የእስራኤል ፓርላማ በዌስት ባንክ ያስተላለፈው ውሳኔ ተቃውሞ ገጠመው

ኢዛ (ማክሰኞ ጥር ፴ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Feb. 07, 2017)፦ በዌስት ባንክ የተገነቡ አራት ሺህ ቤቶችን ለዜጎቹ የሚያስተላልፍ ውሳኔ የእስራኤል ፓርላማ ትናንት ማጽደቁ ተዘገበ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢዛ (ማክሰኞ ጥር ፴ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Feb. 07, 2017)፦ በዌስት ባንክ የተገነቡ አራት ሺህ ቤቶችን ለዜጎቹ የሚያስተላልፍ ውሳኔ የእስራኤል ፓርላማ ትናንት ማጽደቁ ተዘገበ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...እገዳው ከፕ/ት ትራምፕ ጋር የንግድ ግንኙነት ያላቸውን አገራት አላካተተም

ኢዛ (ሰኞ ጥር ፳፪ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Jan. 30, 2017)፦ ፕ/ት ዶናልድ ትራምፕ ባወጡት አስቸኳይ እገዳ ውስጥ በተካተቱት ሰባት አገራት ዜጎች እ.ኤ.አ. ከ1975 እስከ 2015 ድረስ አንድም አሜሪካዊ አለመገደሉን ሲኤንኤን ዘገበ። በተቃራኒው በእነዚሁ ዓመታት ውስጥ የሳውዲ ዐረቢያ ዜጎች 2,369፣ የተባበሩት ዐረብ ኢምሬትስ ዜጎች ደግሞ 314፣ እንዲሁም ግብጻውያን 162 አሜሪካውያንን መግደላቸውን ዘገባው አክሎ ገልጧል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ታህሳስ ፲፱ ቀን ፪ሺ፱ ዓ/ም (DECEMBER 28,2016) ከአሜሪካን ታዋቂ ከሚባሉ ከተሞች መካከል አንዷ በሆነችው በላስ ቬጋስ ከተማ “አገርህን እወቃት፣ ከጠላትም ጠብቃት” በሚል መሪ ቃልና ቅስቀሳ የታደሙው የከተማው ነዋሪ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳን በከፍተኛ ጭብጨባና ከፍ ባለ አክብሮት ወደ አዳራሹ ሲገቡ ተቀብሏቸዋል።

ከጎንደር ታቦቱን ከመቅደሱ ገብተው መሸከም እስኪቀራቸው ድረስ የመንግሥት ወታደሮች ካህናቱን ቶሎ በሉ፣ ቶሎ በሉ እያሉ ያጣድፏቸው ነበር። ታቦት በራሳቼው ላይ የተሸከሙ አባቶች ሁለት እጆቻቸው ታቦቱን ቢደግፉም እንባዎቻቸው በጎንደር አስፋልት ላይ ጠብ፣ ጠብ፣ እያሉ ሲፈሱ ከበርካታ ካህናት ዓይኖች ቀረብ ብዮ አስተውያለሁ፣ መስቀል ኃይል ነው ብላ የምታምን ቤተክርስቲያን ዛሬ ስናይፐር ኃይል ነው የሚል መንግሥት በስናይፐር የጎንደር ታቦቶች እንዲታጀቡ አደረገ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢዛ (ሰኞ ጥር ፰ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Jan. 16, 2017)፦ ትናንት በስፔን አገር የሲቪያ ከተማ አካል በሆነችው ሳንቲፖንሴ ከተማ በተካሄደው 35ኛው አገር አቋራጭ ዓለም አቀፍ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ አንደኛ በመውጣት አሸንፋለች። በወንዶች ደግሞ ለባህሬን የሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊው አትሌት አወቀ አያሌው አንደኛ ሲወጣ፣ አትሌት ታፈሰ ሰቦቃ ደግሞ ኢትዮጵያን ወክሎ ሦስተኛ ወጥቷል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢዛ (ሰኞ ጥር ፰ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Jan. 16, 2017)፦ ኢትዮጵያዊው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ትናንት በሂዩስተን በተካሄደው የግማሽ ማራቶችን ውድድር ዳግም ታሪክ ሠራ። ውድድሩን ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀ ሲሆን፣ እንደለመደው እጆቹን በማመሳቀል በአገሩ ውስጥ መንግሥት እያካሄደ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት አሳይቷል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...”መብቶች ይከበሩ፣ ለሕዝብ ቅሬታዎች መልስ ይሰጥ” ሂዩማን ራይትስ ዎች

ኢዛ (ዓርብ ጥር ፭ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Jan. 13, 2017)፦ ሂዩማን ራይትስ ዎች ትናንት ባወጣው ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት እ.ኤ.አ. 2016 የሰብዓዊ መብቶች ቀውስ ውስጥ ወድቃለች ማለቱ ተደመጠ። ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ መሰረታዊ መብቶችን ገድባ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ደም አፍሳሽ አፈናዋን ቀጥላለች፣ በዘፈቀደ ታስራለች፣ ማኅበራዊ መገናኛ ብዙኀንን ገድባለች በማለት ሪፖርቱ ያትታል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢዛ (ዓርብ ጥር ፭ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Jan. 13, 2017)፦ በአገር ውስጥ ታክሞ መዳን በማይችል ሕመም ሲሰቃይ የከረመው ፖለቲከኛ ሀብታሙ አያሌው አሜሪካ ገባ። በእስር ቤት ሳለ በሕክምና ክትትል ማጣት ሳቢያ በቀላሉ ሊድን ይችል የነበረ ሕመሙ ከተፈታም በኋላ ጸንቶበት ሆስፒታል ተኝቶ ነበር።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ኢዛ (ኀሙስ ታህሳስ ፳፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. Jan. 05, 2017)፦ በዛሬው ዕለት ኢዝሚር በተባለች የቱርክ ከተማ በፍርድ ቤት አቅራቢያ ሦስት ታጣቂዎች የሽብር ጥቃት ፈጸማቸውንና ሁለቱ ጥቃት ፈጻሚዎች፣ አንድ ፖሊስ እና አንድ የፍርድ ቤቱን ሠራተኛ መግደላቸውን የቱርክ የመንግሥት መገናኛ ብዙኀን ዘገቡ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...አቤል ዋበላ ከሚያዝያ 2006 ጀምሮ ለ18 ወራት "በፀረ ሽብርተኝነቱ" አዋጅ ከዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች ጋር ታስሮ ከርሞ በጥቅምት 2008 በነጻ ሲሰናበት የቀድሞ መሥሪያ ቤቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ "መልሼ አልቀበልህም" በማለቱ አቤል ክስ መመሥረቱ ይታወሳል። አየር መንገዱም "እንዲያውም ለሥራ ሥልጠና ያወጣሁበትን ወጪ ካሣ ይክፈለኝ" የሚል ሌላ ክስ መሥርቶበት፣ አቤል የመሠረተው ክስ እስኪጠናቀቅ የአየር መንገዱ ክስ በእንጥልጥል እንዲቆይ ተደርጎ ነበር።
ሙሉውን አስነብበኝ ...