”እረፍት አድርግ አሁን” (ጌታቸው አበራ)

”እረፍት አድርግ አሁን”

(ለፖፕ ሙዚቃ ንጉሥ - ለማይክል ጃክሰን መታሰቢያ)

ጌታቸው አበራ ሰኔ ፪ ሺህ ፩ ዓ.ም. (ጁን 2009) This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

በድምፅህ ቅላፄ ዓለምን ያስደመምክ፣

በእስክስታ ... በዳንስህ አህዛብ ያስጨፈርክ፣

የምዕተ-ዓመቱ ሰው፤ ልቀህ የተተኮስክ፣

ያለምን ዕይታ በበጎ የለወጥክ ...፤

የጥበብ ማኅደር ... የሙዚቃ ድግስ፣

ማይክል ጃክሰን! የ”ፖፕ” ሊቅ ንጉሥ!

(ሙሉውን ግጥም በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ)

የነፃነት እልህ (ወለላዬ)

የነፃነት እልህ

ወለላዬ ከስዊድን This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  

(በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ) 

ነፃነትህ ጠፍቶ መብትህ ሲሸረሸር፣

ተስፋህን ሲያጠፉት እንዳትኖር በሀገር፣

ያለ የሌለውን እየቦጠበጡ፣

በደምህ ሲከብሩ በላብህ ሲያጌጡ፣

ጠረፍ ላይ ያለውን ያጥንትህን ችካል፣

ጠላት አስገብተው ነቃቅለው በመጣል፣

ሊኖሩ ካሰቡ ሥልጣን ላይ ባንተ ደም፣

ደንቆሮ ካረጉህ ያልገባው መኃይም፣

ዝም ብለህ አትይ ከህዝብ ጋር አብር

መሆንክን ተረዳ የሀገር ወታደር

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እሽሩሩ (አስፋወሰን ዓለምሰገድ)

እሽሩሩ

አስፋወሰን ዓለምሰገድ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

እሽሩሩ ...

እሽሩሩ ...

እሽርሩ ማሙዬ ...

ልንከባከብህ ’እሽሩሩ ...’ ብዬ

አባት ሆኛለሁ በተራዬ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በቃኝ! (ብርዞ)

በቃኝ! 

ብርዞ ከፍራንክፈርት This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  

በቃኝ! እኔ በቃኝ! አዎ! በቃኝ! በቃኝ! ...

በደል ግፍ ስሰማ እኔን መሰል ስቃኝ

አልንበረከክም እጄንም አልሰቅልም

ህሊና አስገድሎ ሆድ ማዳን አይቀልም

ውርስ ላይሆን ከቶ ለትውልድ ለሀገር

ነፃነት አይሸጥ መብት አይመነዘር

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ስም ልቀይርልህ (ማናለህ)

ስም ልቀይርልህ

ማናለህ ከአሳረኛው ሀገር ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

 

እየተሳበበ በቁስቋም መባቻ፣

ቁም-ስቅልህን ካየህ በመወለድ ብቻ።

ስሙን ልቀይረው

እነብሴን፣

በሀውዜን።

ትባል እንዋሪ፣

ለጊዜው መይ ነብሪ።

ደላንታም ይሰየም፣

ተብሎ አዲጉደም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...