Ambassador Dina Mufti

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

አሜሪካ እና ሩሲያም ታዛቢ ይልካሉ

ኢዛ (ማክሰኞ ግንቦት ፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 11, 2021)፦ የአውሮፓ ሕብረት በኢትዮጵያ የሚካሔደውን ስድስተኛውን አገር አቀፍ ምርጫ 2013 ላለመታዘብ ወስዶ የነበረውን አቋም በመለወጥ፤ ምርጫውን የሚታዘቡ ባለሙያዎች እንደሚልክ ማረጋገጫ መስጠቱን እና የአሜሪካ እና የሩሲያ ታዛቢዎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 3 ቀን 2013 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ፤ የአውሮፓ ሕብረት ምርጫውን ለመታዘብ ስድስት አባላት የያዘ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ይመጣል። ከዚህም ሌላ ከአሜሪካ ሁለት ተቋማት የተውጣጣ ቡድን፤ እንዲሁም ከሩሲያ፣ ከአፍሪካ ሕብረትም ምርጫውን የሚታዘቡ ልዑካን እንደሚመጡ ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።

የአውሮፓ ሕብረት ምርጫውን አልታዘብም ባለበት ወቅት አስቀምጧቸው የነበሩ ቅድመ ሁኔታዎችን ኢትዮጵያ የማትቀበል መኾኑን ማስታወቋ ይታወሳል።

በዛሬው መግለጫ ላይም፤ አምባሳደር ዲና የአውሮፓ ሕብረት ቀደሞ ባስቀመጠው ቅድመ ሁኔታ ላይ የኢትዮጵያ አቋም አልተቀየረም ብለዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ