”ፕ/ር መረራን ያሰርኩት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ስለጣሱ ነው” ኮማንድ ፖስቱ

Prof. Merera Gudina

ኢትዮጵያ ዛሬ (እሁድ ኅዳር ፳፭ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 4, 2016)፦ ፕ/ር መረራ ጉዲና ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ከፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር በቤልጅየም ብራስልስ ”ተገናኝተው በመውያየታቸውና መግለጫ በመስጠታቸው” ነው ያሰርኳቸው ሲል ኮማንድ ፖስቱ ገለጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የግብጽና የኤርትራ ፕሬዝዳንቶች በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር ተገናኙ

Sisi and Isaias met in Cairo

ኢትዮጵያ ዛሬ (ቅዳሜ ኅዳር ፳፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 3, 2016)፦ የግብጹ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አልሲሲ ከኤርትራው አቻቸው ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በካይሮ ተገናኙ። የተገናኙት በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር እና በቀጣይ ጉዟቸው ላይ ሊመክሩ እንደሆነ ተዘገበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አትሌት አልማዝ አያና የዓመቱ የዓለም ምርጥ አትሌት ተብላ ተመረጠች

Almaz Ayana and Husain Bolt

ኢትዮጵያ ዛሬ (ቅዳሜ ኅዳር ፳፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 3, 2016)፦ ዓለማቀፉ የአትሌቲክስ ማኅበር ፌደሬሽን ኢትዮጵያዊቷን የ10 ሺህ ሜትር ሪኮርድ ባለቤት አልማዝ አያናን የ2016 የዓለም ምርጥ አትሌት በማለት ትናንት ማምሻውን የሸለማት ሲሆን፣ ከወንዶ ትሌቶች ደግሞ ጃማይካዊው የአጭር ርቀት ሯጭ ዩሴን ቦልት ተሸላሚ ሆኗል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አብርሃ ደስታና ዳንኤል በድጋሚ ሊታሰሩ ነው፤ እነ ሀብታሙ በነጻ ተሰናበቱ

ሀብታሙ አያሌው፣ የሽዋስ አሰፋ እና አብርሃም ሰለሞን በነጻ ሲሰናበቱ፤ ዳንኤል ሺበሺ እና አብርሃ ደስታ ተከላከሉ ተባሉ

Ene Abraha Desta

ከፍተኛ ፍርድ ቤት በነፃ ባሰናበታቸው አምስት ተከሳሾች (ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ አብርሃ ደስታ፣ የሽዋስ አሰፋ እና አብርሃም ሰለሞን) ላይ አቃቢ ሕግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብሎ ዓመት ከሦስት ወር በላይ በቀጠሮ ሲራዘም የነበረው ጉዳይ ዓርብ ኅዳር ፳፫ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. (Dec. 2, 2016) ብይን ተሰጥቶበታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኞች ስደት ቁጥር ጨመረ

- ጋዜጠኛ ሁሴን አብዱልቀኒ፣ ብዛየሁ እና ታምሩ ወደ አገር አይመለሱም!

- ፳፯ የስፖርት ጋዜጠኞች በስደት ይገኛሉ

Ethiopian sport journalists

(ኢትዮኪክ) የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበር ዓመታዊ ስብሰባውን በኢንተር ኮንቲነንታል ሆቴል በ2008 ሲያካሄድ፤ የማኅበሩ ም/ፕሬዚዳንት ጋዜጠኛ ሁሴን አብዱልቀኒ እና ጋዜጠኛ አምሀ መድረኩን ሲመሩት እንደነበር የሚታወስ ነው። ሆኖም ዘንድሮ ሁለቱን ጋዜጠኞች ጨምሮ በማኅበሩ ውስጥ አምና የነበሩ ዘንድሮ በስደት ከማኅበሩ 8 የሚደርሱ የስፖርት ጋዜጠኞች አይኖሩም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አና ጎሜዝ የፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን እስር በጽኑ ኮነኑ

Ana Gomes

ኢትዮጵያ ዛሬ (ዓርብ ኅዳር ፳፫ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Dec. 2, 2016)፦ በዶ/ር መረራ ጉዲና መታሰር ስጋት እንደገባቸው በመግለጽ፤ አስቸኳይ ደብዳቤ ለአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ክፍል የጻፉት የአውሮፓ ፓርላማ አባል አና ጎሜዝ፤ የኢትዮጵያ ዋነኛ የልማት አጋር የሆነው ሕብረቱ ፈጣን እርምጃ እንዲወስድ ጠየቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፕ/ር መረራ ጉዲና አዲስ አበባ ሲገቡ ታሰሩ

የታሰሩት በአውሮፓ ሕብረት ባደረጉት ንግግር እና ከፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር በመታየታቸው ይሆናል ተብሎ ይገመታል

Prof. Merera Gudina

ኢትዮጵያ ዛሬ (ረቡዕ ኅዳር ፳፩ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Nov. 30, 2016)፦ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር የሆኑት ፕ/ር መረራ ጉዲና መታሰራቸው ተጠቆመ። ፕ/ር መረራ የታሰሩበት ምክንያት ለጊዜው በትክክል ባይታወቅም፤ በአውሮፓ ሕብረት ተገኝተው ባደረጉት ንግግርና ከፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር በመታየታቸው ሊሆን ይችላል ተብሎ ይጠረጠራል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ