የረቡዕ ግጥም ፴፱
”ግልፅ ነው ይሄ ሰው የግንባር ላይ ሥጋ
እውነትን አፍረጥራጭ ጨርሶ ሳይሰጋ”
በማለት ብዙ ሰው ይችላል ሊያደንቅህ
ወይም ባፉ ብቻ ሸነጋግሎ ሊያልፍህ
እኔ ግን አጥብቄ እናገርሃለሁ
ሁሉንም አትዘርግፍ ብዬ እመክርሃለሁ
ሙሉውን አስነብበኝ ...”ግልፅ ነው ይሄ ሰው የግንባር ላይ ሥጋ
እውነትን አፍረጥራጭ ጨርሶ ሳይሰጋ”
በማለት ብዙ ሰው ይችላል ሊያደንቅህ
ወይም ባፉ ብቻ ሸነጋግሎ ሊያልፍህ
እኔ ግን አጥብቄ እናገርሃለሁ
ሁሉንም አትዘርግፍ ብዬ እመክርሃለሁ
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ጭንቀት
ገ/ኢ. ጐርፉ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
እንዲህ ተዋርጄ በሰው ፊት አፍሬ
ተስፋ መቁረጥ ቆሞ ያንኳኳል ከበሬ
ወዴት ነው እምገባው ከንግዴህስ ወድያ
ይቅር ሁሉ ይብቃኝ፣ ኧረድያ! ኧረድያ!
ሰፊው ዓለም ሳለ የተንጣለለው
ልቤ ተጨነቀ መሬት ጠበበው
ወይእኔ ዘንድሮ የገባሁት ዕዳ
ማምለጫውም ጠፋኝ መሹለኪያ ቀዳዳ
ልቤ እንዳረረ፣ ነድዶ እንደበገነ
ጉዴም ሰው ሳያውቀው እንደተከደነ
ሌላ ተጨማሪ ሳይመጣብኝ ጣጣ
ከመከራው ዓለም በየት በኩል ልውጣ?
ገ/ኢ. ጐርፉ mailto:This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
የትናንትናውን ዛሬ ላታገኘው
ብለህ አትናገር ”ደሞ ለዛሬ ሰው”
ቀኑን ከተረከብክ እስከ አሰስ ገሰሱ
የዛሬ ሆነሃል አንተም ልክ እንደሱ
ሙሉውን አስነብበኝ ...ምነው ኖርዌይ!?
ወለላዬ ከስዊድን
ሀገራችን በግፍ ችንካር ተከንችራ፤
በሞት ሽረት ተውጥራ፤
የመከራ የጭንቅ ማቅ፤
ተከናንባ ስትማቅቅ፤
ከግፈኞች መዳፍ ወጥተን፤
ባንቺ ጉያ ተወሽቀን፤
ግዜ ባማጥን ቀን በገፋን፤
ምነው! ምነው! ምነው! ኖርዌይ ምነው! ኦስሎ?
ችግራችን ታየሽ ቀሎ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ሆዱ ያኖረውን በድንገት ሲያወጣ
ተሰደብኩኝ ብለህ ወንድሜ አትቆጣ
ይልቅ ነካ አድርገው ቆጥቦ እንዳያስቀር
ያንግዜ ነው ጆሮ ባዳነቱ የሚቀር
ሙሉውን አስነብበኝ ...