በሽብር የተጠረጠር የጭነት መኪና በስቶክሆልም ሦስት ገድሎ፣ ስምንት አቆሰለ

ኢዛ (ዓርብ መጋቢት ፳፱ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. April 7, 2017)፦ ዛሬ ረፋዱ ላይ በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም አንድ የጭነት መኪና በመዲናዋ እምብርት ሕዝብ በብዛት በሚተላለፍበት አካባቢ በሰዎች ላይ በመንዳት እና በስተመጨረሻም ኦሊየንስ የሚባለው ሱቅ ከሚገኝበት ሕንጻ ጋር ተላትሞ ነድዷል። በአደጋው ሦስት ሰዎች ሲሞቱ፣ ስምንት ሰዎች ቆስለዋል። ፖሊስ በቦታው ላይ በሰዓቱ ታይቷል ብሎ ያለውን ሰው ፎቶግራፍ ለሕዝብ ይፋ አድርጓል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...











