(ወለላዬ ከስዊድን)

ለረጅም ዓመታት፣

ለብዙ ዘመናት፣

ፓርቲ ሲጠልዘኝ፣

መንግሥት ሲረግጠኝ፣

ፖሊስ ሲነርተኝ፣

ሕጉ ሳይደግፈኝ፣

ዳኛው ቢፈርድብኝ፣

በቡድን ተካፍለው፣

በስም ተሸንሽነው፣

የሚጠልዟት ኳስ፣

የሚነርቷት ኳስ፣

ምትለጋዋ ኳስ፣

እኔ ራሴን መስላኝ፣

ኳስ አፍቃሪ ሆንኩኝ።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ