በዐረብ ሀገራት በኢትዮጵያውያን ላይ ስለሚደርስ በደል ምስክርነት

ላለፉት ሰባት ዓመታት በዐረብ ሀገር የኖረችና ከአራት ወራት በፊት ነዋሪነቷን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገች ወጣት ኢትዮጵያዊት፣ ከኢትዮቲዩብ ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ በዐረብ ሀገር የነበራትን ቆይታ፣ በሀገር ቤትም ያለውን ችግር፣ የኢትዮጵያን ኤምባሲ በተመለከተ በግሏ የደረሰባትን ስትገልጽ ልብ ትሰብራለች። ትናንት ኅዳር 5 ቀን 2006 ዓ.ም. (ኖቨምበር 14፣ 2013 እ.ኤ.አ.) ዋሽንግተን ዲሲ በሳዑዲ ዐረቢያ ኤምባሲ በርካታ ኢትዮጵያውያኖች የተቃውሞ ሰልፍ ባደረጉበት ወቅት ነበር ኢትዮቲዩብ ያናገራት። 

 

”ኖ ዉሜን፣ ኖ ድራይቭ” ሂሻም ፋጊህ

ይኸ ቪዲዮ የቦብ ማርሊን ”No Women, No Cry” ሙዚቃ ”No Women, No Drive” በሚል ግጥሙንና የሙዚቃ መሣሪያዎቹን በመቀየር የተሠራ ሙዚቃ ሲሆን፣ ዩቲዩብ ላይ በተለቀቀ በሁለት ቀን ውስጥ ከ3 ነጥብ 6 ሚሊዮን ጊዜ ታይቷል። በሳዑዲ ዐረቢያ ያለው ሥርዓት ሴቶች መኪና እንዳይነዱ የሚያግድ መሆኑን በምፀታዊ ግጥሙ የሚነካ ሲሆን፣ ዘፋኙ ሂሻም ፋጊህ ሲባል ሙዚቃውን ካቀናበሩት ውስጥ አላ ዋርዲ ይገኝበታል። አላ ዋርዲ ሳዑዲ ዐረቢያ ውስጥ የሚኖር ኢራናዊ የሙዚቃ አቀንቃኝና ባለሙያ ነው።

አርቲስት አላ ዋርዲ ከአራት ዮርዳኖሳውያን ጋር በመሆን አ.ኤ.አ. 2011 ሐያጃን የተባለውን ሮክ በዐረብኛ የሚጫወት የሙዚቃ ቡድን (ባንድ) መስርቷል። አላ ዋርዲ በባንዱ ውስጥ በአቀንቃኝነት፣ ኪቦርድ እና አኮስቲክ ጊታር በመጫወት ያገለግላል። ቡድኑ ግንቦት 2013 ላይ ”ያ ባይ” የተሰኘውን የመጀመሪያውን አልበም አውጥቶ ነበር። (ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!)

 

ኢህአዴግ፣ አንድነት፣ ሰማያዊ፣ መድረክና ኢዴፓ በፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ላይ ያደረጉት ውይይት (ክፍል ፩ እና ፪)

በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ላይ ኢህአዴግ ከተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ከአንድነት፣ ከሰማያዊ፣ ከመድረክ እና ከኢዴፓ ጋር በቴሌቭዥን ውይይት አካሂዷል። ውይይቱን ሊመለከቱት ይገባል ብለን እናምናለን። ሁለተኛውን ክፍል ቪዲዮ ከክፍል አንድ ቪዲዮ በታች ያለውን "ሙሉውን አስነብበኝ"ን በመጫን ያገኙታል። የማጫወቻ ቁልፉን በመጫን ይመልክቱ!

ክፍል ፩


ክፍል ፪

የኢትዮጵያውያን ስደተኞች መከራ

(ሊመለከቱት የሚገባ ቪዲዮ!)

የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ግንቦት 29 ቀን 2005 ዓ.ም. (June 6, 2013) ባሰራጨው ፕሮግራም የኢትዮጵያውያን ስደተኞችን መከራ አስመልክቶ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የበደሉ ገፈት ቀማሽ የሆኑት ተጎጂ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ዲፕሎማቶች፣ የኃይማኖት ተቋማት አባቶች፣ ባለሀብቶች፣ የበጎ አድራጎት ተቋማት ኃላፊዎችና በስደትና ተጓዳኝ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ጥናት ያደረጉ ባለሙያዎችን በመጋበዝ አወያይቶ ነበር። ዝግጅቱ በሁለት ክፍል የተከፈለ ሲሆን፣ ሁለቱንም ከዚህ በታች ያገኙዋቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ