እኛ ግን ለውጥ የለን (ስሜነህ ታምራት)

እኛ ግን ለውጥ የለን

ስሜነህ ታምራት (ከስዊድን)

ከአዲስ ዘመን ጋራ - አዲስ ተስፋ ሳይወለድ

የታሰረው ሳይፈታ - የተፈታው ሳይራመድ

ተቻችሎ ለሀገር መሥራት - እንደባህል ሳይለመድ

አብሮ መብላት አብሮ መጨፈር - ምን ሊፈይድ

ምንስ ሊያመጣ - ምንስ ሊወስድ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለኛኮ ነው! (ጌታቸው አበራ)

ለኛኮ ነው!

(በብርቱካን ሚደቅሳ ስም፣ በመላ አገሪቱ ለሚገኙ የፖለቲካና የኅሊና እስረኞች)

ጌታቸው አበራ (ጳጉሜን 2002 ዓ.ም./ሴፕቴምበር 2010)

ኢትዮጵያዊነት ማተብ ነው - ቃልም የዕምነት ዕዳ፣

እንደ ወርቅ በእሳት የሚፈተን - የመስዋዕትነት ፍዳ፤

ለምዕታት የዘለቀ - አገር-ምድሩን ያዳረሰ፣

እማያቋርጥ ጅረት ... ለትውልዶች ... የፈሰሰ፣

ቋት መከራው የደም ግብር - ስንት ጀግና ያሰየፈ፣

ልምላሜው ላገር ክብር - ዝና፣ ኩራት፣ ... ያተረፈ፤

ኢትዮጵያዊነት ማተብ ነው! በደም-ሥር ውስጥ የሠረጸ!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እንበል አስራ ሰባት (እንቆጳ)

እንበል አስራ ሰባት*

ከእንቆጳ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ከጨለማው በስተጀርባ

ከድቅድቁ ብርሃን አልባ

ከጣይቱ መውጫ ማዶ

ሰው አየሁኝ ዛሬ ማልዶ። ሙሉውን አስነብበኝ ...