በካናዳዋ የንግድ መናገሻ ቶሮንቶ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠራ

የሕግ ባለሙያው ዶ/ር ሸክስፒር ፈይሳ ንግግር ያደርጋል

አሁንም የኢትዮጵያዊያኖች የድረሱልኝ ጥሪ እየተሰማ ነው

Ethiopia Zare (ሐሙስ ኅዳር 5 ቀን 2006 ዓ.ም. November 14, 2013)፦ በካናዳ የንግድ መናገሻ በሆነችው ቶሮንቶ ከተማ በሳኡዲት አረቢያ በኢትዮጵያዊያኖች ላይ የሚፈጸመውን ግፍ በመቃወምና በአሰቃቂ ሁናቴ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የሻማ ማብራት ስነስርአት ነገ አርብ እንደሚካሄድ ይፋ ተደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያን መንግሥት ፍርድ ቤት ለማቅረብ እንቅስቃሴ ተጀመረ

ጠበቃ ስቴላ ያርዴእንቅስቃሴውን የጀመሩት ስዊድናዊ ጠበቃ ከኢትዮጵያውና ጋር ውይይት አደረጉ
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ኅዳር 3 ቀን 2006 ዓ.ም. Nov. 12, 2013)፦ ባለፈው ቅዳሜ ጥቅምት 23 ቀን 2006 ዓ.ም. (ኖቬምበር 2 ቀን 2013) የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ መድረክ በስዊድን የወያኔን መንግሥት በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለማቅረብ የተጀመረውን ክስ መነሻ በማድረግ የክሱን ሂደት ከሚመሩት ከስዊድናዊው ጠበቃ ከስቴላ ያርዴ እና ከሌሎች እንግዶች ጋር በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ወይይት አደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል መልእክት ለባለቤቷና ለህሊና እስረኞች

Ethiopia Zare (አርብ ጥቅምት 23 ቀን 2006 ዓ.ም November 1, 2013):- ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል በእስር ላይ የሚገኘውን የብእር ሰው፣ ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ ባለቤቷን እስክንድር ነጋን ተለይታ ከምትኖርበት ዋሽንግተን ዲሲ የሀገሯን የመጨረሻ ስንብት በሚመለከት ለህሊና እስረኞች ለሆኑት ታሳሪዎች ያስተላለፈችው መልእክት ይፋ ተደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሲያትል የሃና ገዳዮች 37 እና 29 አመት ፍርድ ተወሰነባቸው

"ኢትዮጵያዊያን በፍርዱ ረክተዋል" ወ/ሮ ሙሉመቤት ረታ (በሲያትል የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር)

"በእኔ አስተያየት ፍትህ ተበይኗል፤ ዳኛዋም ሆኑ ፍርድ ሰጭዎቹ (ጁሪዎቹ) በትክክል ጉዳዩን አይተው ወስነዋል ብየ አምናለሁ" ዶ/ር ሸክስፒር ፈይሳ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥቅምት 20 ቀን 2006 ዓ.ም. October 30, 2013)፦ ከሁለት ዓመት በፊት ሃና ዊሊያምስ የተባለችውን ታዳጊ በቅዝቃዜ ደጅ ላይ በማዋልና በማሳደር አሰቃይተው ገድለዋል የተባሉት አሳዳጊዎቿ ኬሪ ዊሊያምስና ባለቤቷ ላሪ ዊሊያምስ የ37 ዓመትና የ29 አመት ጽኑ እስራት የተወሰነባቸው ሲሆን በሲያትል አካባቢ የሚኖሩ ትዮጵያዊያን በፍርዱ መደሰታቸውን በተለይ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሰሜን ዕዝና የአየር ኃይል ዋና አዛዦች በሌሎች ተተኩ

የፓርላማው አባል የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕግ አማካሪ ሆኑ

በዮሐንስ አንበርብር

(ሪፖርተር ረቡዕ ጥቅምት 20 ቀን 2006 ዓ.ም. Oct. 30, 2013)፦ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አቅራቢነትና በፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ አማካይነት የጄኔራል መኮንኖች ሹመት ከተካሄደ በኋላ፣ በመከላከያ ሠራዊቱ አመራሮች ላይ የኃላፊነት ሽግሽግ ተካሄደ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ በረከት ስምኦን የኢቲቪ ቦርድ ሰብሳቢነቱን ለአቶ ሬድዋን ሁሴን አስረከቡ

አቶ በረከት ስምኦን Bereket Simonየሹመቱ አግባብነት ጥያቄ አስነስቷል
አፈጉባዔ አባዱላ ጠ/ሚኒስትሩ በሹመቱ ላይ ማብራሪያ ለመስጠት አይገደዱም አሉ

በፍሬው አበበ
(ሰንደቅ ጋዜጣ ረቡዕ ጥቅምት 20 ቀን 2006 ዓ.ም. Oct. 30, 2013)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ለኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ ኃላፊነት ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ ያቀረቡትን ሹመት ተቀብሎ አጸደቀ። በዚሁ መሠረት ድርጅቱን ለረዥም ጊዜ በቦርድ ኃላፊነት ባገለገሉት በአቶ በረከት ስምኦን ምትክ አቶ ሬድዋን ሁሴን የድርጅቱ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሹመዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በስዊድን የመድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን የበጎ ሥራ ምስጋና ሽልማት ሰጠች

ብፁዕ አቡነ ኤልያስ Abune EliasEthiopia Zare (ሰኞ ጥቅምት 18 ቀን 2006 ዓ.ም. Oct. 28, 2013)፦ ትናንት እሁድ ኦክቶበር 27 ቀን 2013 (ጥቅምት 17፣ 2006 ዓ.ም.) በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም የምትገኘው የመድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ለቀድሞ የቤተክርስቲያኑ የሰበካ ጉባዔ አባላት የበጎ ሥራ የምስጋና ሽልማትና የምስክር ወረቀት ሰጠች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአውራምባ ታይምሱ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባል

ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ Journalist Dawit Kebede(ቪዲዮ አለው)

"እጅግ አስደንጋጭ ዜና ነው" ሀገር ቤት ያሉ ጋዜጠኞች

Ethiopia Zare (ዓርብ ጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ.ም. Oct. 25, 2013)፦ በሀገር ቤት ይታተም የነበረው "አውራምባ ታይምስ" ጋዜጣ እና የድረ ገጹ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ከሁለት ዓመት በሰሜን አሜሪካ የስደት ቆይታ በኋላ በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚበር ገለጸ። በጉዳዩ ላይ ከአቶ ያሬድ ጥበቡ ጋር በቪዲዮ ቃለምልልስ አድረጓል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ በአሜሪካ ለሚገኙትን አቶ ስብኀት ነጋን በጥያቄ አፋጠጠ

በግል ስልኩ የተቀረጸ የቪድዮ ምስል ይመልከቱ!

Ethiopia Zare (አርብ ጥቅምት 1 ቀን 2006 ዓ.ም. October 11, 2013)፦ የሙስሊም ራዲዮ ጋዜጠኛ እና በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጥያቄዎች ላይ ትንተናዎችን በመስጠት የሚታወቀው ሳዲቅ አህመድ በአሜሪካን ሀገር ይፋዊ ያልሆነ ጎዞ ላይ ከሚገኙት የህወሃት ባለስልጣናት መሀከል አቶ ስብኃት ነጋን በአካል አግኝቶ በግል ስልኩ እየቀረጸ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ጥያቴ አቀረበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በስዊድን ጉተንበርግ ከተማ ሊደረግ የታሰበው የዓባይ ግድብ የቦንድ ሽያጭ ከሸፈ

ተቃዋሚው ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ መድረኩን ተቆጣጠሮ ያዘ (ቪዲዮ አለው!)

በስዊድን ጉተንበርግ ከተማ ሊደረግ የታሰበው የዓባይ ግድብ የቦንድ ሽያጭ ከሸፈ

ከኢትዮጵያ ዛሬ ሪፖርተር

"ይገርማል!" ብሎ መጀመር ይቻላል። አዎን ይገርማል! ከስቶክሆልም የሄድነው ወደ አዳራሹ የገባነው ጥሪ ባደረጉበት 13፡00 ሰዓት ነበር። እ.ኤ.አ ኦገስት 31 ቀን 2013.። ህዝቡ እስኪሰባሰብ ጥቂት ከተጠበቀ በኋላ ስብሰባው በአንድ የኢህአዴግ/ወያኔ ካድሬ ተከፈተ። እንዲህም አለ፤ "እዚህ እኛን ለመቃወም የመጣችሁ እንዳላችሁ እናውቃለን። ሃሳባችሁን እንድትናገሩ አንከለክልም፤ ነገር ግን ጩኸት፣ አላስፈላጊ ረብሻና ግርግር የምትፈጥሩ ከሆነ ወዮላችሁ! አስቀድመን ባዘዝነው የፖሊስ ኃይል እየተለቀማችሁ ትወጣላችሁ። መውጣታችሁ ብቻ አይደለም፤ ታሪካችሁ ይጠፋል፣ ውርደት ይከተላችኋል። በመለያ ቁጥራችሁም ላይ የሚጻፈው ወንጀል ዕድሜ ልካችሁን ይከተላችኋል።"

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ