በበርሊን ከተማ ደማቅ የተቃውሞ ስልፍ ተደረገ
ዮሃንስ ደሳለኝ (በርሊን -ጀርመኒ)
Ethiopia Zare ሐሙስ ኅዳር 24 ቀን 2007 ዓም December 4, 2014 ከደች ባንክ ብድር ለመጠየቅ ረቡዕ ለታ ከጀርመኗ ቻንስለር መርከል ጋር ውይይት ለማድረግ ወደ ስፍራው ያቀኑት ጠ/ሚር ኃይለማርያም ደሳለኝን በመቃወም በርካታ ኢትዮጵያዊያን በቦታው በመገኘት ተቃውሟቸውን ማስማታቸው ታወቀ፡፡
ዮሃንስ ደሳለኝ (በርሊን -ጀርመኒ)
Ethiopia Zare ሐሙስ ኅዳር 24 ቀን 2007 ዓም December 4, 2014 ከደች ባንክ ብድር ለመጠየቅ ረቡዕ ለታ ከጀርመኗ ቻንስለር መርከል ጋር ውይይት ለማድረግ ወደ ስፍራው ያቀኑት ጠ/ሚር ኃይለማርያም ደሳለኝን በመቃወም በርካታ ኢትዮጵያዊያን በቦታው በመገኘት ተቃውሟቸውን ማስማታቸው ታወቀ፡፡
"... እንደ ኪሩብ ሁሉ - ክንፍ አካል ቢኖረኝ፣ፍኖተ ነፃነት
በዛሬው ዕለት ወደ ቂሊንጦ የተዛወሩትን የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ወደ ስፍራው በማምራት አቶ ሀብታሙ አያሌውን፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺንና ሌሎችን የፖለቲካ እስረኞችን ማነጋገራቸውን ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡
ሙሉውን አስነብበኝ ...ደማቅ ውይይትም አድርገዋል
አቢይ አፈወርቅ
ዕውቁ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና ምሁር ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ባለፈው እሁድ ኦክቶበር 26 ቀን በሲድኒ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጋር ደማቅ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ልዩ የምስጋና ስጦታም ተበርክቶላቸዋል። በዕለቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ተገኝተው አዳራሹ በመሙላቱ የተወሰኑ ታዳሚዎች ከፊትና ከኋላ ባሉ በረንዳዎች ላይ ተደርድረው ፕሮግራሙን ለመከታተል መገደዳቸው ይህ ሪፖርተር ተመልክቷል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...እውቁ ኢትዮጵያዊ ምሁርና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም በሜልበርን የሚገኘው ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ቡድን ባደረገላቸው ግብዣ መሰረት ባለፈው እሮብ ኦክተበር 15 ሜልበርን (አውስትራሊያ) ገብተዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...የገዥው ፓርቲ ቅድመ ምርጫ የጽዳት ዘመቻ
Ethiopia Zare (ቅዳሜ ነሐሴ 17 ቀን 2006 ዓ.ም. August 23, 2014)፦ በአምስት ሣምንታዊ መጽሔቶችና አንድ ጋዜጣ ላይ የተመሰረተውን ክስ ተከትሎ አስራ አንድ ጋዜጠኞች ለስደት ተዳረጉ። አስራ አንዱ ጋዜጠኞች የተሰደዱት በፍትህ ሚኒስቴር ሐምሌ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. "የዐመጸ ቅስቀሳና የሐሰት ወሬዎችን በመንዛት ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመናድ ጥረት አድርገዋል" በሚል በተመሰረተባቸው ክስ መሆኑን ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ የደረሰን መረጃ ያስረዳል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare (ረቡዕ ሐምሌ 14 ቀን 2006 ዓ.ም. August 20, 2014)፡- በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም በሚገኘው የደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን የደብረታቦር በዓል በደማቅ ሁኔታ በትናንትናው ዕለት ተከበረ። ጸሎትና ትምህርቱ በኃይማኖት አባቶች ለምዕመናኑ ከተሰጠ በኋላ፣ ከምሽቱ አንድ ሰዓት (19፡00 ሰዓት) ላይ የበዓሉ መገለጫ የሆነው ችቦ በርቷል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸሙ አሰቃቂ የማሰቃያ (Torture) አይነቶችን በሚመለከት የተጠናቀረ ልዩ ዝግጅት - አቢይ አፈወርቅ (አውስትራሊያ -ሲድኒ)፣ (ልዩ ጥንቅሩን ለማዳመጥ የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!)
የዐቃቤ ሕግ የመሰረተውን ሙሉ ክስ ይዘናል
የዋስትና መብት ተከልክለው ወደቃሊቲና ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተወሰዱ፣ ለሐምሌ 28 ተቀጠሩ
Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም. July 17, 2014)፡- ዛሬ ጠዋት በ84 ቀናቸው በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተሰየመ ችሎት ስድስቱ ጦማርያን በፍቃዱ ኃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ ዘለዓለም ክብረት፣ አቤል ዋበላ እና ሦስቱ ጋዜጠኞች አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሣዬና ተስፋለም ወልደየስ ዐቃቤ ሕግ የመሰረተባቸው የክስ ፋይል ለመጀመሪያ ጊዜ ደርሷቸዋል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሐምሌ 8 ቀን 2006 ዓ.ም. July 15, 2014)፦ ከአቶ ሀብተማርያም ሞገስ እና ከወ/ሮ ደስታ አየለ በ1935 ዓ.ም. የተወለዱት ደራሲ መስፍን ሀብተማርያም እሁድ ሐምሌ 6 ቀን 2006 ዓ.ም. በ71 ዓመታቸው በአዲስ አበባ ከተማ አረፉ።