የጋራ ንቅናቄው ከሰማያዊ ፓርቲ ጎን ይቆማል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ጳጉሜን 2 ቀን 2005 ዓ.ም. September 7, 2013) ባለፈው ቅዳሜ ነኀሴ 25 የፌዴራል ፖሊስና የደኅንነት አባላት የሰማያዊ ፓርቲን ጽ/ቤት ጥሰው በመግባት የፈጸሙት ተራ የውብንድና ተግባር ብቻ ሳይሆን የህወሓት/ኢህዴግን ማንነት በግልጽ ያሳየ ለመሆኑ ከማንም በላይ ተግባሩ ራሱ ምስክር ነው በማለት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ድርጊቱን ኮነነ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"በመንግሥታዊ ውንብድና ትግላችን አይገታም!" ሰማያዊ ፓርቲ

ሰማያዊ ፓርቲ ቅዳሜ ጳጉሜን 2 ቀን በመስቀል አደባባይ ህዝባዊ የሰላማዊ ሰልፍ ጠራ

Ethiopia Zare (ሰኞ ነኀሴ 27 ቀን 2005 ዓ.ም. September 2, 2013)፦ እሁድ ነኀሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ የነበረው የሰማያዊ ፓርቲ ቅዳሜ ነኀሴ 25 ቀን ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ሲቪል በለበሱ ግለሰቦች መሪነት በፖሊሶች ጽሕፈት ቤቱን ጥሰው በመግባት አመራሮቹ መታሰራቸውንና ንብረቶች መወረሳቸውን ፓርቲው ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ህወሓት በአዜብ ጉዳይ ተወጥሯል

(እየሩሳሌምአርአያ)

ለስድስት አመት ኤፈርትን ሲመሩ የቆዩት /አዜብ መስፍን ከሃላፊነት መነሳት ተከትሎ በሕወሐት ውስጥ ውጥረት መንገሱን ምንጮች አመለከቱ። የኤፈርት ቦርድ ሰብሳቢ በነበሩት ባለቤታቸው አቶመለስ አማካይነት ዳይሬክተር ተደርገው አዜብ መሾማቸውን ያስታወሱት ምንጮች፣ ከመለስ ሕልፈት በኋላ ቦታውን የተረከቡት ኤርትራዊው ቴዎድሮስ ሃጎስ መሆናቸውን፣ እንዲሁም ዳይሬክተር የመሾምና የመሻር ስልጣኑ የቦርዱ መሆኑን ያስረዳሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያዊያኖች በቫንኩቨር ሰልፍ ወጡ

አባይ የህዝብ እንጂ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም!

Ethiopia Zare (እሁድ ነኀሴ 19  ቀን 2004 ዓ.ም. August 25, 2013)የአባይ ግድብ ሂደት ግልጻማነት የጎደለውና ኢትዮጵያዊያን ያልመከሩበት አገዛዙ የፈጠረው የፖለቲካ መጠቀሚያ ነው የሚሉ ኢትዮጵያዊያን በቫንኩቨር ካናዳ የተጠራውን የግድብ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ምሽት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአማራ ክልል የሚያመክን መድኃኒት የተወጉት ይናገራሉ

(ሊመለከቱት የሚገባ!)
በአማራ ክልል የሚገኙ በተለይም ወጣት ሴቶችን "ወረርሽኝ ገባ" በሚል ክትባት በመስጠት መውለድ እንዳይችሉ የማድረግ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመንግሥት መፈጸሙ አይዘነጋም። የዚሁ ሰለባ የሆኑ ሴቶችን "የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ" ለፀበል ያሉበት ቦታ ድረስ በመሄድ ቃለምልልስ አድርጎላቸዋል። እነሆ!

የቫንኩቨር ኢትዮጵያዊያን ተደስተዋል

 

ቤተክርስቲያናቸውቋሚቤተመቅደስአግኝታለች

በጥቅምት 2009 .. የብሪቲሽ ኮሉምቢያ ጠቅላይ ፍርድቤት 1990ዎቹ መጀመሪያ በሊቀካህናት ምሳሌ እንግዳ ቤተክርስቲያን ስር፡በነአቡነ ዜናማርቆስ ቡራኬ የተመሰረተውን የቫንኩቨር ቅድስት ማርያም ቤተክርትስቲያን አንስቶ ወደ ኢህአዴግ ለሚያጋድለው ስብስብ እንዲሰጥ ሲወስን፡ በስደተኛው ሲኖዶስ ስር የሚገኙ የቫንኩቨር ማርያም ልጆች አዝነው ነበር። የፍርድ ቤቱ ክርክር ሂደት በወቅቱበ ኢትዮጵያ ዛሬና በሌሎች ድረገጾች ላይ ተዘግቧል።ልምዱ ለሌሎችም ይጠቅም ዘንድ ወደፊትም እናትትበታለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በስዊዘርላን ኒዮን ከተማ የሚካሄደው የኢትጵያውያን ፌስቲቫል ዛሬ ይጠናቀቃል

ያሬድ ክንፈ ከኒዮ፣ ስዊዘርላንድ (ጥቂት ፎቶግራፎች ይዘናል)

በዓሉን ካደመቁት ሕፃናት በጥቂቱ
Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሐምሌ 13 ቀን 2005 ዓ.ም. July 20, 2013)፦ ረቡዕ ሐምሌ 10 ቀን 2005 ዓ.ም. (ጁላይ 17፣ 2013) በኒዮን የስዊዘርላንድ ከተማ የተጀመረው 11ኛው የአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ዛሬ ቅዳሜ ይጠናቀቃል። ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት፣ ከሰሜን አሜሪካ፣ ከኢትዮጵያ እንዲሁም ከተለያዩ አህጉራት የመጡ በርካታ ኢትዮጵያውንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለበዓሉ ድምቀት አስተዋጽዖ አድርገዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሽግግር ም/ቤቱ በኦስሎ ከተማ የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባ አደረገ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት የኖርዌይ ቻፕተር ጠቅላላ ህዝባዊ ስብሰባ 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት የኖርዌይ ቻፕተር ጠቅላላ ህዝባዊ ስብሰባውን ሰኔ 15 ቀን 2005 ዓ.ም (ጁን 22 ቀን 2013) ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በተገኙበት ታሪካዊና ስኬታማ ህዝባዊ ስብሰባ አደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከዓመት ከስድስት ወር እስር በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቃሊቲ ሰው ገብቶ እንዲጠይቀው ተፈቀደ

ከሕግ ውጪ መታሰሩን ተረድተው በያሉበት ድምፃቸውን ለሚያሰሙ ምስጋና አቅርቧል

"ስላደረጋችኹልኝ እና ስለምታደርጉልኝ ኹሉ አመሰግናለሁ!" እስክንድር ነጋ

"እስክንድር ለዚህን ያህል ወራት እስር ቤት መቆየቱን ተጠራጠርኩ፤ ጥንካሬው አሁንም አብሮት አለ" ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ Jornalist Eskinder Nega

Ethiopia Zare (ዓርብ ሰኔ 7 ቀን 2005 ዓ.ም. June 14, 2013)፦ ላለፉት አስራ ስምንት ወራት በእስር ላይ ያለው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ለመጀመሪያ ጊዜ ከባለቤቱ ከጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል እና ከልጁ ከናፍቆት ሌላ ሰው እንዲጠይቀው በዚህ ሣምንት መፈቀዱን ለመረዳት ችለናል። ዛሬ ጠዋት ቃሊቲ ሄደው ከጠየቁት ውስጥ ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ አንዷ ስትሆን፤ አላግባብ ከሕግ ውጪ መታሰሩን ተረድተው በያሉበት ድምፃቸውን ላሰሙና ለሚያሰሙ ሁሉ በያሉበት ምስጋናዬ ይድረሳቸው ብሏታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ