አሆ:'( ...
ያውና ያውና
ይታያልና
አዎ( ...
የቁርጥ ቀን ዜና
ይሰማል ገና

ሚዜ ነን ያላችሁ
ወዴት ገባችሁ? ? ?

ሀገሬ ናት ሀብቴ
ህዝቤ ነው ኩራቴ
ችግር ቢደራረብ ብጠቁር ብከሳም
አሄ ... ሄ ... ሄ!
አገሬን አልረሳም

ብለው የዘፈኑ
ብለው የደነሱ
ብለው ያለቀሱ
ወደ የት ደረሱ? ? ?

‘ማይክ‘ ይዘው እንስቅስቅ
ስቅ
ስቅ
ብለው እያነቡ
ባገር ፍቅር ሰክረው እንባ እያዘነቡ
ባገር አደባባይ እንዳልተጠበቡ
ኧረ ምን ዋጣቸው? ዛሬ ወዴት ገቡ???

አሄሄ
ሳንመዝነው ጥጡን
ንገሩን ቁርጡን!!

ሚዜነን ብላችሁ
ልክ እንዳብሪ ኮኮብ አምራችሁ ደምቃችሁ
ከኛ በላይ ላሳር
በሚባል ስንክሳር
ድብንቅ ያላችሁ
በሙሸራው ዘመን
በቁርጠኛው ጊዜ የት ተሰወራችሁ???
እናንተን ሲጠብቅ እድምተኛው ከቦ
ከብር አምባር በፊት
አለ ነገር ሲባል የት ገባችሁ አቦ ???

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ