ምርጫ 2013

በምርጫ 2013 ከፍተኛ ፉክክር ያደረጉት ፓርቲዎች

ኢዜማ ድምፅ መስጠቱ ከተጠናቀቀ በኋላ የምርጫ ሒደቱን በተመለከተ የመጀመሪያውን መግለጫ የሚሰጥ ፓርቲ ይኾናል

ኢዛ (ረቡዕ ሰኔ ፲፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 23, 2021)፦ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስድስተኛውን አገር አቀፍ ምርጫ 2013 ሒደት የተመለከተ ግምገማ ማድረጉን ሲያሳውቅ፤ ኢዜማ አጠቃላይ የምርጫውን ሒደት በተመለከተ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 16 ቀን 2013 ዓ.ም. እንዳስታወቁት፤ ሥራ አስፈጻሚው በቅድመ ምርጫ ዝግጅት፣ በምርጫ ክንውን፣ በሕዝብ ተሳትፎ እና አጠቃላይ የምርጫው ሒደት ላይ ያተኮረ ነበር።

ከምርጫው ጠቅላላ ሒደቱ ጋር የተያያዙ ደካማ እና ጠንካራ ጎኖችን ለማየት መሞከሩን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሥራ አስፈጻሚው ኮሚቴ በሰላም እና ደኅንነት ጉዳዮች እንዲሁም በቀጣይ መሠራት ባለባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ በዘንድሮው ምርጫ ጠንካራ ተፎካካሪ ኾኖ ቀርቦ የነበረው ኢዜማም የምርጫውን አጠቃላይ ይዘት በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ አስታውቋል።

ድምፅ መስጠቱ ከተጠናቀቀ በኋላ የምርጫ ሒደቱን በተመለከተ የመጀመሪያውን መግለጫ የሚሰጥ ፓርቲ ይኾናል።

ከዘንድሮው ምርጫ ጋር በተያያዘ እስካሁን ይፋዊ የኾነ አስተያየት በመስጠት ቀዳሚ መኾን የቻለው የአፍሪካ ሕብረት ታዛቢ ቡድን፤ ምርጫው ሰላማዊ እንደነበር አስታውቀው፤ ከሎጅስቲክ ጋር በተያያዘ ግን ነበር ያሉትን ችግርም ገልጸዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ