የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማስፈፀሚያ ድንብ ይፋ ኾነ

Attorney General Adanech Abebe

ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ስብሰባዎች ተከልክለዋል፤ ቤት ኪራይ መጨመር፣ ሠራተኛ መቀነስና ውል ማቋረጥም አይቻልም

ኢዛ (ቅዳሜ ሚያዝያ ፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 11, 2020)፦ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ወረርሽኝ ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ያስችል ዘንድ ትናንት በፓርላማ የጸደቀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማስፈፀም አራት ዋና ዋና ክፍሎች ያሉት ደንብ ይፋ ኾነ። የደንቡን አጠቃላይ ይዘት ማብራሪያ በመሥጠት ይፋ ያደረጉት የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በጽኑ ሕመም ላይ የነበሩት ወይዘሮ አረፉ

Ministry of Health, Ethiopia

በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ሦስት ደርሰዋል

ኢዛ (ዓርብ ሚያዝያ ፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 10, 2020)፦ የዱከም ከተማ ነዋሪ የነበሩትና በቅርቡ የኮሮና ቫይረስ እንደተኘባቸው ከታወቀበት ቀን ጀምሮ በጽኑ ሕክምና ላይ የነበሩት ታማሚ፤ ዛሬ ዓርብ ሚያዝያ 2 ቀን 2012 ዓ.ም. ሕይወታቸው ማለፉ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የብልጽግና ፓርቲ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ አወጣ

Prosperity Party

“የገጠመን ጦርነት የሞት ሽረት ነው”

ኢዛ (ዓርብ ሚያዝያ ፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 10, 2020)፦ የኮሮና ቫይረስ እንደ አገር የሰነቅናቸውን ሕልሞች ሊነጥቀን የመጣ ጠላት በመኾኑ፤ የምናደርገው ጦርነት በሁሉም መስክ የሞት ሽረት ትግል እንደሚኾን የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በ24 ሰዓት ምርመራ ዘጠኝ የቫይረሱ ተጠቂዎች ተገኙ

Ministry of Health, Ethiopia

በአንድ ቀን ከፍተኛ ተጠቂ መገኘቱ ሪፖርት የተደረገበት ቀን ኾኗል

ኢዛ (ዓርብ ሚያዝያ ፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 10, 2020)፦ በኢትዮጵያ በ24 ሰዓት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የቫይረሱ ተጠቂ የተገኘበትና በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 65 መድረሱ ተመለከተ። የጤና ሚኒስቴር ይፋ እንዳደረገው በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ በተደረገ ምርመራ አዲስ ዘጠኝ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ተገኝተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ነገ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

አዋጁ የሚጸድቀው ከፓርላማው ሕንፃ ውጭ ነው

ኢዛ (ሐሙስ ሚያዝያ ፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 9, 2020)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፓርላማው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውጭ በሚደረግ ልዩ ስብሰባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ነገ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የትግራይ ክልል ለ15 ቀን ያለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወደ ሦስት ወር አራዘመ

Dr. Debretsion Gebremichael

ከመጋቢት 17 ቀን ጀምሮ ታሳቢ ተደርጎ የሚቀጥል ነው

ኢዛ (ሐሙስ ሚያዝያ ፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 9, 2020)፦ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለ15 ቀን ተግባራዊ የሚደረግ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጥቶ የነበረው የትግራይ ክልል ምክር ቤት፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለሦስት ወራት እንዲራዘም ወሰነ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኮሮና ቫይረስ የሞተ ሰው አስክሬን ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ተከለከለ

Ethiopian Public Health Institute

ኢዛ (ሐሙስ ሚያዝያ ፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 9, 2020)፦ በኮሮና ቫይረስ የሞተ ሰው አስክሬኑ ከውጭ አገር ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓጓዝ ወይም እንዳይገባ ይደረግ ዘንድ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ማብራሪያ ሠጠ

Federal Attorney General

• የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለአምስት ወር ይቆያል
• በአዋጁ ተፈፃሚ የሚኾኑ ገደቦች ገና የሚወሰኑ ናቸው
• አዋጁን ለሚጥሱ የቅጣት መጠን ተቀምጧል

ኢዛ (ረቡዕ መጋቢት ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 8, 2020)፦ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ሲባል ዛሬ መጋቢት 30 ቀን የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ማብራሪያ የሠጠ ሲሆንል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም ለአምስት ወር የሚፀና መኾኑን አስታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሕግ በተላለፉ ከ25 ሺህ በላይ የሚኾኑ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ

 Ethiopia Ministry of Trade and Industry

ሰዎች የሚሰበሰቡባቸው የንግድ ድርጅቶች በሽታው በቁጥጥር ስር እስኪውል ድረስ ተዘግተው ይቆያሉ

ኢዛ (ረቡዕ መጋቢት ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. April 8, 2020)፦ ከኮሮና ቫይረስ መከሰት ጋር ተያይዞ ፍትሐዊ ግብይት ለማስፈንና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪን ለመቆጣጠር የተቋቋመው ብሔራዊ የገበያ ማረጋጋት ግብረኃይል ከ25 ሺህ በላይ ሕግ የተላለፉ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ እንደወሰደ ገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ