መቶ አለቃ እሸቱ ዓለሙ ዕድሜ ልክ እስራት ተፈረዳባቸው
ዘሄግ (ታኅሣሥ ፮ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም. / 15 Dec. 2017) ዛሬ ዲሴምበር 15 ቀን 2017 ከቀትር በኋላ በሆላንድ ዘሄግ ከተማ የዋለው ችሎት በመቶ አለቃ በእሸቱ ዓለሙ አቃቤ ሕግ በቀረበባቸው የጦር ወንጀል ክስ ዕድሜ ልክ እስራት በይኖባቸዋል። በተጠቀሰባቸው ክስ በሙሉ ጥፋተኛ ተብለዋል። ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ እንዲህ ዐይነት ፍርድ በሆላንድ አገር ሲሰጥ የመጀመሪያው መሆኑን አቃቤ ሕግ ተናግረዋል። በአገሪቱ ሕግ የዕድሜ ልክ እስራት አመክሮ የለውም።
ሙሉውን አስነብበኝ ...









