World Rally, Sweden 02032009By Matias Ketema

Ethiopia Zare (ማክሰኞ የካቲት 24 ቀን 2001 ዓ.ም. March 3, 2009)፦ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑትን የወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳን አላግባብ መታሰር በመቃወም ትናንት ሰኞ የካቲት 23 ቀን በዓለም አቀፍ ሁኔታ የተዘጋጀው ሰልፍ በስዊድን ዋና ከተማ በስቶክሆልም በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ።

 

ሰልፉ የተደረገው በአሜሪካን ኤምባሲ ፊት ለፊት ሲሆን፣ ሰልፈኛው ከቀኑ ሰባት ሰዓት (13፡00 ሰዓት) ጀምሮ ልዩ ልዩ በጨርቅ የተወጠሩ ጽሑፎችን በጋራና በግል በመያዝ፣ መፈክሮችን በማሰማት ቆይቶ፤ የሰልፉ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ምትኩ የሱፍ ስለሰልፉ አጭር መግለጫ ከሰጡ በኋላ የስዊድን የአንድነት ፓርቲን ለመምራት በቅርቡ የተመረጡት አቶ ራስወርቅ መንገሻ ንግግር እንዲያደርጉ ጋብዘዋል።

 

አቶ ራስወቅም ኢትዮጵያን ጨምድዶ የያዘው ኃይል የሀገሪቷ ጠንቅ መሆኑን ገልጸው፤ የሰልፉንም ዓላማ በማብራራት የፓርቲያቸው ሊቀመንበር የሆኑት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳና ሌሎች አለፍርድ የታሰሩ ሁሉ እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

 

 

World Rally, Sweden, 02032009
 

 

ንግግራቸውንም በመቀጠል፣ ባሁን ጊዜ ያለብን ችግር በገዥው የግፍ ሥራ ላይ ያተኮረ በመሆኑ፤ አዛውንት፣ ወጣትና ልጅ ሳንል በድርጅት ሳንከፋፈል በአንድነት በመነሳት ተቃውሞአችንንና ትግላችንን ማጠናከር አለብን በማለት አሳስበዋል።

 

በቦታው ላይ ከ150 በላይ ሰዎች የተገኙ ሲሆን፣ በተናጠል እየወጡ ንግግርና መፈክሮች በማሰማት በግፍ የታሰሩ ሁሉ እንዲፈቱ ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል። እንዲሁም ”ድምፃችን ይሰማ!” የሚል የሰልፉን ዓላማ አስመልክቶ የተጻፈ ወቅታዊ ግጥም ተነቧል። በማያያዝም በአሜሪካን ኤምባሲ በኩል ለፕሬዝዳንት ኦባማ እንዲሰጥ የተዘጋጀውን ደብዳቤ በኤምባሲው ጽሕፈት ቤት ሁለተኛ ሰው ተሰጥቶል።

 

በመጨረሻም ለዓለም አቀፉ ሰልፍ የስዊድን ተውካይ ለሆኑት ለአቶ አህመድ ዓሊ የተላለፈና ለኤምባሲው የቀረበው ደብዳቤ በአቶ ስሜነህ ታምራት ለህዝቡ ተነቦ ሰልፉ ዘጠኝ ሰዓት ተኩል (15፡30 ሰዓት) ተጠናቋል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ