The Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD)

ታላቁ የህዳሴ ግድብ

ምክር ቤቱ ድርድሩ ውስጥ ይግባ ብለው ሱዳንና ግብጽ ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ አደረገች

ኢዛ (ዓርብ ሰኔ ፲፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 25, 2021)፦ ግብጽ እና ሱዳን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በአፍሪካ ሕብረት እየተደረገ ያለውን ድርድር እንዲያከብሩ ኢትዮጵያ ለጸጥታው ምክር ቤት ጥያቄ አቀረበች። የግብጽንና የሱዳንን ጥያቄም ውድቅ አደረገች።

ኢትዮጵያ ለጸጥታው ምክር ቤት ፕሬዝዳንት በደብዳቤ ባቀረበችው ጥያቄ መሠረት፤ ሱዳን እና ግብጽ በህዳሴው ግድብ በሦስቱ አገራት መካከል በሚደረጉ ድርድሮች የጸጥታው ምክር ቤት ጣልቃ እንዲገባ ያቀረቡትን ሐሳብ እንደማትቀበልም አስታውቃለች።

የጸጥታው ምክር ቤት በድርድሩ ውስጥ እንዲገባ ከሱዳን እና ከግብጽ የቀረበውን ጥያቄ ኢትዮጵያ ከማትቀበልባቸው ምክንያቶች አንዱ የጸጥታው ምክር ቤት ከተሰጠው ተልእኮ ውጭ በመኾኑ ነው።

ሱዳን እና ግብጽ የጸጥታው ምክር ቤት በድርድሩ እንዲገባ የፈለጉት በአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪነት እየተደርገ ያለውን ሒደት ያላገናዘበና በአገሮች መካከል ያለውን መተማመን የሚሸረሽር መኾኑንም የኢትዮጵያ መንግሥት ለምክር ቤቱ በጻፈው ደብዳቤ አስታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ