 2020)፦ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ መጋቢት 26 ቀን ባካሔደው 81ኛ መደበኛ ስብሰባው በኤሌክትሮኒክ ትራንዛክሽን ረቂቅ አዋጅና የኤካ ኮተቤ ሆስፒታልን ለማቁቋም በቀረበው ረቂቅ ላይ ውሳኔ አሳልፏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ