በጀርመን ፍራንክፈርት የሻማ ማብራት ሥነሥርዓትና የፊርማ ማሰባሰብ ተካሄደ

Ethiopia Zare (ሰኞ መስከረም ፲፮ ቀን ፪፲፻፱ ዓ.ም. September 26, 2016)፦ በኢትዮጵያ በሥልጣን ላይ ያለው የወያኔ/ኢህአዴግ መንግሥት በኦሮሞ፣ በአማራና በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ውስጥ እየወሰደ ያለውን የመግደል፣ የማሰቃየትና የማሰር ተግባር በመቃወም፤ በጀርመን ሀገር ፍራንክፈርት ከተማ ቅዳሜ መስከረም ፲፬ ቀን ፪፲፻፱ ዓ.ም. ዕለት የሻማ ማብራት ሥነሥርዓት ተካሄደ። ይኸው ሥነሥርዓት የጀርመንዋ መሪ አንጌላ መርክል በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉዞ እንዲሰርዙ የሚጠይቅ የፊርማ ማሰባሰብን ያካተተ እንደነበር ለኢትዮጵያ ዛሬ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...

(ኢ.ኤም.ኤፍ) ከሚኖርበት ሆላንድ ወደ ትውልድ ሀገሩ ኢትዮጵያ የገባው ወጣት ለይኩን እሸቱ፤ በፋሲካ በዓል ዋዜማ ስምንት ቦታ በስለት ወግተው የገደሉት ወንጀለኞች እስካሁን አልተያዙም። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ገዳዮቹ ባለጊዜዎች ስለሆኑ ሟች ደመ ከልብ ሆኖ ቀርቷል።








