ግብጽ ደስተኛ አይደለችም

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሰኔ 16 ቀን 2001 ዓ.ም. June 23, 2009)፦ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወዳጅነታቸው እየጠነከረ የመጣው ኢትዮጵያ እና ሱዳን በወታደራዊ ሥልጠና ዙሪያ ለሦስት ዓመታት የሚቆይ ወታደራዊ ስምምነት በመከላከያ ሚኒስትሮቻቸው በኩል ተፈራረሙ።

 

ሁለቱም ሀገራት ከወታደራዊ ስምምነት በተጨማሪ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ከፍተኛ የጋራ ኮሚሽንና የሀገሪቱ የንግድና ኢኮኖሚ ኮሚቴዎች በስምምነቱ ማግስት ስብሰባ አካሂደዋል።

 

በተያያዘ ዜና ግብጽ በሱዳን ድርጊት ኩርፊያዋን እያሳየች መጥታለች። ከዕለት ዕለት እየሻከረ በመጣው ግንኙነታቸው ምክንያት ግብጽ የሱዳን ዲፕሎማቶቿን በአዳዲስ ሰዎች የተካች ሲሆን፤ የግብጽ ኩርፊያ በዳርፉር ግጭት አፈታት ጉዳይ ግብጽ ገሸሽ ተደርጋ ኳታር በሽምግልና በመመረጧ እንደሆነም ምንጮች ጠቁመዋል።

 

በጋዛ የእስራኤል ጥቃት ወቅት ግብጽ ከእስራኤል ወግናለች በሚል በዓረብ ሀገራት ጣት የተቀሰረባት ሲሆን፤ ጋዛን መልሶ በማልማት ጉዳይ ኳታር በጠራችው የዓረብ ሀገራት ስብሰባ ግብጽ ካለመሳተፏም በተጨማሪ ጉባዔውን “ሀማስን የሚደግፉ ፅንፈኛ ሀገራት የተካፈሉበት ነው” በማለት ተችታለች። በጉባዔው ሱዳን ተካፋይ የነበረች ሲሆን፣ የግብጽ መንግሥት በግዛቴ ላይ የሽብር ተግባር ለመፈጸም ሌት ተቀን ይማስናል፤ ተንኮልም ይሸርብብኛል የምትለውን ሂዝቦላን ሱዳን ማወዳደሷ ሌላው የኩርፊያዋ ሰበብ ነው ተብሏል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ