እያንጓለለ - የምርጫ ጭውውት (ዳግማዊ ዳዊት)
እያንጓለለ (የምርጫ ጭውውት)
ዳግማዊ ዳዊት This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
እያንጓለለ …
ያ ገብስማ ዶሮ - ዘንድሮስ ምን አለ? ሙሉውን አስነብበኝ ...
እያንጓለለ (የምርጫ ጭውውት)
ዳግማዊ ዳዊት This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
እያንጓለለ …
ያ ገብስማ ዶሮ - ዘንድሮስ ምን አለ? ሙሉውን አስነብበኝ ...
በጥምቀት በገና
በትልቁ በዓል በብርሀነ ልደቱ
ኃይሉ ከእኛ ራቀ ምን ይሆን ምክንያቱ
ላስታ እጅግ ተከፍቶ አምናና ካቻምና
አላከብርም አለ ልደት ክርስትና
ዘንድሮ ተረኛው አንኮበር ሆነና
ኃይሉን አጥቶ ዋለ በጥምቀት በገና
ታ. ታ.
ታኅሳሥ 1999
ሐይቲ
ጌታቸው አበራ (ጥር 2002 ዓ.ም. / ጃንዋሪ 2010)
ጠዋት ፀሐይ ወጥታ፣
ብርሃን ተሞልታ፤
ቀዬው ደጁ ደምቆ፣
ሕይወትን ሰንቆ …፤
የፊቱን አሻግሮ …፣
ርዕዩን ቀምሮ፣
“ነገም ሌላ ቀን ነው” ብሎ ሳያበቃ፣
ዛሬ “ሌላ” ሆነበት ተፈፀመ፤ በቃ! ሙሉውን አስነብበኝ ...አልነጋም- ገና ነው!
ዳግማዊ ዳዊት This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
የሰማይ ኮርኒሥ ሆኖ - ማቅ የመሰለ ደመና
ከታችም አውሎ ነፋስ - ፉጨቱን እያሰማ
አቧራውን አስነስቶ - ዛፍ ቅርንጫፉን እያሾረ
ዛሩ እንደወረደ ባለአውሌ - አለመጠን እያስጨፈረ
ዓይን ቢወጉ በማያሳይ - ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ
ወዴት ነው መድረሻችን - ጉዟችን የሚያቀና? ሙሉውን አስነብበኝ ...
ምነው?!
ጌታቻው አበራ
እንደሾተላይ ቅርቃር - ልቤ ውስጥ ተሰንቅሮ፣
እንደመጋኛ ውጋት - ክፉኛ ጎኔን ወድሮ፣
ሽብር በሆዴ ነስንሶ - እሚልሰኝ ጧት ማታ፣
ሕመሟ ሕመም ሆኖኝ - ዘወትር እማይገታ፣
ክፉ ዜናዋን ሰምቼ - እንዴትስ ልደር ተኝቼ?
ምነው ስቃይ መከራ - ተሰጠስ ለኔ ባደራ! ሙሉውን አስነብበኝ ...