ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ የኃይለመድህን አበራን ጉዳይ ለመከታተል ጄኔቫ አመራ
13 may 2014 (EMF) የረዳት ፓይለት ኃይለመድህን አበራን ጉዳይ ለመከታተል ኢትዮጵያዊው የህግ ባለሞያ ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ ባለፈው ሳምንት ወደ ጄኔቭ-ስዊዘርላንድ ተጉዟል።
13 may 2014 (EMF) የረዳት ፓይለት ኃይለመድህን አበራን ጉዳይ ለመከታተል ኢትዮጵያዊው የህግ ባለሞያ ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ ባለፈው ሳምንት ወደ ጄኔቭ-ስዊዘርላንድ ተጉዟል።
ጫቱን ሲያስገቡ የተያዙት የሦስት ዓመት እስራት ይጥብቃቸዋል
Ethiopia Zare (ዓርብ ግንቦት 1 ቀን 2006 ዓ.ም. May 9, 2014)፦ 816 ኪሎ ጫት ከሎንዶን በስዊድንዋ የወደብ ከተማ ጉተምበርግ በኩል በመርከብ ተጭኖ ሲገባ አፕሪል ላይ መያዙንና ሁለት ሰዎችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ሜትሮ ጋዜጣ በዛሬው ዕትሙ አስነብቧል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...በተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች ታስረው የሰነበቱትና ቀሪዎቹ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ዛሬ ባደረጉት ሳምንታዊ የወጣቶች የውይይት ፕሮግራም አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) የ"እሪታ ቀን" በሚል የጠራውን ሰልፍ በግንባር ቀደምነት በመቀላቀል ድምጻቸውን እንደሚያሰሙ አስታውቀዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ጽዮን ግርማ - አዲስ አበባ
ዘወትር እንደምታደርገው ሁሉ በምታዝበት ሬዲዮ ጣቢያ ጓደኞቿን ሰብስባ ወደ ስቱዲዮ የገባችው ሚሚ ስብሃቱ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ስለታሠሩት ሁለት ጋዜጠኞችና ሰባት ጦማሪዎች ከፖሊስ አገኘኹት ያለችውን መረጃ ጠቅሳ ስታወራ ነበር። ኢትዮጵያን ለማተራመስ ከሚሠራው አርቲክል ዐሥራ ዘጠኝ ከሚባል ድርጅት ጋር ሲሠሩ ነበር፣ትልልቅ ሆቴል እየተገናኙ ይወያዩ ነበር፣ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎችን ያደራጁ ነበር፣ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅትና ከአምነስቲ እንዲሁም ከግብጽና ከኤርትራ ገንዘብ ይቀበሉ ነበር፤ የሚሉ ውርጅብኞችን በማውረድ እነርሱን የኢትዮጵያ ጠላት እራሷን ደግሞ የኢትዮጵያ ወዳጅ አድርጋ በመሳል ውንጀላዋን ስታዥጎደጉደው ነበር።
ጽዮን ግርማ (አዲስ አበባ)
Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዝያ 21 ቀን 2006 ዓ.ም. April 28, 2014)፦ ባለፈው ሳምንት ወደ ማእከላዊ እስር ቤት የተጣሉት ስድስት የ'ዞን ዘጠኝ' አባላትና ሶስት ጋዜጠኞች ሁኔታ አነጋጋሪ ሆኖ መሰንበቱ ይታወቃል። በአሁኑ ሰአት እስረኞቹ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ሲሆን ክስም እንደተመሰረተባቸው ለማወቅ ተችሏል። ሁኔታውን ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ በፌስ ቡክ ገጿ እንደሚከተለው ዘግባዋለች።
የማዕከላዊ ወንጅል ምርመራ ፖሊስ በትናንትናው (እሁድ) ዕለት ጠዋት አራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት አቅርቦ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል፡፡ በሦስት መዝገብ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ዘጠኝ ጸሐፊዎች አገሪቷን በሶሻል ሚዲያ ለማተራመስ ራሱን የመብት ተሟጋች ነኝ ብሎ ከሚጠራ የውጭ ኃይል ጋር በሐሳብም በገንዘብም ተረዳድተውና ተስማተው በአገሪቷ ላይ የብጥብጥ ቅስቀሳ ለማነሳሳት አቅደው ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸው በቁጥጥር ውለዋል ይህንንም በሚመለከት መረጃ እስክናሰባስብ ጊዜ ይሰጠን በሚል የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል፡፡
ሙሉውን አስነብበኝ ...በተመስገንደሳለኝ (አዲስ አበባ)
ፍትሕ ሚኒስቴር በረዳት አብራሪ ኃይለመድን አበራ ላይ የካቲት 9 ቀን 2006 ዓ.ም ሌሊት የበረራ ቁጥር ET 702 የሆንን ቦይንግ አውሮፕላንን ከእነ 202 ተሳፋሪዎቹ ወደ ሮም በሚበርበት ወቅት ጠልፎ ሲውዘርላንድ አሳርፏል በማለት በከፍተኛው ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ክስ መመስረቱን የፍትሕ ሚኒስቴር ምንጮቼ አረጋግጠውልኛል፡፡
ሙሉውን አስነብበኝ ...አምስት የአንድነት ፓርቲ አባላት ታስረዋል
Ethiopia Zare (ቅዳሜ መጋቢት 20 ቀን 2006 ዓ.ም. March 29, 2014)፦ ዛሬ ገዥው ፓርቲ በጎንደር ከተማ አደባባይ እየሱስ በጠራው ስብሰባ ለእያንዳንዳቸው ተሰብሳቢዎች 8ሺህ ብር ብድር በመስጠት መጭውን ምርጫ ግን ኢህአዲግን እንዲመርጡ በመቀስቀስ ላይ ባለበት ወቅት ምርጫን በገንዘብ መግዛት አይቻልም ብለው ጥያቄ ያቀረቡ አምስት የአንድነት ፓርቲ አባላት መታሰራቸውን አቶ ሃብታሙ አያሌው ዛሬ ይፋ አደረገ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...“በዉጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ በአካል ርቆ ቢገኝም ልቡ አገር ቤት ነዉ።” ኢ/ር ግዛቸው
አንድነት ፓርቲ በ450 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ለመወዳደር እቅድ አለው
Ethiopia Zare ሰኞ ካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. March 3, 2014)፦ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር፣ በአሜሪካ ካሉ የድጋፍ ማህበራት ጋር ወደ ሁለት ሰዓት የሚጠጋ ሰፊ ዉይይት በቴሌኮንፈራንስ አደረጉ። ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራዉ ፣ የአንድነት ፓርቲ እያደረጋቸው ስላለው ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች ሰፋ ያለ ሃታተ የሰጡ ሲሆን፣ ከስብሰባው ተሳታፊዎች በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጠዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ጽዮን ግርማ
Ethiopia Zare (ሰኞ የካቲት 17 ቀን 2006 ዓ.ም. Feb. 24, 2014)፦ ዛሬ በምሳ ሰዓት አካባቢ፤ በሱፍቃድ በጋሻው የተባለ ዕድሜው በሃያዎቹ ውስጥ የሚገመት ወጣት በቦሌ መንገድ ላይ ከአራት ጊዜ በላይ በተከታታይ ወደ ሰማይ ከተኮሰ በኋላ ራሱን አጠፋ። ራሱን ከማጥፋቱ በፊት ”ኑሮ መሮኛል” ሲል ተሰምቷል።
አዲሱ አምባሳደር ሀፍረት ገጠማቸው
አቢይ አፈወርቅ
Ethiopia Zare (ቅዳሜ የካቲት 15 ቀን 2014 ዓ.ም. Feb. 22, 2014)፦ በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አረጋ ሀይሉ ትላንት (ቅዳሜ ፌብሯሪ 22 ቀን) የሲድኒ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያንን በልማት ዙሪያ ለማነጋገር የያዙት ፕሮግራም በአሳፋሪ ሁኔታ ተደመደመ።